Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 44:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እኛም ለጌ​ታዬ እን​ዲህ አልን፦ ሽማ​ግሌ አባት አለን፤ በሽ​ም​ግ​ል​ናው የወ​ለ​ደ​ውም ታናሽ ብላ​ቴና አለ፤ ወን​ድሙ ግን ሞተ፤ ለእ​ና​ቱም እርሱ ብቻ​ውን ቀረ፤ አባ​ቱም ይወ​ድ​ደ​ዋል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እኛም፣ ‘አዎን፣ ሽማግሌ አባት አለን፤ አባታችንም በስተርጅና የወለደው ትንሽ ልጅ አለው፤ ወንድምየው ሞቷል፤ ከአንድ እናት ከተወለዱት ልጆች መካከል የተረፈው እርሱ ብቻ ነው፤ አባቱም በጣም ይወድደዋል’ ብለንህ ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እኛም፥ ‘አዎን፥ ሽማግሌ አባት አለን፤ አባታችንም በስተርጅና የወለደው ትንሽ ልጅ አለው፤ ወንድምየው ሞቷል፤ ከአንድ እናት ከተወለዱት ልጆች መካከል የተረፈው እርሱ ብቻ ነው፤ አባቱም በጣም ይወደዋል’ ብለንህ ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እኛም ‘ሽማግሌ አባት አለን፤ በስተርጅና የወለደውም ታናሽ ወንድም አለን፤ የልጁ ወንድም ሞቶአል፤ ከእናቱ ልጆች የቀረው እርሱ ብቻ ስለ ሆነ አባቱ በጣም ይወደዋል’ ብለንህ ነበር፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እኛም ለጌታዬ እንዲህ አልነ፦ ሸማግሌ አባት አለን በሽምግልናው የወለደውም ታናሽ ብላቴና አለ ወንድሙም ሞተ ከእናቱም እርሱ ብቻውን ቀረ አባቱም ይወድደዋል።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 44:20
12 Referências Cruzadas  

ከዚ​ያም በኋላ ነፍ​ስዋ ልት​ወጣ ደረ​ሰች፤ ሞትዋ በእ​ርሱ ሆኖ​አ​ልና ስሙን የጭ​ን​ቀቴ ልጅ ብላ ጠራ​ችው ፤ አባቱ ግን ብን​ያም አለው።


አን​ዱም ለአ​ንዱ እን​ዲህ አለው፥ “ያ ባለ ሕልም ይኸው መጣ።


ያዕ​ቆ​ብም ዮሴ​ፍን ከል​ጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወ​ድ​ደው ነበር፤ እርሱ በሽ​ም​ግ​ል​ናው የወ​ለ​ደው ነበ​ርና። በብዙ ኅብር ያጌ​ጠ​ችም ቀሚስ አደ​ረ​ገ​ለት።


እነ​ር​ሱም አሉ፥ “ባሪ​ያ​ዎ​ችህ በከ​ነ​ዓን ምድር የም​ን​ኖር ዐሥራ ሁለት ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች ነን፤ ታና​ሹም እነሆ ዛሬ ከአ​ባ​ታ​ችን ጋር ነው፤ ሌላ​ውም ሞቶ​አል።”


አባ​ታ​ቸው ያዕ​ቆ​ብም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ልጅ አልባ አስ​ቀ​ራ​ች​ሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስም​ዖ​ንም የለም፤ ብን​ያ​ም​ንም ትወ​ስ​ዱ​ብ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ይህ ሁሉ በእኔ ላይ ደረሰ።”


እር​ሱም አለ፥ “ልጄ ከእ​ና​ንተ ጋር አይ​ወ​ር​ድም፤ ወን​ድሙ ሞቶ እርሱ ብቻ ቀር​ቶ​አ​ልና፤ በም​ት​ሄ​ዱ​በት መን​ገድ ምና​ል​ባት ክፉ ነገር ቢያ​ገ​ኘው ሽም​ግ​ል​ና​ዬን በኀ​ዘን ወደ መቃ​ብር ታወ​ር​ዱ​ታ​ላ​ችሁ።”


የብ​ን​ያ​ምም ልጆች፤ ቤላ፥ ቦኮር፥ አስ​ቤር፤ የቤላ ልጆ​ችም፤ ጌራ፥ ኖሔ​ማን፥ አሒ፥ ሮስ፥ ማን​ፌን፥ ሑፈም፤ ጌራም አራ​ድን ወለደ።


“ይሁዳ፥ ወን​ድ​ሞ​ችህ አን​ተን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፤ እጅህ በጠ​ላ​ቶ​ችህ ደን​ደስ ላይ ነው፤ የአ​ባ​ትህ ልጆች በፊ​ትህ ይሰ​ግ​ዳሉ።


ወደ ከተ​ማው በር በደ​ረሰ ጊዜም እነሆ፥ ያን​ዲት መበ​ለት ሴት ልጅ ሙቶ ሬሳ​ውን ተሸ​ክ​መው ሲሄዱ አገኘ፤ ይኸ​ውም ለእ​ናቱ አንድ ነበረ፤ ብዙ​ዎ​ችም የከ​ተማ ሰዎች አብ​ረ​ዋት ነበሩ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios