Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዕብራውያን 12:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 አን​ካ​ሳ​ነ​ታ​ችሁ እን​ዲ​ድ​ንና እን​ዳ​ት​ሰ​ነ​ካ​ከሉ ለእ​ግ​ሮ​ቻ​ችሁ የቀና መን​ገ​ድን አድ​ርጉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ዐንካሳው እንዲፈወስ እንጂ የባሰውኑ እንዳያነክስ “ለእግራችሁ ቀና መንገድ አብጁ።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 አንካሳውም እንዲፈወስ እንጂ እንዳይሰበር፥ ለእግራችሁ ቀና መንገድ አበጁ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 አንካሳ የሆነው እንዲፈወስ እንጂ ከቦታው ወጥቶ እንዳይናጋ ለእግራችሁ የቀና መንገድ አድርጉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ያነከሰውም እንዲፈወስ እንጂ እንዳይናጋ፥ ለእግራችሁ ቅን መንገድ አድርጉ።

Ver Capítulo Cópia de




ዕብራውያን 12:13
15 Referências Cruzadas  

ደካ​ሞች እጆ​ችና አን​ካ​ሶች ጕል​በ​ቶች፥ ጽኑ።


በዚ​ያን ጊዜ አን​ካ​ሳ​ዎች እንደ ሚዳቋ ይዘ​ል​ላሉ፤ የዲ​ዳ​ዎ​ችም ምላስ ርቱዕ ይሆ​ናል፤ በም​ድረ በዳ ውኃ፥ በተ​ጠማ መሬ​ትም ፈሳሽ ይፈ​ል​ቃ​ልና።


ዕው​ሮ​ች​ንም በማ​ያ​ው​ቋት መን​ገድ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የማ​ያ​ው​ቋ​ት​ንም ጎዳና እን​ዲ​ረ​ግጡ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ጨለ​ማ​ውን ብር​ሃን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ጠማ​ማ​ው​ንም አቀ​ና​ለሁ። ይህ​ንም አደ​ር​ግ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አል​ተ​ዋ​ቸ​ው​ምም።


ከድሮ ዘመን የፈ​ረ​ሱት ስፍ​ራ​ዎ​ችህ ይሠ​ራሉ፤ መሠ​ረ​ት​ህም ለልጅ ልጅ ዘመን ይሆ​ናል፤ አን​ተም፦ ሰባ​ራ​ውን ጠጋኝ፥ የመ​ኖ​ሪያ መን​ገ​ድ​ንም አዳሽ ትባ​ላ​ለህ።


ሕዝቤ ግን ረስ​ተ​ው​ኛል፤ ለከ​ንቱ ነገ​ርም አጥ​ነ​ዋል፤ የቀ​ድ​ሞ​ውን ጐዳና ትተው ወደ ጠማ​ማ​ውና ወደ ሰን​ከ​ል​ካ​ላው መን​ገድ ለመ​ሄድ በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ተሰ​ና​ከሉ።


ጐድ​ጓ​ዳው ሁሉ ይምላ፤ ተራ​ራ​ውም፥ ኮረ​ብ​ታ​ውም ሁሉ ዝቅ ይበል፤ ሰን​ከ​ል​ካ​ላ​ውም የቀና ጥር​ጊያ ይሁን፤ ወጣ ገባው መን​ገ​ድም ይስ​ተ​ካ​ከል።


ነገር ግን ወደ እው​ነ​ተ​ኛው ወን​ጌል እግ​ራ​ቸ​ውን እን​ዳ​ላ​ቀኑ ባየሁ ጊዜ፥ በሰው ሁሉ ፊት ኬፋን እን​ዲህ አል​ሁት፥ “አንተ አይ​ሁ​ዳዊ ስት​ሆን በአ​ይ​ሁድ ሥር​ዐት ያይ​ደለ፥ በአ​ረ​ማ​ው​ያን ሥር​ዐት የም​ት​ኖር ከሆነ እን​ግ​ዲህ አይ​ሁድ እን​ዲ​ሆኑ አረ​ማ​ው​ያ​ንን ለምን ታስ​ገ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለህ?”


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ከእ​ና​ንተ ወገን የተ​ሳ​ሳተ ሰው ቢኖር በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የጸ​ና​ችሁ እና​ንት እን​ዳ​ት​ሳ​ሳቱ ለራ​ሳ​ችሁ እየ​ተ​ጠ​በ​ቃ​ችሁ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ሰው ቅን​ነት ባለው ልቡና አጽ​ኑት።


እርስ በርሳችሁ በኀጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኀይል ታደርጋለች።


ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios