Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 26:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ይስ​ሐ​ቅም ከዚያ ሄደ በዚ​ያም ሌላ ጕድ​ጓድ ማሰ፥ ስለ እር​ስ​ዋም ደግሞ ተጣ​ሉት፤ ስም​ዋ​ንም “ጽልእ” ብሎ ጠራት።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 አሁንም እንደ ገና ሌላ የውሃ ጕድጓድ ቈፈሩ፤ አሁንም ሌላ ግጭት ተፈጠረ፤ ስለዚህ የውሃ ጕድጓዱን ስጥና ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ሌላ ጉድጓድም ማሱ፥ ስለ እርሷም ደግሞ ተጣሉ፥ ስምዋንም “ስጥና” ብሎ ጠራት።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 የይስሐቅ አገልጋዮች ሌላ የውሃ ጒድጓድ ቈፈሩ፤ በዚህኛውም ጒድጓድ ምክንያት ሌላ ጠብ ተነሣ፤ ስለዚህ ይስሐቅ ይህን ጒድጓድ “ስጥና” ብሎ ሰየመው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ሌላ ጕድጓድም ማሱ ስለ እርስዋም ደግሞ ተጣሉ፤ ስምዋንም ስጥና ብሎ ጠራት።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 26:21
4 Referências Cruzadas  

አብ​ር​ሃ​ምም አቤ​ሜ​ሌ​ክን ብላ​ቴ​ኖቹ በቀ​ሙት በውኃ ጕድ​ጓድ ምክ​ን​ያት ወቀ​ሰው።


የጌ​ራራ እረ​ኞች ከይ​ስ​ሐቅ እረ​ኞች ጋር፥ “ውኃው የእኛ ነው” ሲሉ ተጣሉ፤ የዚ​ያ​ች​ንም ጕድ​ጓድ ስም “ዐዘ​ቅተ ዐመፃ” ብሎ ጠራት፤ እነ​ርሱ በድ​ለ​ው​ታ​ልና።


ከዚ​ያም እልፍ ብሎ ሌላ ጕድ​ጓድ ቈፈረ፤ ስለ እር​ስ​ዋም አል​ተ​ጣ​ሉ​ትም፤ ስም​ዋ​ንም “መር​ኅብ” ብሎ ጠራት፤ እን​ዲህ ሲል፥ “አሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሰ​ፋ​ልን፤ በም​ድ​ርም አበ​ዛን።”


በአ​ሕ​ሳ​ዊ​ሮ​ስም መን​ግ​ሥት፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ቱም በመ​ጀ​መ​ሪያ ዘመን፥ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሚ​ኖ​ሩት ላይ ደብ​ዳቤ ጻፉ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios