Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዕብራውያን 13:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ የም​ክ​ርን ቃል እን​ድ​ት​ቀ​በሉ እመ​ክ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ በጥ​ቂት ቃል ጽፌ​ላ​ች​ኋ​ለ​ሁና።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ወንድሞች ሆይ፤ የጻፍሁላችሁ መልእክት ዐጭር እንደ መሆኑ፣ የምክር ቃሌን በትዕግሥት እንድትቀበሉ ዐደራ እላችኋለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ወንድሞች ሆይ! ይህን በጥቂት ቃል የጻፍኩላችሁን የምክርን ቃል እንድትታገሡ እመክራችኋለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ወንድሞች ሆይ! ይህ የጻፍኩላችሁ መልእክት አጭር ስለ ሆነ ይህን የምክር ቃሌን በትዕግሥት እንድትቀበሉ አጥብቄ እለምናችኋለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ወንድሞች ሆይ፥ የምክርን ቃል እንድትታገሡ እመክራችኋለሁ፥ በጥቂት ቃል ጽፌላችኋለሁና።

Ver Capítulo Cópia de




ዕብራውያን 13:22
22 Referências Cruzadas  

ኦሪ​ት​ንና ነቢ​ያ​ትን ካነ​በቡ በኋ​ላም የም​ኵ​ራቡ አለ​ቆች፥ “እና​ንተ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ለሕ​ዝብ ሊነ​ገር የሚ​ገ​ባው የም​ክር ቃል እንደ አላ​ችሁ ተና​ገሩ” ብለው ላኩ​ባ​ቸው።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኔ ጳው​ሎስ በእ​ና​ንተ ዘንድ ፊት ለፊት ሳለሁ ትሑት የሆ​ንሁ፥ ከእ​ና​ንተ ብርቅ ግን የም​ደ​ፍ​ራ​ችሁ በክ​ር​ስ​ቶስ የዋ​ህ​ነ​ትና ቸር​ነት እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፥ በፍ​ቅ​ራ​ችሁ እታ​መ​ና​ለ​ሁና።


እኛስ በክ​ር​ስ​ቶስ አም​ሳል እን​ለ​ም​ና​ለን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእኛ መጽ​ና​ና​ትን ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጋር ትታ​ረቁ ዘንድ በክ​ር​ስ​ቶስ እን​ለ​ም​ና​ች​ኋ​ለን።


ከእ​ር​ሱም ጋር አብ​ረን እየ​ሠ​ራን፥ የተ​ቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ለከ​ንቱ እን​ዳ​ታ​ደ​ር​ጓት እን​ማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለን።


በእጄ እንደ ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ እዩ።


አስ​ቀ​ድሞ በጥ​ቂቱ እንደ ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ ይህን ምሥ​ጢር ገልጦ አሳ​ይ​ቶ​ኛ​ልና።


እንደ ልጆ​ችም ከእ​ና​ንተ ጋር፥ “ልጄ ሆይ፥ የጌ​ታን ቅጣት አታ​ቅ​ልል በሚ​ገ​ሥ​ጽ​ህም ጊዜ አት​ድ​ከም።


ይል​ቁ​ንም ፈጥኜ እን​ድ​መ​ለ​ስ​ላ​ችሁ ይህን ታደ​ርጉ ዘንድ አጥ​ብቄ እለ​ም​ና​ች​ኋ​ለሁ።


ስለ​ዚ​ህም ከሰ​ማ​ነው ነገር ምን​አ​ል​ባት እን​ዳ​ን​ወ​ሰድ ለእ​ርሱ አብ​ዝ​ተን ልን​ጠ​ነ​ቀቅ ይገ​ባ​ናል።


አሁ​ንም ከሰ​ማ​ያዊ ጥሪ ተካ​ፋ​ዮች የሆ​ና​ችሁ ቅዱ​ሳን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የሃ​ይ​ማ​ኖ​ታ​ች​ንን ሐዋ​ር​ያና ሊቀ ካህ​ናት ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ተመ​ል​ከቱ።


እን​ግ​ዲህ አን​ፍራ፤ ወደ ዕረ​ፍ​ቱም እን​ድ​ን​ገባ ትእ​ዛ​ዙን አን​ተው፤ ከእ​ና​ን​ተም ምን​አ​ል​ባት በተ​ለ​መደ ስሕ​ተት የሚ​ገ​ኝና የሚ​ጸና ቢኖር ወደ ዕረ​ፍቱ እን​ዲ​ገባ የሚ​ተ​ዉት አይ​ም​ሰ​ለው።


እን​ግ​ዲህ እንደ እነ​ዚያ እንደ ካዱት እን​ዳ​ን​ወ​ድቅ፥ ወደ ዕረ​ፍቱ እን​ገባ ዘንድ እን​ፋ​ጠን።


እየመከርኋችሁና የምትቆሙባት ጸጋ እውነትኛ የእግዚአብሔር ጸጋ እንድትሆን እየመሰከርሁላችሁ፥ የታመነ ወንድም እንደ ሆነ በቈጠርሁት በስልዋኖስ እጅ በአጭሩ ጽፌላችኋለሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios