Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዕብራውያን 12:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ያን​ጊዜ ቃል ምድ​ርን አና​ወ​ጣት፤ “አሁ​ንም እኔ ምድ​ርን እንደ ገና አንድ ጊዜ አና​ው​ጣ​ታ​ለሁ” ብሎ ተና​ገረ፤ ምድ​ርን ብቻም አይ​ደ​ለም፤ ሰማ​ይ​ንም ጭምር እንጂ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በዚያ ጊዜ ድምፁ ያናወጠው ምድርን ነበር፤ አሁን ግን፣ “አንድ ጊዜ እንደ ገና ምድርን ብቻ ሳይሆን፣ ሰማያትንም አናውጣለሁ” ብሎ ቃል ገብቷል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ያንጊዜ ድምፁ ምድርን አናወጧት ነበር፤ አሁን ግን “አንድ ጊዜ ደግሜ እኔ ሰማይን አናውጣለሁ እንጂ ምድርን ብቻ አይደለም፤” ብሎ ተስፋ ሰጥቶአል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 በዚያን ጊዜ ቃሉ ምድርን አናውጦአል፤ አሁን ግን “ምድርን ብቻ ሳይሆን አንድ ጊዜ ደግሜ ሰማይን ጭምር አናውጣለሁ” በማለት ቃል ገብቶአል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በዚያም ጊዜ ድምፁ ምድርን አናወጠ፥ አሁን ግን፦ አንድ ጊዜ ደግሜ እኔ ሰማይን አናውጣለሁ እንጂ ምድርን ብቻ አይደለም ብሎ ተስፋ ሰጥቶአል።

Ver Capítulo Cópia de




ዕብራውያን 12:26
12 Referências Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ሳት ስለ ወረ​ደ​በት የሲና ተራራ ሁሉ እንደ ምድጃ ጢስ ይጤስ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም እንደ እቶን ጢስ ያለ ጢስ ይወጣ ነበር፤ ተራ​ራ​ውም ሁሉ እጅግ ይና​ወጥ ነበር፤ ሕዝ​ቡም ፈጽ​መው ደነ​ገጡ።


ስለ​ዚህ በሠ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓት በጽኑ ቍጣው ቀንም ሰማ​ያት ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ምድ​ርም ከመ​ሠ​ረቷ ትና​ወ​ጣ​ለች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምድ​ርን ያና​ውጥ ዘንድ በተ​ነሣ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ፍ​ራ​ትና ከግ​ር​ማው ክብር የተ​ነሣ ወደ ድን​ጋይ ዋሻና ወደ ምድር ንቃ​ቃት ውስጥ ያገ​ቡ​አ​ቸ​ዋል።


“እኔ የም​ሠ​ራ​ቸው አዲስ ሰማ​ይና አዲስ ምድር በፊቴ ጸን​ተው እን​ደ​ሚ​ኖሩ፥ እን​ዲሁ ዘራ​ች​ሁና ስማ​ችሁ ጸን​ተው ይኖ​ራሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጽ​ዮን ሆኖ ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ ይጮ​ኻል፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሆኖ ቃሉን ይሰ​ጣል፤ ሰማ​ይና ምድ​ርም ይና​ወ​ጣሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ለሕ​ዝቡ ይራ​ራል፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ያጸ​ናል።


ተራሮች አንተን አይተው ተጨነቁ፣ የውኃ ሞገድ አልፎአል፣ ቀላዩም ድምፁን ሰጥቶአል፥ እጁንም ወደ ላይ አንሥቶአል።


ለይሁዳ አለቃ ለዘሩባቤል ተናገር እንዲህም በል፦ ሰማያትንና ምድርን አናውጣለሁ፣


የመንግሥታትንም ዙፋን እገለብጣለሁ፥ የአሕዛብንም መንግሥታት ኃይል አጠፋለሁ፣ ሰረገሎችንና የሚቀመጡባቸውንም እገለብጣለሁ፣ ፈረሶችና ፈረሰኞቻቸውም እያንዳንዳቸው በወንድማቸው ሰይፍ ይወድቃሉ።


አንድ ጊዜ ደግሞ ያለ​ውም ፍጡ​ራን ናቸ​ውና፥ የማ​ይ​ና​ወ​ጠው ይኖር ዘንድ፥ የሚ​ና​ወ​ጠ​ውን እን​ደ​ሚ​ያ​ሳ​ል​ፈው ያሳ​ያል።


አቤቱ! ከሴ​ይር በወ​ጣህ ጊዜ፥ ከኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ሜዳ በተ​ራ​መ​ድህ ጊዜ፥ ምድ​ሪቱ ተና​ወ​ጠች፤ ሰማ​ያ​ትም ጠልን አን​ጠ​ባ​ጠቡ፤ ደመ​ና​ትም ደግሞ ውኃን አን​ጠ​ባ​ጠቡ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios