Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሆሴዕ 6:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 “ምሕ​ረ​ታ​ችሁ እንደ ማለዳ ደመና፥ በማ​ለ​ዳም እን​ደ​ሚ​ያ​ልፍ ጠል ነውና ኤፍ​ሬም ሆይ! ምን ላድ​ር​ግ​ልህ? ይሁዳ ሆይ! ምን ላድ​ር​ግ​ልህ?

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 “ኤፍሬም ሆይ፤ ምን ላድርግህ? ይሁዳ ሆይ፤ ምን ላድርግህ? ፍቅራችሁ እንደ ማለዳ ጉም፣ እንደሚጠፋም የጧት ጤዛ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ፍቅራችሁ እንደ ማለዳ ደመና፥ በማለዳም እንደሚያልፍ ጠል ነውና ኤፍሬም ሆይ! ምን ላድርግልህ? ይሁዳ ሆይ! ምን ላድርግልህ?

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! እናንተን ምን ላድርጋችሁ? እናንተ ለእኔ ያላችሁ ፍቅር እንደ ማለዳ ጉምና እንደ ጠዋት ጤዛ ፈጥኖ ይጠፋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ምሕረታችሁ እንደ ማለዳ ደመና፥ በማለዳም እንደሚያልፍ ጠል ነውና ኤፍሬም ሆይ፥ ምን ላድርግልህ? ይሁዳ ሆይ፥ ምን ላድርግልህ?

Ver Capítulo Cópia de




ሆሴዕ 6:4
19 Referências Cruzadas  

በዚ​ህም ሁሉ ከዳ​ተ​ኛ​ዪቱ ይሁዳ በሐ​ሰት እንጂ በፍ​ጹም ልብዋ ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“እኔም፦ ይሁን አልሁ፤ በወ​ን​ዶች ልጆች መካ​ከል እሾ​ም​ሃ​ለሁ፤ አሕ​ዛ​ብን የሚ​ገዛ ሁሉን ቻይ የሆነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ርስት የተ​መ​ረ​ጠ​ች​ውን ምድር ለአ​ንተ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ አባቴ ትለ​ኛ​ለህ፤ ከእ​ኔም አት​መ​ለ​ስም አልሁ ብለ​ሃ​ልና።


እና​ን​ተም ዛሬ ተመ​ል​ሳ​ችሁ ሰው ሁሉ ባል​ን​ጀ​ራ​ውን አር​ነት ለማ​ው​ጣት ዓመተ ኅድ​ገ​ትን በማ​ድ​ረግ በዐ​ይኔ ፊት ቅን የሆ​ነ​ውን ነገር አድ​ር​ጋ​ችሁ ነበር፤ ስሜም በሚ​ጠ​ራ​በት ቤት ውስጥ በፊቴ ቃል ኪዳን አድ​ር​ጋ​ችሁ ነበር።


ለዚ​ህም ሕዝብ የማ​ይ​ሰ​ማና የዐ​መፀ ልብ አላ​ቸው፤ ተመ​ል​ሰ​ውም ሄደ​ዋል።


“ከእ​ነ​ዚህ ነገ​ሮች በየ​ት​ኛው ይቅር እል​ሻ​ለሁ? ልጆ​ችሽ ትተ​ው​ኛል፤ አማ​ል​ክ​ትም ባል​ሆኑ ምለ​ዋል፤ አጠ​ገ​ብ​ኋ​ቸ​ውም፤ እነ​ርሱ ግን አመ​ነ​ዘሩ፤ በአ​መ​ን​ዝ​ራ​ዎ​ቹም ቤት ዐደሩ።


በውኑ ስለ እነ​ዚህ ነገ​ሮች አል​ቀ​ሥ​ፍ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነፍ​ሴስ እን​ደ​ዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አት​በ​ቀ​ል​ምን?


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ አቀ​ል​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እፈ​ት​ና​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት እን​ደ​ዚሁ አደ​ር​ጋ​ለ​ሁና።


እኔም “አም​ል​ኮ​ቴን ትተ​ሃል አልሁ፤ ኤፍ​ሬም ሆይ! እን​ዴት አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ? እስ​ራ​ኤል ሆይ! እን​ዴ​ትስ እደ​ግ​ፍ​ሃ​ለሁ? እን​ዴ​ትስ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ? እንደ አዳማ ነውን? ወይስ እንደ ሲባዮ? ልቤ በው​ስጤ ተና​ው​ጣ​ለች፤ ምሕ​ረ​ቴም ተገ​ል​ጣ​ለች።


ስለ​ዚ​ህም እንደ ማለዳ ደመና፥ በጥ​ዋት እን​ደ​ሚ​ያ​ልፍ ጠል፥ በዐ​ውሎ ነፋ​ስም ከዐ​ው​ድማ እን​ደ​ሚ​በ​ተን እብቅ፥ ከም​ድ​ጃም እን​ደ​ሚ​ወጣ ጢስ ይሆ​ናሉ።


በሐ​ሰት አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፥ ሌባም ገብ​ቶ​አ​ልና፥ በው​ጭም ወን​በ​ዴ​ዎች ቀም​ተ​ዋ​ልና እስ​ራ​ኤ​ልን እፈ​ውስ ዘንድ በወ​ደ​ድሁ ጊዜ የኤ​ፍ​ሬም ኀጢ​አ​ትና የሰ​ማ​ርያ ክፋት ተገ​ለጠ።


ነገር ግን ለጊዜው ነው እንጂ በእርሱ ሥር የለውም፤ በቃሉ ምክንያትም መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያው ይሰናከላል።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ስለ ሠሩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሞ​ዓ​ብን ንጉሥ ዔግ​ሎ​ምን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አበ​ረ​ታ​ባ​ቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios