Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 14:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የሚ​መ​ለ​ከ​ቱ​ህም ይደ​ነ​ቃሉ፤ እን​ዲ​ህም ይላሉ፦ በውኑ ምድ​ርን ያን​ቀ​ጠ​ቀጠ፥ መን​ግ​ሥ​ታ​ት​ንም ያና​ወጠ፥

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የሚያዩህም አትኵረው እየተመለከቱህ፣ በመገረም ስለ አንተ እንዲህ ይላሉ፤ “ያ ምድርን ያናወጠ፣ መንግሥታትን ያንቀጠቀጠ፣ ይህ ሰው ነውን?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የሚያዩህ ይመለከቱሃልና፦ በውኑ ምድርን ያንቀጠቀጠ፥ መንግሥታትንም ያናወጠ፥

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ሙታንም የአንተን ሁኔታ አይተው በመገረም ተመልክተው እንዲህ ይላሉ፦ “ያ ዓለምን ያንቀጠቀጠና መንግሥታትን ያናወጠ ሰው ይህ ነውን?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 የሚያዩህ ይመለከቱሃልና፦ በውኑ ምድርን ያንቀጠቀጠ፥ መንግሥታትንም ያናወጠ፥

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 14:16
13 Referências Cruzadas  

ምድ​ርን ጐበ​ኘ​ሃት አረ​ካ​ሃ​ትም፥ ብል​ጽ​ግ​ና​ዋ​ንም እጅግ አበ​ዛህ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወንዝ ውኆ​ችን የተ​መላ ነው፤ ምግ​ባ​ቸ​ውን አዘ​ጋ​ጀህ፥ እን​ዲሁ ታሰ​ና​ዳ​ለ​ህና።


ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወ​ድ​ቃ​ለህ፤ ወደ ምድር ጥል​ቅም ትወ​ር​ዳ​ለህ።


ዓለ​ሙን ሁሉ ባድማ ያደ​ረገ፥ ከተ​ሞ​ች​ንም ያፈ​ረሰ፥ ምር​ኮ​ኞ​ቹ​ንም ወደ ቤታ​ቸው ያል​ሰ​ደደ ሰው ይህ ነውን?


ምድ​ርን ሁሉ የም​ት​ፈ​ጫት መዶሻ እን​ዴት ደቀ​ቀች! እን​ዴ​ትስ ተሰ​በ​ረች! ባቢ​ሎ​ንስ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እን​ዴት ባድማ ሆነች!


መቃ​ብ​ራ​ቸው በጕ​ድ​ጓዱ በው​ስ​ጠ​ኛው ክፍል ነው፤ ጉባ​ኤ​ዋም በመ​ቃ​ብ​ርዋ ዙሪያ ነው፤ በሕ​ያ​ዋን ምድር ያስ​ፈሩ ሁሉ በሰ​ይፍ ወድ​ቀው ተገ​ድ​ለ​ዋል።


በሕ​ያ​ዋ​ንም ምድር ኀያ​ላ​ኑን ያስ​ፈሩ ነበ​ርና፤ መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይዘው ወደ ሲኦል ከወ​ረዱ፥ ሰይ​ፋ​ቸ​ው​ንም ከራ​ሳ​ቸው በታች ከአ​ደ​ረጉ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም በአ​ጥ​ን​ታ​ቸው ላይ ከሆነ ጋር ከወ​ደቁ ካል​ተ​ገ​ረዙ ኀያ​ላን ጋር ይተ​ኛሉ።


ርኵሰትንም በላይሽ እጥላለሁ፥ እንቅሽማለሁ፥ ማላገጫም አደርግሻለሁ።


በነገሥታት ላይ ያላግጣሉ፥ መሳፍንትም ዋዛ ሆነውላቸዋል፣ በምሽጉ ሁሉ ይስቃሉ፥ አፈሩንም ከምረው ይወስዱታል።


ስለዚህ መረቡን ይጥላልን? አሕዛብንም ዘወትር ይገድል ዘንድ አይራራምን?


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios