Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 16:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የሐ​ሴ​ቦን እር​ሻ​ዎ​ችና የሴ​ባማ ወይን ግን​ዶች አዝ​ነ​ዋል። የአ​ሕ​ዛብ አለ​ቆች የሰ​ባ​በ​ሩ​አ​ቸው ቅር​ን​ጫ​ፎች እስከ ኢያ​ዜር ደር​ሰው ወደ ምድረ በዳ ወጥ​ተው ነበር፤ ቍጥ​ቋ​ጦ​ቹም ተዘ​ር​ግ​ተው ባሕ​ርን ተሻ​ግ​ረው ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የሐሴቦን ዕርሻ፣ የሴባማም የወይን ተክል ጠውልጓል፤ የአሕዛብ ገዦች፣ ኢያዜርን ዐልፈው፣ ምድረ በዳውን ዘልቀው፣ ሥሮቻቸውን እስከ ባሕር ሰድደው የነበሩትን የተመረጡ የወይን ተክሎችን ረጋግጠዋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የሐሴቦን እርሻዎችና የሴባማ ወይን ግንዶች አዝነዋል። የአሕዛብ አለቆች የሰባበሩአቸው ቅርንጫፎች ኢያዜርን አልፈው ወደ ምድረ በዳ ወጥተው ነበር፤ ቁጥቋጦቹም ተዘርግተው ባሕርን ተሻግረው ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የሀሴቦን እርሻዎችና የሲብማ የወይን ተክል ቦታዎች ተደምስሰዋል፤ እነዚህ የወይን ተክል ቦታዎች የአሕዛብ መሪዎችን የሚያሰክር የወይን ጠጅ ለማዘጋጀት የሚያስችሉ ነበሩ፤ ከዚያ በፊት የእነዚያ የወይን ተክሎች ሐረግ እስከ ያዕዜር ከተማ ድረስ የተንሰራፋ ነበር፤ እንዲሁም በስተ ምዕራብ እስከ ሙት ባሕር ማዶና በስተ ምሥራቅም እስከ በረሓው ይደርስ ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የሐሴቦን እርሻዎችና የሴባማ ወይን ግንዶች አዝነዋል። የአሕዛብ አለቆች የሰባበሩአቸው ቅርንጫፎች እስከ ኢያዜር ደርሰው ወደ ምድረ በዳ ወጥተው ነበር፥ ቍጥቋጦቹም ተዘርግተው ባሕርን ተሻግረው ነበር።

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 16:8
13 Referências Cruzadas  

እና​ንተ የጌ​ላ​ቡሄ ተራ​ሮች ሆይ፥ ዝና​ብና ጠል አይ​ው​ረ​ድ​ባ​ችሁ፤ ቍር​ባ​ን​ንም የሚ​ያ​በ​ቅል እርሻ አይ​ሁ​ን​ባ​ችሁ። የኀ​ያ​ላን ጋሻ በዚያ ወድ​ቆ​አ​ልና፤ የሳ​ኦ​ልም ጋሻ ዘይት አል​ተ​ቀ​ባ​ምና።


እርሱ በልቡ እን​ዲህ አይ​መ​ስ​ለ​ውም፤ እን​ዲ​ህም አያ​ስ​ብም፤ ነገር ግን ማጥ​ፋት፥ ጥቂት ያይ​ደ​ሉ​ት​ንም አሕ​ዛብ መቍ​ረጥ በልቡ አለ።


ሐሴ​ቦ​ንና ኤል​ያሊ ጮኹ፤ ድም​ፃ​ቸ​ውም እስከ ያሳ ድረስ ይሰ​ማል፤ ስለ​ዚህ የሞ​ዓብ ወገብ ይታ​መ​ማል።


ስለ​ዚህ በኢ​ያ​ዜር ልቅሶ ስለ ሴባማ ወይን ግንድ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ፤ ሐሴ​ቦ​ንና ኤል​ያሊ ሆይ፥ ዛፎ​ችሽ ወድ​ቀ​ዋል፤ የዛ​ፍ​ሽን ፍሬና የወ​ይ​ን​ሽን መከር እረ​ግ​ጣ​ለሁ፤ ተክ​ሎ​ችሽ ሁሉ ይወ​ድ​ቃሉ።


የወ​ይን ጠጅ አለ​ቀ​ሰች፤ የወ​ይን ግንድ ደከ​መች፤ ልባ​ቸው ደስ ያለው ሁሉ ተከዙ።


አንቺ የሴ​ባማ ወይን ሆይ! የኢ​ያ​ዜ​ርን ልቅሶ ለአ​ንቺ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ችሽ ባሕ​ርን ተሻ​ግ​ረ​ዋል፤ ወደ ኢያ​ዜ​ርም ባሕር ደር​ሰ​ዋል፤ ሳይ​በ​ስል በሰ​ብ​ል​ሽና በወ​ይ​ንሽ ላይ ጥፋት መጥ​ቶ​አል።


ሙሴም ሰላ​ዮ​ቹን ወደ ኢያ​ዜር ላከ፤ እር​ስ​ዋ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋ​ንም ያዙ፤ በዚ​ያም የነ​በ​ሩ​ትን አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አባ​ረሩ።


“አጣ​ሮት፥ ዲቦን፥ ያዜር፥ ነምራ፥ ሐሴ​ቦን፥ ኤል​ያሌ፥ ሲባማ፥ ናባው፥ ቤያን፤


ሶፋ​ንን፥ ኢያ​ዜ​ርን፥


እነ​ዚ​ህ​ንም የሠ​ሩ​አ​ቸ​ውን ከተ​ሞች በየ​ስ​ማ​ቸው ጠሩ​አ​ቸው።


ቂር​ያ​ታ​ይም፥ ሴባማ፥ ሲራ​ዳት፥ በሸ​ለ​ቆ​ውም ተራራ ያለ​ችው ሲዮን፥


ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ኢያ​ዜ​ርና የገ​ለ​ዓድ ከተ​ሞች ሁሉ፥ የአ​ሞ​ንም ልጆች ምድር እኩ​ሌታ በራ​ባት ፊት እስ​ካ​ለ​ችው እስከ አሮ​ዔር ድረስ፥


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios