Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 45:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 አሁ​ንም እና​ንተ ወደ​ዚህ የላ​ካ​ች​ሁኝ አይ​ደ​ላ​ች​ሁም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላከኝ እንጂ፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም እንደ አባት አደ​ረ​ገኝ፤ በቤ​ቱም ሁሉ ላይ ጌታ፥ በግ​ብፅ ምድ​ርም ሁሉ ላይ አለቃ አደ​ረ​ገኝ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “ስለዚህ አሁን ወደዚህ የላከኝ እግዚአብሔር እንጂ እናንተ አይደላችሁም፤ እርሱም ለፈርዖን እንደ አባት፣ በቤት ንብረቱ ላይ ጌታ፣ እንዲሁም በግብጽ ምድር ላይ ገዥ አደረገኝ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አሁንም እናንተ ወደዚህ የላካችሁኝ አይደላችሁም፥ እግዚአብሔር ላከኝ እንጂ፥ ለፈርዖንም እንደ አባት አደረገኝ፥ በቤቱምም ሁሉ ላይ ጌታ፥ በግብጽ ምድርም ሁሉ ላይ አለቃ አደረገኝ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 “ስለዚህ ወደዚህ የላከኝ ራሱ እግዚአብሔር እንጂ እናንተ አይደላችሁም፤ እግዚአብሔር ለፈርዖን እንደ መካሪ አባት፥ በቤት ንብረቱ ላይ ጌታና የመላው ግብጽ አገር ገዢ አደረገኝ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 አሁንም እናንተ ወደዚህ የላካችሁኝ አይደላችሁም እግዚአብሔር ላከኝ እንጂ ለፈርዖንም እንደ አባት አደረገኝ በቤቱምም ሁሉ ላይ ጌታ በግብፅ ምድርም ሁሉ ላይ አለቃ አደረገኝ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 45:8
11 Referências Cruzadas  

እን​ዲ​ህም ብለው ነገ​ሩት፥ “ልጅህ ዮሴፍ በሕ​ይ​ወቱ ነው፤ እር​ሱም በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ላይ ገዥ ሆኖ​አል።” ያዕ​ቆ​ብም ልቡ ደነ​ገጠ፤ አላ​መ​ና​ቸ​ው​ምም፤


አሁ​ንም ወደ​ዚህ ስለ​ሸ​ጣ​ች​ሁኝ አት​ፍሩ፤ አት​ቈ​ር​ቈ​ሩም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ይ​ወት ከእ​ና​ንተ በፊት ልኮ​ኛ​ልና።


ለድ​ሃ​ዎች አባት ነበ​ርሁ፥ የማ​ላ​ው​ቀ​ው​ንም ሰው ክር​ክር መረ​መ​ርሁ።


መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ህ​ንም አለ​ብ​ሰ​ዋ​ለሁ፤ አክ​ሊ​ል​ህ​ንም እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ ሹመ​ት​ህ​ንም በእጁ አሳ​ልፌ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ለሚ​ኖ​ሩና በይ​ሁ​ዳም ለሚ​ኖሩ አባት ይሆ​ናል።


እኔ መረ​ጥ​ኋ​ችሁ እንጂ እና​ንተ የመ​ረ​ጣ​ች​ሁኝ አይ​ደ​ለም፤ እን​ድ​ት​ሄዱ፥ ፍሬም እን​ድ​ታ​ፈሩ፥ ፍሬ​አ​ች​ሁም እን​ዲ​ኖር፤ አብ​ንም በስሜ የም​ት​ለ​ም​ኑት ነገር ቢኖር ሁሉን እን​ዲ​ሰ​ጣ​ችሁ ሾም​ኋ​ችሁ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ከሰ​ማይ ካል​ተ​ሰ​ጠህ በቀር በእኔ ላይ አን​ዳች ሥል​ጣን የለ​ህም፤ ስለ​ዚህ ለአ​ንተ አሳ​ልፎ የሰ​ጠኝ ሰው ታላቅ ኀጢ​ኣት አለ​በት” አለው።


አሁ​ንም ለሮ​ጠና ለቀ​ደመ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ላለው ነው እንጂ።


ተቀብለህ ለዘላለም እንድትይዘው ስለዚህ ምናልባት ለጊዜው ተለይቶሃልና፤


ሚካም፥ “በእኔ ዘንድ ተቀ​መጥ፤ አባ​ትና ካህ​ንም ሁነኝ፤ እኔም ልብ​ሶ​ች​ንና ምግ​ብ​ህን፥ በየ​ዓ​መ​ቱም ዐሥር ብር እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” አለው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios