Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 37:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 እር​ሱም ዐውቆ፥ “የልጄ ቀሚስ ነው፤ ክፉ አውሬ በል​ቶ​ታል፤ ዮሴ​ፍን ቦጫ​ጭ​ቆ​ታል” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 እርሱም ልብሱን ዐውቆት፣ “ይህማ የልጄ እጀ ጠባብ ነው! ክፉ አውሬ በልቶታል፤ በርግጥም ዮሴፍ ተቦጫጭቋል” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 እርሱም ለይቶ ስላወቀው፦ “የልጄ ቀሚስ ነው፤ ክፉ አውሬ በልቶታል፤ ዮሴፍ በእርግጥ ተበጫጭቋል” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 እርሱም የልጁ ልብስ መሆኑን ተረድቶ “በእርግጥ የእርሱ ልብስ ነው! አንድ ክፉ አውሬ ገድሎታል፤ ልጄን ዮሴፍን አውሬ ቦጫጭቆ በልቶታል!” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 እርሱም አውቆ፦ የልጄ ቀሚስ ነውም ክፋ አውሬ በልቶታል ዮሴፍ በእርግጥ ተበጫጭቋል አለ

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 37:33
10 Referências Cruzadas  

ኑ፥ እን​ግ​ደ​ለ​ውና በአ​ንድ ጕድ​ጓድ ውስጥ እን​ጣ​ለው፤ ክፉ አው​ሬም በላው እን​ላ​ለን፤ ሕል​ሞ​ቹም ምን እን​ደ​ሚ​ሆኑ እና​ያ​ለን።”


ብዙ ኅብር ያለ​በ​ትን ቀሚ​ሱ​ንም ላኩ፤ ወደ አባ​ታ​ቸ​ውም አገ​ቡት፤ እን​ዲ​ህም አሉት፥ “ይህን ልብስ አገ​ኘን፤ ይህ የል​ጅህ ልብስ እንደ ሆነ ወይም እን​ዳ​ል​ሆነ እስኪ እየው?”


እር​ሱም አለ፥ “ልጄ ከእ​ና​ንተ ጋር አይ​ወ​ር​ድም፤ ወን​ድሙ ሞቶ እርሱ ብቻ ቀር​ቶ​አ​ልና፤ በም​ት​ሄ​ዱ​በት መን​ገድ ምና​ል​ባት ክፉ ነገር ቢያ​ገ​ኘው ሽም​ግ​ል​ና​ዬን በኀ​ዘን ወደ መቃ​ብር ታወ​ር​ዱ​ታ​ላ​ችሁ።”


እኛም ለጌ​ታዬ እን​ዲህ አልን፦ ሽማ​ግሌ አባት አለን፤ በሽ​ም​ግ​ል​ናው የወ​ለ​ደ​ውም ታናሽ ብላ​ቴና አለ፤ ወን​ድሙ ግን ሞተ፤ ለእ​ና​ቱም እርሱ ብቻ​ውን ቀረ፤ አባ​ቱም ይወ​ድ​ደ​ዋል።


አን​ዱም ከእኔ ወጣ፤ አውሬ በላው አላ​ች​ሁኝ፤ እስከ ዛሬም ገና አላ​የ​ሁ​ትም፤


እስ​ራ​ኤ​ልም ዮሴ​ፍን፥ “ከፊ​ትህ አል​ተ​ለ​የ​ሁም፤ እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘር​ህን ደግሞ አሳ​የኝ” አለው።


ተነ​ሥ​ቶም ሄደ፤ በመ​ን​ገ​ዱም ላይ አን​በሳ አግ​ኝቶ ገደ​ለው፤ ሬሳ​ውም በመ​ን​ገድ ላይ ተጋ​ድሞ ነበር፤ አህ​ያ​ውም በእ​ርሱ አጠ​ገብ ቆሞ ነበር፤ አን​በ​ሳ​ውም ደግሞ በሬ​ሳው አጠ​ገብ ቆሞ ነበር።


ዘወ​ርም ብሎ አያ​ቸው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም ረገ​ማ​ቸው፤ ወዲ​ያ​ውም ከዱር ሁለት ድቦች ወጥ​ተው ከእ​ነ​ርሱ አርባ ሁለ​ቱን ሰባ​በ​ሩ​አ​ቸው።


የዋህ ነገርን ሁሉ ያምናል፤ ዐዋቂ ግን ወደ ንስሓ ይመለሳል።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔ የም​ሠ​ራ​ውን አንተ ዛሬ አታ​ው​ቅም፤ ኋላ ግን ታስ​ተ​ው​ለ​ዋ​ለህ” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios