Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሆሴዕ 12:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በነ​ቢይ እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣው፤ በነ​ቢ​ይም ጠበ​ቀው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ኤፍሬም ግን ክፉኛ አስቈጣው፤ ጌታውም የደም አፍሳሽነቱን በደል በላዩ ላይ ያደርግበታል፤ ስለ ንቀቱም የሚገባውን ይከፍለዋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ጌታም በነቢይ እጅ እስራኤልን ከግብጽ አወጣ፥ በነቢያትም እጅ ጠበቀው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ይሁን እንጂ የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔርን እጅግ አስቈጡት፤ በበደላቸውም ይጠየቁበታል፤ ስሙንም ስለ ሰደቡ ይፈርድባቸዋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እግዚአብሔርም በነቢይ እጅ እስራኤልን ከግብጽ አወጣ፥ በነቢያትም እጅ ጠበቀው።

Ver Capítulo Cópia de




ሆሴዕ 12:14
16 Referências Cruzadas  

ዳዊ​ትም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ባ​ውን እኔ ገድ​ያ​ለሁ ብሎ አፍህ በላ​ይህ መስ​ክ​ሮ​አ​ልና ደምህ በራ​ስህ ላይ ይሁን” አለው።


“እር​ሱም ቀማ​ኛና ደም አፍ​ሳሽ ልጅን፥ ከዚ​ህም ሁሉ አን​ዳ​ቸ​ውን የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ቢወ​ልድ፥


በአ​ራጣ ቢያ​በ​ድር፥ አት​ር​ፎም ቢወ​ስድ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ ሰው በሕ​ይ​ወት አይ​ኖ​ርም፤ ይህን ርኵ​ሰት ሁሉ አድ​ር​ጎ​አ​ልና ፈጽሞ ይሞ​ታል፤ ደሙም በላዩ ይሆ​ናል።


የመ​ለ​ከ​ቱን ድምፅ ሰምቶ ስላ​ል​ተ​ጠ​ነ​ቀቀ ደሙ በራሱ ላይ ይሆ​ናል፤ ቢጠ​ነ​ቀ​ቅስ ኖሮ ነፍ​ሱን በአ​ዳነ ነበር።


ነገር ግን ሐሰት፥ ግዳ​ይና ስር​ቆት፥ ምን​ዝ​ር​ናም ምድ​ርን ሞል​ተ​ዋል፤ ደም​ንም ከደም ጋር ይቀ​ላ​ቅ​ላሉ።


ወደ ከንቱ ነገር ተመ​ለሱ፤ እንደ ጠማማ ቀስ​ትም ሆኑ፤ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውም ከም​ላ​ሳ​ቸው ስን​ፍና የተ​ነሣ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ይህም በግ​ብፅ ምድር ውስጥ መሳ​ለ​ቂያ ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል።


አንተን ለጥፋት፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ለማፍዋጫ እሰጥ ዘንድ የዘንበሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቃችኋል፥ በምክራቸውም ሄዳችኋል፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከወ​ን​ድ​ሞ​ችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስ​ነ​ሣ​ል​ሃል፤ እር​ሱ​ንም ስሙት።


ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቃሌ​ንም በአፉ አኖ​ራ​ለሁ፤ እንደ አዘ​ዝ​ሁ​ትም ይነ​ግ​ራ​ቸ​ዋል፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ እነ​ርሱ በሚ​ወ​ስ​ድህ አሕ​ዛብ መካ​ከል ሁሉ የደ​ነ​ገ​ጥህ፥ ለም​ሳ​ሌና ለተ​ረ​ትም ትሆ​ና​ለህ።


ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ው​ነት ቤትህ፥ የአ​ባ​ት​ህም ቤት፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በፊቴ እን​ዲ​ኖር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ አሁን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያከ​በ​ሩ​ኝን አከ​ብ​ራ​ለ​ሁና፥ የና​ቁ​ኝም ይና​ቃ​ሉና ይህ አይ​ሆ​ን​ል​ኝም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios