Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 47:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 እስ​ራ​ኤ​ልም በግ​ብፅ ምድር በጌ​ሤም ሀገር ተቀ​መጠ፤ እር​ስ​ዋም ርስ​ታ​ቸው ሆነች፤ በዙ፤ እጅ​ግም ተባዙ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን በግብጽ አገር በጌሤም ይኖሩ ነበር፤ በዚያም ሀብት ንብረት ዐፈሩ፤ ቍጥራቸውም እጅግ እየበዛ ይሄድ ጀመር።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 እስራኤልም በግብጽ ምድር በጌሤም አገር ተቀመጠ፥ ገዙአትም፥ ረቡ፥ እጅግም በዙ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እስራኤላውያን በግብጽ አገር ጌሴም በተባለ ምድር ይኖሩ ነበር፤ እዚያም ብዙ ሀብት አገኙ፤ ብዙ ልጆችም ወለዱ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 እስራኤልም በግብፅ ምድር በጌሤም አገር ተቀመጠ ገዙአትም ረቡ እጅግም በዙ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 47:27
19 Referências Cruzadas  

ዘር​ህ​ንም እንደ ባሕር አሸዋ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የባ​ሕር አሸ​ዋን ይቈ​ጥር ዘንድ የሚ​ችል ሰው ቢኖር ዘርህ ደግሞ ይቈ​ጠ​ራል።


እጅ​ግም በጣም አበ​ዛ​ሃ​ለሁ፤ ሕዝ​ብም፥ ነገ​ሥ​ታ​ትም ከአ​ንተ እን​ዲ​ወጡ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።


ዘር​ህ​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ይህ​ች​ንም ምድር ሁሉ ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ፤ የም​ድ​ርም ሕዝ​ቦች ሁሉ በዘ​ርህ ይባ​ረ​ካሉ፤


ዘር​ህም እንደ ባሕር አሸዋ ይሆ​ናል፤ እስከ ባሕ​ርና እስከ አዜብ እስከ መስ​ዕና እስከ ምሥ​ራቅ ይበ​ዛል፤ ይሞ​ላ​ልም፤ የም​ድ​ርም ሕዝ​ቦች ሁሉ በአ​ንተ፥ በዘ​ር​ህም ይባ​ረ​ካሉ።


ከእ​ኛም ጋር ተቀ​መጡ፤ ምድ​ራ​ች​ንም በፊ​ታ​ችሁ ሰፊ ናት፤ ኑሩ​ባት፤ ነግ​ዱም፤ ግዙ​አ​ትም።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “አም​ላ​ክህ እኔ ነኝ፤ ብዛ፤ ተባ​ዛም፤ ሕዝ​ብና የአ​ሕ​ዛብ ማኅ​በር ከአ​ንተ ይሆ​ናል፤ ነገ​ሥ​ታ​ትም ከጕ​ል​በ​ትህ ይወ​ጣሉ።


አለ​ውም፥ “የአ​ባ​ቶ​ችህ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ፤ ወደ ግብፅ መው​ረ​ድን አት​ፍራ፤ በዚያ ትልቅ ሕዝብ አደ​ር​ግ​ሃ​ለ​ሁና።


ዮሴ​ፍም አባ​ቱ​ንና ወን​ድ​ሞ​ቹን አኖረ፤ ፈር​ዖን እን​ዳ​ዘ​ዘ​ላ​ቸ​ውም በግ​ብፅ ምድር በተ​ሻ​ለ​ችው በራ​ምሴ ምድር ርስ​ትን ሰጣ​ቸው።


ከም​ድ​ርም ላይ ውኃዉ ጐድሎ እን​ደ​ሆነ ያይ ዘንድ ቁራ​ውን ላከው፤ እር​ሱም ሄደ፤ ነገር ግን ውኃው ከም​ድር ላይ እስ​ኪ​ደ​ርቅ ድረስ አል​ተ​መ​ለ​ሰም።


ነገር ግን ርግብ እግ​ር​ዋን የም​ታ​ሳ​ር​ፍ​በት ስፍራ አላ​ገ​ኘ​ችም፤ ወደ እር​ሱም ወደ መር​ከብ ተመ​ለ​ሰች፤ ውኃው በም​ድር ላይ ሁሉ ነበ​ረና፤ እጁን ዘረ​ጋና ተቀ​በ​ላት፤ ወደ እር​ሱም ወደ መር​ከብ ውስጥ አገ​ባት።


ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አበ​ዛህ፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወደ ተና​ገ​ር​ህ​ላ​ቸው ምድር አገ​ባ​ሃ​ቸው።


የተ​ወ​ደ​ደ​ች​ው​ንም ምድር ናቁ፥ በቃ​ሉም አል​ታ​መ​ኑም፥


ነገር ግን እን​ዳ​ስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸው መጠን እን​ዲሁ በዙ፤ እጅ​ግም ጸኑ ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ይጸ​የ​ፉ​አ​ቸው ነበር።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በዙ፤ ተባ​ዙም፤ የተ​ጠ​ሉም ሆኑ። እጅ​ግም ጸኑ፤ ምድ​ሪ​ቱም በእ​ነ​ርሱ ሞላች።


ተቤዥቼአቸዋለሁና በፉጨት ጠርቼ እሰበስባቸዋለሁ፣ ቀድሞም በዝተው እንደ ነበሩ ይበዛሉ።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ብ​ር​ሃም የማ​ለ​ለት የተ​ስ​ፋው ዘመን በደ​ረሰ ጊዜ እስ​ራ​ኤል በዙ፤ የግ​ብ​ፅ​ንም ሀገር መሉ።


አባ​ቶ​ችህ ሰባ ነፍስ ሆነው ወደ ግብፅ ወረዱ፤ አሁን ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብዛ​ት​ህን እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አደ​ረገ።


በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዲህ ብለህ ተና​ገር፦ አባቴ ከሶ​ርያ ወጥቶ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በዚ​ያም በቍ​ጥር ጥቂት ሆኖ ኖረ፤ በዚ​ያም ታላ​ቅና የበ​ረታ፥ ብዙም ሕዝብ ሆነ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios