Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዕንባቆም 2:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ብዙ አሕዛብን አጥፍተሃልና ለቤትህ እፍረትን መክረሃል፥ በነፍስህም ላይ ኃጢአትን አድርገሃል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የብዙ ሰዎች ነፍስ እንዲጠፋ አሢረሃል፤ በገዛ ቤትህ ላይ ውርደትን፣ በራስህም ላይ ጥፋትን አምጥተሃል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ብዙ ሕዝቦችን ቆራርጠህ ለቤትህ እፍረትን መክረሃል፥ በነፍስህም ላይ ኃጢአትን አድርገሃል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ተንኰልን ዐቅደህ ብዙ ሰዎችን በመግደል በቤትህ ኀፍረትን አምጥተሃል፤ ሕይወትህንም ለአደጋ አጋልጠሃል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ብዙ አሕዛብን አጥፍተሃልና ለቤትህ እፍረትን መክረሃል፥ በነፍስህም ላይ ኃጢአትን አድርገሃል።

Ver Capítulo Cópia de




ዕንባቆም 2:10
16 Referências Cruzadas  

ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን፦ እን​ዲህ ሲል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማለ። “አዶ​ን​ያስ ይህን ቃል በሕ​ይ​ወቱ ላይ እንደ ተና​ገረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ያድ​ር​ግ​ብኝ፤ ይህ​ንም ይጨ​ም​ር​ብኝ።


ደብ​ዳ​ቤ​ውም በደ​ረ​ሳ​ቸው ጊዜ የሀ​ገሩ ሰዎች የን​ጉ​ሡን ልጆች ሰባ​ውን ሰዎች ይዘው ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም በቅ​ር​ጫት አድ​ር​ገው ወደ እርሱ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ላኩ።


በእ​ው​ነት የና​ቡ​ቴ​ንና የል​ጆ​ቹን ደም ትና​ን​ትና አይ​ቻ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ በዚ​ህም እርሻ እበ​ቀ​ለ​ዋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ረው ቃል ወስ​ደህ በእ​ር​ሻው ውስጥ ጣለው።”


መግደልን የለመዱ እነርሱ ክፋትን ለራሳቸው ይሰበስባሉ። የኀጢአተኞች ሰዎች አወዳደቃቸው ክፉ ነው።


የንጉሥ ቍጣ ከአንበሳ ቍጣ አያንስም፤ የሚያስቈጣውም ሰው የራሱን ነፍስ ይበድላል።


በእኔ ላይ በደልን የሚፈጽሙ ራሳቸውን ይበድላሉ፤ የሚጠሉኝም ሞትን ይወድዳሉ።


ዛሬ ታያ​ላ​ችሁ፤ ዛሬ ታደ​ን​ቃ​ላ​ችሁ፤ የመ​ን​ፈ​ሳ​ች​ሁም ኀይል ከንቱ ይሆ​ናል፤ እሳ​ትም ትበ​ላ​ች​ኋ​ለች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በዘ​መኑ አይ​ከ​ና​ወ​ን​ምና፥ ከዘ​ሩም በዳ​ዊት ዙፋን የሚ​ቀ​መጥ አይ​ነ​ሣ​ምና፥ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ለይ​ሁዳ ገዢ አይ​ሾ​ም​ምና ይህን ሰው እንደ ሞተ ቍጠ​ሪው” አለ።


በውኑ የይ​ሁዳ ንጉሥ ሕዝ​ቅ​ያ​ስና ሕዝቡ ሁሉ ገደ​ሉ​ትን? በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ፈ​ሩ​ምን? ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ አል​ተ​ማ​ለ​ሉ​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ የተ​ና​ገ​ረ​ባ​ቸ​ውን ክፉ ነገር አይ​ተ​ዉ​ምን? እኛም በነ​ፍ​ሳ​ችን ላይ ታላቅ ክፋት እና​ደ​ር​ጋ​ለን።”


ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም እር​ሱ​ንና ዘሩን አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም በመ​ዓት እጐ​በ​ኛ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም አል​ሰ​ሙ​ምና የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ባ​ቸ​ውን ክፉ ነገር ሁሉ በእ​ነ​ርሱ ላይና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሚ​ቀ​መጡ በይ​ሁ​ዳም ሰዎች ላይ አመ​ጣ​ለሁ።”


“አሁ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከይ​ሁዳ ወገን መካ​ከል ቅሬታ እን​ዳ​ይ​ቀ​ር​ላ​ችሁ፥ ወን​ድ​ንና ሴትን፥ ብላ​ቴ​ና​ንና የሚ​ጠባ ሕፃ​ንን ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ታጠፉ ዘንድ ይህን ታላቅ ክፋት በራ​ሳ​ችሁ ላይ ለምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?


እግዚአብሔርም ከስምህ ማንም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይዘራ ስለ አንተ አዝዞአል፣ ከአምላኮችህ ቤት የተቀረጸውንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል አጠፋለሁ። አንተም የተጠቃህ ነህና መቃብርህን እምሳለሁ።


በክብር ፋንታ እፍረት ሞልቶብሃል፣ አንተ ደግሞ ጠጥተህ ተንገድገድ፣ የእግዚአብሔር የቀኙ ጽዋ ይመለስብሃል፥ እፍረትም በክብርህ ላይ ይሆናል።


የእ​ነ​ዚህ ኃጥ​ኣን ጥና​ዎ​ቻ​ቸው በሰ​ው​ነ​ታ​ቸው ጥፋት ተቀ​ድ​ሰ​ዋ​ልና፤ የተ​ጠ​ፈ​ጠፈ ሰሌዳ አድ​ር​ጋ​ቸው፤ ለመ​ሠ​ዊያ መለ​በ​ጫም ይሁኑ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቅ​ር​በ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና የተ​ቀ​ደሱ ናቸው፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ምል​ክት ይሆ​ናሉ።”


ሕዝቡም ሁሉ መልሰው “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን፤” አሉ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios