Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 6:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምድ​ርን እንደ ተበ​ላ​ሸች፥ ሥጋን የለ​በሱ ሁሉም በም​ድር ላይ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን እንደ አበ​ላሹ አየ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እግዚአብሔር ምድር ምን ያህል በክፉ ሥራ እንደ ረከሰች አየ። እነሆ፤ ሰው ሁሉ አካሄዱን አበላሽቶ ነበርና

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እግዚአብሔርም ምድርን አየ፥ እነሆም፥ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በምድር ላይ መንገዳቸውን አበላሽተው ነበርና፥ ምድር የተበላሸች ነበረች።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እግዚአብሔር ዓለምን ተመለከተ፤ የተበላሸች እንደ ሆነችና በውስጧም ያሉት ሰዎች ሁሉ በክፋት እንደሚኖሩ አየ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እግዚአብሔርም ምድርን አየ፤ እነሆም ተበላሸች ሥጋን የለበሰ ሁሉ በምድር ላይ መንገዱን አበላሽቶ ነበርና።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 6:12
18 Referências Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ብ​ር​ሃም አለው፥ “የሰ​ዶ​ምና የገ​ሞራ ጩኸት በእኔ ዘንድ በዛ፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም እጅግ ከበ​ደች፤


እን​ግ​ዲ​ህስ ወደ እኔ እንደ መጣች እንደ ጩኸቷ ይፈ​ጽ​ሙ​አት እንደ ሆነ አይ ዘንድ እወ​ር​ዳ​ለሁ፤ እን​ዲ​ሁም ባይ​ሆን አው​ቃ​ለሁ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ኖኅን አለው፥ “የሰው ሁሉ ጊዜው በፊቴ ደር​ሶ​አል፤ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ነሣ ምድር በግፍ ተመ​ል​ታ​ለ​ችና፤ እኔም እነሆ፥ ከም​ድር ጋር አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ኖኅ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሞገ​ስን አገኘ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ኖኅን አለው፥ “አንተ ቤተ​ሰ​ቦ​ች​ህን ሁሉ ይዘህ ወደ መር​ከብ ግባ፤ በዚህ ትው​ልድ በፊቴ ጻድቅ ሆነህ አይ​ች​ሃ​ለ​ሁና።


በም​ድር ላይ ሥጋ ያለው የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰው ሁሉ ወፉም፥ እን​ስ​ሳ​ውም፥ አራ​ዊ​ቱም፥ በም​ድር ላይ የሚ​ር​መ​ሰ​መ​ሰው ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሹ​ም​ሁሉ፥ ሰውም ሁሉ ጠፋ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ለኖኅ አለው፥ “በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል፥ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ባለው በሕ​ያው ነፍስ ሁሉ መካ​ከል፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ትው​ልድ የማ​ደ​ር​ገው የቃል ኪዳኔ ምል​ክት ይህ ነው፤


ያን​ጊ​ዜም ሰው ራሱን ይነ​ቅ​ፋል፤ እን​ዲ​ህም ይላል፦ ‘እኔ ምን አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ? እንደ ኀጢ​አ​ቶ​ችም መጠን አል​ቀ​ጣ​ኝም፤


የእግዚአብሔር ዐይኖች በሁሉ ቦታ ናቸው፤ ክፉዎችንና ደጎችንም ይመለከታሉ።


ሰውም ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትድ​ግና ይይ።”


ለቀደመውም ዓለም ሳይራራ ከሌሎች ሰባት ጋር ጽድቅን የሚሰብከውን ኖኅን አድኖ በኀጢአተኞች ዓለም ላይ የጥፋትን ውሃ ካወረደ፥


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios