Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዕብራውያን 3:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 አርባ ዘመን የተ​ቈ​ጣ​ቸ​ውስ እነ​ማን ነበሩ? የበ​ደሉ፥ ሬሳ​ቸ​ውም በም​ድረ በዳ የወ​ደ​ቀው አይ​ደ​ሉ​ምን?

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 አርባ ዓመት የተቈጣውስ እነማንን ነበር? ኀጢአት ሠርተው ሬሳቸው በምድረ በዳ ወድቆ የቀረውን አይደለምን?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 አርባ ዓመትስ የተቆጣባቸው እነማን ነበሩ? ሬሳቸው በምድረ በዳ የወደቀ፥ ኃጢአትን ያደረጉት እነርሱ አይደሉምን?

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እግዚአብሔርን አርባ ዓመት ሙሉ ሲያስቈጡት የኖሩ እነማን ነበሩ? እነዚያ ኃጢአት የሠሩና ሬሳቸው በበረሓ ወድቆ የቀረው አይደሉምን?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 አርባ አመትም የተቆጣባቸው እነማን ነበሩ? ሬሳቸው በምድረ በዳ የወደቀ፥ ኃጢአትን ያደረጉት እነርሱ አይደሉምን?

Ver Capítulo Cópia de




ዕብራውያን 3:17
11 Referências Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንደ ነገሠ ለአ​ሕ​ዛብ ንገ​ሩ​አ​ቸው፥ እን​ዳ​ይ​ና​ወ​ጥም ዓለ​ሙን ሁሉ አጸ​ናው፥ አሕ​ዛ​ብ​ንም በቅ​ን​ነት ይገ​ዛል።


የሰ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ሬሳ እንደ ጕድፍ በእ​ርሻ ላይ፥ ማንም እን​ደ​ማ​ይ​ሰ​በ​ስ​በው ከአ​ጫ​ጆች በኋላ እን​ደ​ሚ​ቀር ቃር​ሚያ ይወ​ድ​ቃል።


በግ​ብፅ ምድ​ርና በም​ድረ በዳ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ተአ​ም​ራ​ቴ​ንና ክብ​ሬን ያዩ እነ​ዚህ ሰዎች ሁሉ ዐሥር ጊዜ ስለ ተፈ​ታ​ተ​ኑኝ፥ ቃሌ​ንም ስላ​ል​ሰሙ፥


እን​ዲህ በላ​ቸው፦ እኔ ሕያው ነኝና በጆ​ሮዬ እንደ ተና​ገ​ራ​ች​ሁት እን​ዲሁ በእ​ው​ነት አደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በድ​ኖ​ቻ​ችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወ​ድ​ቃሉ፤ የተ​ቈ​ጠ​ራ​ችሁ ሁሉ፥ እንደ ቍጥ​ራ​ችሁ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ የሆነ ሁሉ፥ እና​ንተ ያጕ​ረ​መ​ረ​ማ​ች​ሁ​ብኝ፥


ስለ​ዚ​ያ​ችም ምድር ክፉን ነገር ተና​ገሩ፤ ስለ​ዚ​ያ​ችም ምድር ክፉ የተ​ና​ገሩ እነ​ዚያ ሰዎች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በመ​ቅ​ሠ​ፍት ሞቱ፤ ምድ​ሪቱ ግን መል​ካም ነበ​ረች።


ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ ጌታ ከግብጽ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios