Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዕብራውያን 11:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ሴቶ​ችም እንደ ትን​ሣኤ ቀን ተነ​ሥ​ተ​ው​ላ​ቸው ሙታ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ተቀ​በሉ፤ ተፈ​ር​ዶ​ባ​ቸው የሞ​ቱም አሉ፤ የም​ት​በ​ል​ጠ​ውን ሕይ​ወት ያገኙ ዘንድ ሊድኑ አል​ወ​ደ​ዱ​ምና።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ሴቶች፣ ሙታናቸው ተነሡላቸው። ሌሎቹ ደግሞ የተሻለውን ትንሣኤ ለማግኘት ሲሉ፣ መትረፍን ንቀው ለሞት ለሚዳርግ ሥቃይ ራሳቸውን ሰጡ፤ ከዚህም ነጻ ለመውጣት አልፈለጉም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም የሚታደጓቸውን ሳይሹ የሚበልጠውን ትንሣኤ ለማግኘት እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ሴቶች የሞቱባቸውን ዘመዶቻቸውን ከሞት ተነሥተው አገኘአቸው። ሌሎችም የበለጠ ትንሣኤ ለማግኘት አስበው ልዩ ልዩ ሥቃይ ተቀበሉ፤ ከእስራት ነጻ መሆንንም አልፈቀዱም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤

Ver Capítulo Cópia de




ዕብራውያን 11:35
17 Referências Cruzadas  

በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡምም።


ከሙታንስ ሲነሡ በሰማያት እንዳሉ መላእክት ይሆናሉ እንጂ አያገቡም፤ አይጋቡምም።


አን​ተም ብፁዕ ትሆ​ና​ለህ፤ የሚ​ከ​ፍ​ሉህ የላ​ቸ​ው​ምና፤ ነገር ግን ጻድ​ቃን በሚ​ነ​ሡ​በት ጊዜ ዋጋ​ህን ታገ​ኛ​ለህ።”


እን​ግ​ዲህ ወዲህ ሞት የለ​ባ​ቸ​ውም፤ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ናቸው እንጂ፤ የት​ን​ሣኤ ልጆ​ችም ስለ​ሆኑ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ይሆ​ናሉ።


መል​ካም የሠሩ ለሕ​ይ​ወት ትን​ሣኤ፥ ክፉ የሠ​ሩም ለፍ​ርድ ትን​ሣኤ ይነ​ሣሉ።


ከዚ​ህም በኋላ ይመ​ረ​ም​ሩት ዘንድ የሚ​ሹት ተዉት፤ የሻ​ለ​ቃ​ውም ሮማዊ መሆ​ኑን በዐ​ወቀ ጊዜ“ ለምን አሰ​ር​ሁት?” ብሎ ፈራ።


ጳው​ሎ​ስም እኩ​ሌ​ቶቹ ሰዱ​ቃ​ው​ያን እኩ​ሌ​ቶ​ቹም ፈሪ​ሳ​ው​ያን እንደ ሆኑ ዐውቆ፥ “እኔ ፈሪ​ሳዊ የፈ​ሪ​ሳዊ ልጅ ነኝ፤ ስለ ተስ​ፋና ስለ ሙታን መነ​ሣ​ትም ይፈ​ረ​ድ​ብ​ኛል” ብሎ በአ​ደ​ባ​ባይ ጮኸ።


እነ​ር​ሱም ለጻ​ድ​ቃ​ንና ለኃ​ጥ​ኣን የሙ​ታን ትን​ሣኤ ይሆን ዘንድ እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቁ ለእ​ኔም እን​ዲሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ተስፋ አለኝ።


ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም እን​ዲህ ብለው መለ​ሱ​ላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያይ​ደለ እና​ን​ተን ልን​ሰማ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይገ​ባ​ልን? እስኪ እና​ንተ ራሳ​ችሁ ፍረዱ።


እጁ​ንም ለእ​ር​ስዋ ሰጥቶ አስ​ነ​ሣት፤ ቅዱ​ሳ​ን​ንና ባል​ቴ​ቶ​ች​ንም ጠርቶ እር​ስ​ዋን አድኖ ሰጣ​ቸው።


ይህ የሚ​ፈ​ር​ሰው የማ​ይ​ፈ​ር​ሰ​ውን በለ​በሰ ጊዜ፥ የሚ​ሞ​ተ​ውም የማ​ይ​ሞ​ተ​ውን በለ​በሰ ጊዜ፤ “ሞት በመ​ሸ​ነፍ ተዋጠ” ተብሎ የተ​ጻ​ፈው ያን​ጊዜ ይፈ​ጸ​ማል።


ይኸ​ውም ሙታን በሚ​ነሡ ጊዜ ምና​ል​ባት በዚህ አገ​ኘው እንደ ሆነ ብዬ ነው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios