Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዕብራውያን 13:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ሊቀ ካህ​ናቱ የሚ​ሠ​ዉ​ትን እን​ስሳ ደም ስለ ኀጢ​አት ወደ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳን ያቀ​ርብ ነበ​ርና፤ ሥጋ​ው​ንም ከሰ​ፈር ውጭ ያቃ​ጥ​ሉት ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ሊቀ ካህናቱ ስለ ኀጢአት ስርየት የሚሆነውን የእንስሳት ደም ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ይገባል፤ የእንስሳቱ ሥጋ ግን ከሰፈር ውጭ ይቃጠላል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሊቀ ካህናት ስለ ኃጢአት የእንስሶችን ደም ወደ ቅድስት ያቀርባል፤ ሥጋቸው ግን ከሰፈሩ ውጭ ይቃጠላል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የአይሁድ የካህናት አለቃ የኃጢአት ይቅርታን የሚያስገኘውን የእንስሳት ደም ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ይገባል፤ የእንስሳቱ በድን ግን ከሰፈሩ ውጪ ይቃጠላል፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሊቀ ካህናት ስለ ኃጢአት ወደ ቅድስት የእንስሶችን ደም ያቀርባልና፤ ሥጋቸው ግን ከሰፈሩ ውጭ ይቃጠላል።

Ver Capítulo Cópia de




ዕብራውያን 13:11
13 Referências Cruzadas  

የወ​ይ​ፈ​ኑን ሥጋ ግን፥ ቍር​በ​ቱ​ንም፥ ፈር​ሱ​ንም ከሰ​ፈር ውጭ በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ለ​ዋ​ለህ፤ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና።


ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን ወይ​ፈን ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ በመ​ቅ​ደ​ሱም ውጭ በቤቱ በተ​ለ​የው ስፍራ ይቃ​ጠ​ላል።


ለማ​ስ​ተ​ስ​ረ​ያም እን​ዲ​ሆን ደማ​ቸው ወደ መቅ​ደስ የገ​ባ​ውን የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈ​ንና የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ፍየል ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ ያወ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ ቍር​በ​ታ​ቸ​ው​ንም፥ ሥጋ​ቸ​ው​ንም፥ ፈር​ሳ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላሉ።


ልብ​ሱ​ንም ያወ​ል​ቃል፤ ሌላም ልብስ ይለ​ብ​ሳል፤ አመ​ዱ​ንም ተሸ​ክሞ ከሰ​ፈሩ ንጹሕ ወደ ሆነ ስፍራ ወደ ውጭ ያወ​ጣ​ዋል።


ነገር ግን በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ለማ​ስ​ተ​ስ​ረያ ይሆን ዘንድ ከደሙ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን የሚ​ገ​ባው የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁሉ አይ​በ​ላም፤ በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላል።


ሥጋ​ው​ንና ቍር​በ​ቱ​ንም ከሰ​ፈሩ ውጭ በእ​ሳት አቃ​ጠሉ።


የአ​ሮ​ንም ልጆች ደሙን አቀ​ረ​ቡ​ለት፤ ጣቱ​ንም በደሙ ውስጥ ነክሮ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ቀን​ዶች ቀባ፤ ደሙ​ንም ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች አፈ​ሰ​ሰው።


እር​ስ​ዋ​ንም ለካ​ህኑ ለአ​ል​ዓ​ዛር ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ፤ ከሰ​ፈር ወደ ውጭ ወደ ንጹሕ ስፍራ ይወ​ስ​ዷ​ታል፤ በፊ​ቱም ያር​ዷ​ታል።


ካህ​ኑም ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በውሃ ይታ​ጠ​ባል፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገ​ባል፤ ካህ​ኑም እስከ ማታ ርኩስ ይሆ​ናል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios