Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 25:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 አብ​ር​ሃ​ምም ለቁ​ባ​ቶቹ ልጆች ሀብ​ትን ሰጣ​ቸው፤ እር​ሱም ገና በሕ​ይ​ወቱ ሳለ ከልጁ ከይ​ስ​ሐቅ ለይቶ ወደ ምሥ​ራቅ ሀገር ሰደ​ዳ​ቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ለቁባቶቹ ልጆች ግን በሕይወት እያለ ስጦታ አደረገላቸው፤ ከልጁ ከይሥሐቅም ርቀው እንዲኖሩ ወደ ምሥራቅ ምድር ሰደዳቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ነገር ግን የአብርሃም ለነበሩትም ለቁባቶቹ ልጆች አብርሃም ስጦታ ሰጣቸው፥ እርሱም ገና በሕይወቱ ሳለ ከልጁ ከይስሐቅ ለይቶ ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ አገር ሰደዳቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከሌሎች ሴቶች ለተወለዱትም ልጆች ገና በሕይወት ሳለ ስጦታ ሰጣቸው፤ ከዚህ በኋላ እነዚህ ሌሎች ልጆች ከይስሐቅ ርቀው ወደ ምሥራቅ አገር እንዲሄዱ አደረጋቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የአብርሃም ለነበሩ ለቁብቶቹ ልጆች አብርሃም ስጦታን ሰጣቸው እርሱም ገና በሕይወቱ ሳለ ከልጁ ከይስሕቅ ለይቶ ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ አገር ሰደዳቸው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 25:6
18 Referências Cruzadas  

አብ​ራ​ምም በከ​ነ​ዓን ምድር ዐሥር ዓመት ከተ​ቀ​መጠ በኋላ፥ የአ​ብ​ራም ሚስት ሦራ ግብ​ፃ​ዊት አገ​ል​ጋ​ይ​ዋን አጋ​ርን ወስዳ ለአ​ብ​ራም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ሰጠ​ችው።


አብ​ር​ሃ​ምም ማልዶ ተነሣ፤ እን​ጀ​ራ​ንም ወሰደ፤ የውኃ አቍ​ማ​ዳ​ንም ለአ​ጋር በት​ከ​ሻዋ አሸ​ከ​ማት፤ ሕፃ​ኑ​ንም ሰጥቶ አስ​ወ​ጣት፤ እር​ስ​ዋም ሄደች፤ በዐ​ዘ​ቅተ መሐ​ላም በኩል ባለው ምድረ በዳ ተቅ​በ​ዘ​በ​ዘች።


አብ​ር​ሃ​ምም ደግሞ ስምዋ ኬጡራ የተ​ባ​ለች ሚስት አገባ።


ያዕ​ቆ​ብም በማ​ለዳ ተነ​ሥቶ የያ​ዕ​ቆ​ብና የዔ​ሳው እናት የር​ብቃ ወን​ድም የሶ​ርያ ሰው የባ​ቱ​ኤል ልጅ ወደ​ሚ​ሆን ወደ ላባ ሄደ።


አገ​ል​ጋ​ይ​ዋን ባላ​ንም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ለእ​ርሱ ሰጠ​ችው፤ ያዕ​ቆ​ብም ወደ እር​ስዋ ገባ።


ልያም መው​ለ​ድን እን​ዳ​ቆ​መች በአ​የች ጊዜ አገ​ል​ጋ​ይ​ዋን ዘለ​ፋን ወሰ​ደች፤ ሚስት ትሆ​ነ​ውም ዘንድ ለያ​ዕ​ቆብ ሰጠ​ችው፤ ያዕ​ቆ​ብም ወደ እር​ስዋ ገባ።


በዚ​ያ​ችም ሌሊት ተነሣ፥ ሁለ​ቱን ሚስ​ቶ​ቹ​ንና ሁለ​ቱን ዕቁ​ባ​ቶ​ቹን ዐሥራ አን​ዱ​ንም ልጆ​ቹን ይዞ የያ​ቦ​ቅን ወንዝ ተሻ​ገረ።


የያ​ዕ​ቆ​ብም ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው፤


ሮብ​ዓ​ምም ከሚ​ስ​ቶ​ቹና ከቁ​ባ​ቶቹ ሁሉ ይልቅ የአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምን ልጅ መዓ​ካን ወደደ፤ ዐሥራ ስም​ን​ትም ሚስ​ቶ​ችና ስድሳ ቁባ​ቶች ነበ​ሩት፤ ሃያ ስም​ንት ወን​ዶ​ችና ስድሳ ሴቶች ልጆ​ች​ንም ወለደ።


አው​ስ​ጢድ በሚ​ባል ሀገር ስሙ ኢዮብ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ቅን፥ ንጹ​ሕና ጻድቅ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ፈራ፥ ከክፉ ሥራም ሁሉ የራቀ ነበር።


ከብ​ቶ​ቹም፦ ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመ​ሎች፥ አም​ስት መቶም ጥማድ በሬ፥ አም​ስት መቶም እን​ስት አህ​ዮች ነበሩ፤ እጅግ ብዙም አገ​ል​ጋ​ዮች ነበ​ሩት፤ ሥራ​ውም በም​ድር ላይ ታላቅ ነበረ፤ ያም ሰው በም​ሥ​ራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ገናና ነበረ።


ከዚ​ህም ሁሉ ጋር መል​ካም ሥራን እየ​ሠራ ከሰ​ማይ ዝና​ምን፥ ፍሬ የሚ​ሆ​ን​በ​ት​ንም ወራት ሲሰ​ጠን፥ ልባ​ች​ን​ንም በመ​ብ​ልና በደ​ስታ ሲሞ​ላው ራሱን ያለ ምስ​ክር አል​ተ​ወም።”


የብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም አባት አማቱ ወደ ቤቱ አገ​ባው፤ በቤ​ቱም ሦስት ቀን ተቀ​መጠ፤ በሉም፤ ጠጡም፤ በዚ​ያም አደሩ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ዘር በዘሩ ጊዜ ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንና አማ​ሌ​ቃ​ው​ያን ይዘ​ም​ቱ​ባ​ቸው ነበር፥ በም​ሥ​ራ​ቅም የሚ​ኖሩ ልጆች አብ​ረው ይዘ​ም​ቱ​ባ​ቸው ነበር፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios