Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዕብራውያን 7:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ኢየ​ሱስ ይህን ያህል በም​ት​በ​ል​ጥና ከፍ ባለች ሹመት ተሾመ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከዚህ መሐላ የተነሣ፣ ኢየሱስ ለተሻለ ኪዳን ዋስ ሆኗል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 በዚህ መሐላ ምክንያት ኢየሱስ ለተሻለው ቃል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 በዚህ መሐላ ምክንያት ኢየሱስ ለተሻለው ቃል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።

Ver Capítulo Cópia de




ዕብራውያን 7:22
17 Referências Cruzadas  

እኔ እዋ​ሳ​ለሁ፤ ከእጄ ትሻ​ዋ​ለህ፤ ወደ አንተ ባላ​መ​ጣው፥ በፊ​ት​ህም ባላ​ቆ​መው፥ በዘ​መ​ናት ሁሉ አን​ተን የበ​ደ​ል​ሁህ ልሁን።


እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ በአ​ባቴ ዘንድ ስለ ብላ​ቴ​ናው እን​ዲህ ብዬ ተው​ሼ​አ​ለ​ሁና፦ እር​ሱ​ንስ ወደ አንተ መልሼ በፊ​ትህ ባላ​ቆ​መው በአ​ባቴ ዘንድ በዘ​መ​ናት ሁሉ ኀጢ​አ​ተኛ እሆ​ና​ለሁ።


ለማያውቀው ከተዋሰ ሰው ልብሱን ውሰድ፥ ለእንግዳ የተዋሰውንም እርሱን አግተው።


ልጄ ሆይ፥ ለወዳጅህ ዋስ ብትሆን፥ እጅህን ለባላጋራህ ትሰጣለህ፤


እንደ ሸመላ እን​ዲሁ ጮህሁ፤ እንደ ርግ​ብም አጕ​ረ​መ​ረ​ምሁ፤


ስለ ብዙዎች ለኀጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።


እርሱም “ይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው።


እን​ዲ​ሁም ከእ​ራት በኋላ ጽዋ​ዉን አን​ሥቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ይህ ጽዋ ስለ እና​ንተ በሚ​ፈ​ስ​ሰው ደሜ የሚ​ሆን አዲስ ኪዳን ነው።


እን​ዲ​ሁም ኅብ​ስ​ቱን ከተ​ቀ​በሉ በኋላ ጽዋ​ውን አን​ሥቶ፥ “አዲስ ሥር​ዐት የሚ​ጸ​ና​በት ይህ ጽዋ ደሜ ነው እን​ዲህ አድ​ርጉ፤ በም​ት​ጠ​ጡ​በ​ትም ጊዜ አስ​ቡኝ” አላ​ቸው።


የአ​ዲስ ኪዳ​ንም መካ​ከ​ለኛ ወደ​ሚ​ሆን ወደ ኢየ​ሱስ፥ ከአ​ቤ​ልም ደም ይልቅ የሚ​ሻ​ለ​ውን ወደ​ሚ​ና​ገር ወደ ተረ​ጨው ደሙ ደር​ሳ​ች​ኋል።


በዘ​ለ​ዓ​ለም ኪዳን ደም ለበ​ጎች ትልቅ እረኛ የሆ​ነ​ውን ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ከሙ​ታን ያስ​ነ​ሣው፥


ለእ​ነ​ዚ​ያስ ብዙ​ዎች ካህ​ናት ነበ​ሩ​አ​ቸው፤ ሞት ይሽ​ራ​ቸው፥ እን​ዲ​ኖ​ሩም አያ​ሰ​ና​በ​ታ​ቸ​ውም ነበ​ርና።


አዲስ ትእ​ዛዝ በማ​ለቱ የቀ​ደ​መ​ች​ቱን አስ​ረ​ጃት፤ አሮ​ጌና ውራጅ የሆ​ነ​ውስ ለጥ​ፋት የቀ​ረበ ነው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios