Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 26:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ስም​ዋ​ንም “መሐላ” ብሎ ጠራት፤ ስለ​ዚ​ህም የከ​ተ​ማ​ዪቱ ስም እስከ ዛሬ ድረስ “ዐዘ​ቅተ መሐላ” ይባ​ላል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 እርሱም የውሃውን ጕድጓድ ሳቤህ አለው፤ ከዚያም የተነሣ የከተማዪቱ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ቤርሳቤህ ተብሎ ይጠራል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ስምዋንም “ሳቤህ” ብሎ ጠራት፥ ስለዚህም የከተማይቱ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ቤርሳቤህ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 እርሱም የውሃውን ጒድጓድ “ሳቤህ” ብሎ ጠራው፤ ስለዚህም የከተማይቱ ስም እስከ ዛሬ “ቤርሳቤህ” እየተባለ ይጠራል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ስምዋንም ሳቤህ ብሎ ጠራት ስለዚህም የከተማይቱ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ቤርሳቤህ ነው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 26:33
6 Referências Cruzadas  

አብ​ር​ሃ​ምም ማልዶ ተነሣ፤ እን​ጀ​ራ​ንም ወሰደ፤ የውኃ አቍ​ማ​ዳ​ንም ለአ​ጋር በት​ከ​ሻዋ አሸ​ከ​ማት፤ ሕፃ​ኑ​ንም ሰጥቶ አስ​ወ​ጣት፤ እር​ስ​ዋም ሄደች፤ በዐ​ዘ​ቅተ መሐ​ላም በኩል ባለው ምድረ በዳ ተቅ​በ​ዘ​በ​ዘች።


ስለ​ዚ​ህም ያን ጕድ​ጓድ ዐዘ​ቅተ መሐላ ብሎ ጠራው፤ በዚያ እርስ በር​ሳ​ቸው ተማ​ም​ለ​ዋ​ልና።


እነ​ር​ሱም አሉት፥ “እኛ የጠ​ላ​ንህ አይ​ደ​ለም፤ በመ​ል​ካም አኑ​ረን፥ በመ​ል​ካም አሰ​ና​በ​ት​ንህ እንጂ፥ አሁ​ንም አንተ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ ነህ።


በዚ​ያም ቀን የይ​ስ​ሐቅ ሎሌ​ዎች መጡ፤ ስለ ቈፈ​ሩ​አ​ትም ጕድ​ጓድ፥ ውኃ አገ​ኘን ብለው ነገ​ሩት።


በሐ​ጸ​ር​ሱ​ዓል፥ በቤ​ር​ሳ​ቤ​ህና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ፥


ነገር ግን ጌል​ገላ ፈጽሞ ትማ​ረ​ካ​ለ​ችና፥ ቤቴ​ልም እን​ዳ​ል​ነ​በ​ረች ትሆ​ና​ለ​ችና ቤቴ​ልን አት​ፈ​ልጉ፤ ወደ ጌል​ገ​ላም አት​ሂዱ፤ ወደ ቤር​ሳ​ቤ​ህም አት​ለፉ።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios