Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 34:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ብዙ ማጫ አምጣ በሉኝ፤ በም​ት​ጠ​ይ​ቁ​ኝም መጠን እሰ​ጣ​ለሁ፤ ይህ​ችን ብላ​ቴና ግን ሚስት ትሆ​ነኝ ዘንድ ስጡኝ።”

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ጥሎሽ ብትሉኝ ጥሎሽ፣ ስጦታ ብትሉም የፈለጋችሁትን ያህል እሰጣለሁ፤ ብቻ ልጅቱን እንዳገባ ፍቀዱልኝ።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ብዙ ጥሎሽና ስጦታ አምጣ በሉኝ፥ ይህችን ልጅ እንዳገባ ስጡኝ እንጂ፥ በነገራችሁኝም መጠን እሰጣለሁ።”

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ለሙሽራዋም ጥሎሽ የፈለጋችሁትን ያኽል ጠይቁኝ፤ እርስዋን እንዳገባ ፍቀዱልኝ እንጂ፥ የፈለጋችሁትን ሁሉ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ብዙ ማጫን እጅ መንሻ አምጣ በሉኝ በነገራችሁኝም መጠን እሰጣለሁ ይህችን ብላቴና ግን አጋቡኝ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 34:12
13 Referências Cruzadas  

ሎሌ​ውም የብ​ርና የወ​ርቅ ጌጥ፥ ልብ​ስም አወጣ፤ ለር​ብ​ቃም ሰጣት፤ ዳግ​መ​ኛም ለአ​ባ​ቷና ለእ​ናቷ እጅ መንሻ ሰጣ​ቸው።


ያዕ​ቆ​ብም ራሔ​ልን ወደ​ዳት፤ ያዕ​ቆ​ብም ላባን እን​ዲህ አለው፥ “ስለ ታና​ሺቱ ልጅህ ስለ ራሔል ሰባት ዓመት እገ​ዛ​ል​ሃ​ለሁ። ሚስት ትሆ​ነኝ ዘንድ እር​ስ​ዋን ስጠኝ” አለው።


ለአ​ንተ ቤት የተ​ገ​ዛ​ሁ​ልህ ዛሬ ሃያ አንድ ዓመት ነው፤ ዐሥራ አራት ዓመት ስለ ሁለቱ ሴቶች ልጆ​ችህ፥ ሰባት ዓመት ስለ በጎ​ችህ ተገ​ዛ​ሁ​ልህ፤ ደመ​ወ​ዜ​ንም ዐሥር ጊዜ ለዋ​ወ​ጥ​ኸው።


ሴኬ​ምም አባ​ቷ​ንና ወን​ድ​ሞ​ች​ዋን እን​ዲህ አለ፥ “በፊ​ታ​ችሁ ሞገ​ስን በአ​ገኝ የም​ት​ሉ​ትን ሁሉ እሰ​ጣ​ለሁ።


የያ​ዕ​ቆ​ብም ልጆች ለሴ​ኬ​ምና ለአ​ባቱ ለኤ​ሞር በተ​ን​ኰል መለሱ፤ እኅ​ታ​ቸ​ውን ዲናን አስ​ነ​ው​ሮ​አ​ታ​ልና፤


ዳዊ​ትም ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያ​ቡ​ስቴ፥ “በመቶ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሸለ​ፈት ያጨ​ኋ​ትን ሚስ​ቴን ሜል​ኮ​ልን መል​ስ​ልኝ” ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ።


ባለ​ቤቱ ግን ከእ​ርሱ ጋር ቢኖር አይ​ክ​ፈል፤ ቢከ​ራ​የ​ውም ኪራ​ዩን ይክ​ፈል።


እኔም በዐ​ሥራ አም​ስት ብርና በአ​ንድ ቆሮስ መስ​ፈ​ሪያ ተኩል ገብ​ስና በአ​ንድ ፊቀን ወይን ተወ​ዳ​ጀ​ኋት።


እነርሱም “ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ በቀር በዚህ የለንም፤” አሉት።


የሳ​ኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖች ይህን ቃል በዳ​ዊት ጆሮ ተና​ገሩ፤ ዳዊ​ትም፥ “እኔ የተ​ዋ​ረ​ድ​ሁና ክብር የሌ​ለኝ ሰው ስሆን ለን​ጉሥ አማች እሆን ዘንድ ለእ​ና​ንተ ትንሽ ነገር ይመ​ስ​ላ​ች​ኋ​ልን?” አለ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios