Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 34:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 የያ​ዕ​ቆብ ልጆ​ችም ወደ ሞቱት ገብ​ተው እኅ​ታ​ቸው ዲናን ያስ​ነ​ወ​ሩ​ባ​ትን ከተ​ማ​ዪ​ቱን ዘረፉ፤

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 የያዕቆብ ልጆች ሁሉ በሬሳ ላይ እየተረማመዱ እኅታቸው የተደፈረችበትን ከተማ ዘረፉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 የያዕቆብም ልጆች እኅታቸውን ዲናን ሰለ አረከሱአት ወደ ሞቱት ገብተው ከተማይቱን ዘረፉ፥

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 የቀሩትም የያዕቆብ ልጆች ወደሞቱት ሰዎች ቤት እየገቡ እኅታቸው የተደፈረችበትን ከተማ በሙሉ ዘረፉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 የያዕቆብም ልጆች እኅታቸውን ዲናን ሰለ አረከሱአት ወደ ሞቱት ገብተው ከተማይቱን ዘረፉ፤

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 34:27
13 Referências Cruzadas  

የሀ​ገሩ አለቃ የኤ​ዊ​ያ​ዊው ሰው የኤ​ሞር ልጅ ሴኬም አያት፤ ወሰ​ዳ​ትም፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ተኛ፤ አስ​ነ​ወ​ራ​ትም።


ኤሞ​ር​ንና ልጁን ሴኬ​ም​ንም በሰ​ይፍ ገደሉ፤ እኅ​ታ​ቸው ዲና​ንም ከሴ​ኬም ቤት ይዘው ወጡ።


ላሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ በጎ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ አህ​ዮ​ቻ​ቸ​ው​ንም በሜ​ዳም፥ በከ​ተ​ማም ያለ​ውን ወሰዱ ።


እነ​ር​ሱም፥ “እኅ​ታ​ች​ንን እንደ አመ​ን​ዝራ አድ​ር​ገው ለምን አዋ​ረ​ዷት?” አሉት።


ወን​ድ​ሙን የሚ​በ​ድ​ለው ያም ሰው፥ “በእኛ ላይ አን​ተን አለቃ ወይስ ዳኛ ማን አደ​ረ​ገህ? ወይስ ግብ​ፃ​ዊ​ውን ትና​ንት እንደ ገደ​ል​ኸው ልት​ገ​ድ​ለኝ ትሻ​ለ​ህን?” አለው። ሙሴም፥ “በእ​ው​ነት ይህ ነገር ታው​ቆ​አ​ልን?” ብሎ ፈራ።


እን​ጨ​ትን ከሜዳ አይ​ወ​ስ​ዱም፤ ከዱ​ርም አይ​ቈ​ር​ጡም፤ ነገር ግን የጦር መሣ​ሪ​ያን በእ​ሳት ያነ​ድ​ዳሉ፤ የገ​ፈ​ፉ​አ​ቸ​ው​ንም ይገ​ፍ​ፋሉ፤ የበ​ዘ​በ​ዙ​አ​ቸ​ው​ንም ይበ​ዘ​ብ​ዛሉ፤ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እስከ ጢሮስ በአ​ለው ዙሪ​ያሽ ድረስ ምድ​ርሽ ይጠ​ፋል፥ ብር​ታ​ት​ሽ​ንም ከአ​ንቺ ያወ​ር​ዳል፤ ሀገ​ሮ​ች​ሽም ይበ​ዘ​በ​ዛሉ።”


ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፤ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን እርም በሆ​ነው ነገር ታላቅ በደል በደሉ፤ ከይ​ሁዳ ነገድ የሆነ አካን፥ እር​ሱም የከ​ርሚ ልጅ፥ የዘ​ን​በሪ ልጅ፥ የዛራ ልጅ እርም ከሆ​ነው ነገር ወሰደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ተቈጣ።


ተነ​ሣና ሕዝ​ቡን ቀድስ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ‘እስ​ራ​ኤል ሆይ! እርም የሆነ ነገር በመ​ካ​ከ​ልህ አለ፤ እር​ምም የሆ​ነ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እስ​ክ​ታ​ጠፉ ድረስ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ፊት መቆም አት​ች​ሉም’ ብሎ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሮ​አ​ልና እስከ ነገ ራሳ​ች​ሁን አንጹ።


በዘ​ረፋ መካ​ከል አንድ ያማረ ካባ፥ ሁለት መቶ ሰቅል ብር፥ ሚዛ​ኑም አምሳ ሰቅል የሆነ ወርቅ አይቼ ተመ​ኘ​ኋ​ቸው፤ ወሰ​ድ​ኋ​ቸ​ውም፤ እነ​ሆም በድ​ን​ኳኔ ውስጥ በመ​ሬት ተሸ​ሽ​ገ​ዋል፤ ብሩም ከሁሉ በታች ነው” አለው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios