Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 31:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ላባም ወደ ያዕ​ቆብ ድን​ኳ​ንና ወደ ልያም ድን​ኳን ገባና በረ​በረ፤ አላ​ገ​ኘ​ምም፤ ከዚ​ያም ወጣና ወደ ሁለቱ ዕቁ​ባ​ቶቹ ድን​ኳን ገባ፤ ነገር ግን አላ​ገ​ኘም። ወደ ራሔ​ልም ድን​ኳን ገባ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ላባም ወደ ያዕቆብ፣ ድንኳንና ወደ ልያ ድንኳን እንዲሁም ወደ ሁለቱ ደንገጥሮቿ ድንኳኖች ገባ፤ ነገር ግን ምንም አላገኘም። ከልያ ድንኳን ከወጣ በኋላ ወደ ራሔል ድንኳን ገባ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ላባም ወደ ያዕቆብ ድንኳንና ወደ ልያ ድንኳን ወደ ሁለቱም ባርያዎች ድንኳን ገባ፥ ነገር ግን አላገኘም። ከልያም ድንኳን ወጥቶ ወደ ራሔል ድንኳን ገባ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ከዚህ በኋላ ላባ ወደ ያዕቆብ ወደ ልያና ወደ ሁለቱ አገልጋዮች ድንኳን ተራ በተራ ገብቶ በረበረ፤ ነገር ግን ምንም አላገኘም፤ በመጨረሻ ወደ ራሔል ድንኳን ገባ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ላባም ወደ ያዕቆብ ድንኳንና ወደ ልያ ድንኳን ወደ ሁለቱም ባሪይዎች ድንኳን ገባ ነገር ግን አላገኘም።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 31:33
4 Referências Cruzadas  

ብላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም ሮጠች፥ ለእ​ና​ቷም ቤት ይህን ሁሉ ነገር ተና​ገ​ረች።


ይስ​ሐ​ቅም ወደ እናቱ ቤት ገባ፤ ርብ​ቃ​ንም ወሰ​ዳት፤ ሚስ​ትም ሆነ​ችው፤ ወደ​ዳት፤ ይስ​ሐ​ቅም ስለ እናቱ ስለ ሣራ ተጽ​ናና።


ያዕ​ቆ​ብም አለ፥ “አም​ላ​ኮ​ች​ህን የም​ታ​ገ​ኝ​በት ሰው ግን እርሱ ይሙት፤ ገን​ዘ​ብ​ህም በእኔ ዘንድ ካለ በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ፊት እይ፤ ለአ​ን​ተም ውሰ​ደው” አለ። ያዕ​ቆብ ሚስቱ ራሔል እንደ ሰረ​ቀ​ቻ​ቸው አያ​ው​ቅም ነበ​ርና።


ራሔ​ልም የአ​ባ​ቷን ጣዖ​ቶች ወስዳ ከግ​መል ኮርቻ በታች ሸሸ​ገች፤ በላ​ዩም ተቀ​መ​ጠ​ች​በት። ላባም ድን​ኳ​ኑን ሁሉ ፈለገ፤ አን​ዳ​ችም አላ​ገ​ኘም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios