Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 34:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 “እነ​ዚህ ሰዎች በእኛ ዘንድ የሰ​ላም ሰዎች ናቸው፤ በም​ድ​ራ​ችን ይቀ​መጡ፤ ይነ​ግ​ዱ​ባ​ትም፤ እነ​ሆም፥ ምድ​ሪቱ ሰፊ ናት፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለሚ​ስ​ት​ነት እን​ው​ሰድ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ንን እን​ስጥ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እንዲህም አሏቸው፤ “እነዚህ ሰዎች ወዳጆቻችን ናቸው፤ በአገራችን እንዲኖሩ፣ ተዘዋውረውም እንዲነግዱ እንፍቀድላቸው፤ ምድሪቱ እንደሆን ለእኛም ለእነርሱም ትበቃለች። ሴቶች ልጆቻቸውን እናገባለን፤ እነርሱም የእኛን ሴቶች ያገባሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 “እነዚህ ሰዎች በእኛ ዘንድ የሰላም ሰዎች ናቸው፥ በምድራችን ይቀመጡ፥ ይነግዱባትም፥ እነሆም ምድሪቱ ሰፊ ናት፥ ሴቶች ልጆቻቸውን እንውሰድ፥ ለእነርሱም ሴቶች ልጆቻችንን እንስጥ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “እነዚህ ሰዎች ከእኛ ጋር የሚኖሩት በሰላም ነው፤ በምድሪቱ ላይ አብረውን ይቀመጡ፤ በነጻም ይዘዋወሩባት፤ እነሆ፥ ምድሪቱ ለእኛም ለእነርሱም ትበቃናለች፤ የእነርሱን ሴቶች ልጆች እናግባ፤ የእኛንም ሴቶች ልጆች እንዳርላቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ነገሩ፦ እነዚህ ሰዎች በእኛ ዘንድ የሰላም ሰዎች ናቸው በምድራችን ይቀመጡ ይነግዱባትም እነሆም ምድሪቱ ሰፊ ናት ሴቶች ልጆቻቸውን እንውሰድ ለእነርሱም ሴቶች ልጆቻቸንን እንስጥ

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 34:21
4 Referências Cruzadas  

ከእ​ኛም ጋር ተቀ​መጡ፤ ምድ​ራ​ች​ንም በፊ​ታ​ችሁ ሰፊ ናት፤ ኑሩ​ባት፤ ነግ​ዱም፤ ግዙ​አ​ትም።”


ኤሞ​ርና ልጁ ሴኬ​ምም ሄዱና ወደ ከተ​ማ​ቸው በር ደረሱ፤ ለከ​ተ​ማ​ቸ​ውም ሰዎች ሁሉ እን​ዲህ ብለው ነገሩ፦


እነ​ርሱ እንደ እኛ ይሆኑ ዘንድ በዚህ ብቻ እን​ም​ሰ​ላ​ቸው። አንድ ወገ​ንም እን​ሁን፤ እነ​ርሱ እን​ደ​ሚ​ገ​ርዙ ወን​ዶ​ቻ​ች​ንን ሁሉ እን​ገ​ር​ዛ​ለን።


ታና​ሹ​ንም ወን​ድ​ማ​ች​ሁን አም​ጡ​ልኝ፤ ሰላ​ማ​ው​ያን እንጂ ሰላ​ዮች አለ​መ​ሆ​ና​ች​ሁ​ንም በዚህ ዐው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ወን​ድ​ማ​ች​ሁ​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም በሀ​ገ​ራ​ችን ትነ​ግ​ዳ​ላ​ችሁ።’ ”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios