Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 25:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የይ​ስ​ማ​ኤ​ልም የል​ጆቹ ስም በየ​ስ​ማ​ቸ​ውና በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው እን​ዲህ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 የእስማኤል ልጆች ስም እንደ ዕድሜያቸው ቅደም ተከተል እንዲህ ነው፦ የእስማኤል በኵር ልጅ ነባዮት፣ ቄዳር፣ ነብዳኤል፣ መብሳም፣

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በትውልዳቸው ቅደም ተከተል የተዘረዘሩት የእስማኤል የልጆቹ ስም እንዲህ ነው፥ የእስማኤል የበኩር ልጁ ነባዮት፥ እና ቄዳር፥ አድብኤል፥ ሚብሣም፥

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከዚህ በታች በዕድሜአቸው ቅደም ተከተል ተራ የተዘረዘሩትን ልጆች ወለደ፤ እነርሱም፦ ነባዮት፥ ቄዳር፥ አድብኤል፥ ሚብሣም፥

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የእስማኤልም የልጆቹ ስም በየስማቸውን በየትውልዳቸው እንዲህ ነው፤ የእስማኤል የበኵር ልጁ፥

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 25:13
14 Referências Cruzadas  

ስለ ይስ​ማ​ኤ​ልም እነሆ፥ ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ፤ እባ​ር​ከ​ዋ​ለሁ፤ አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ እጅ​ግም አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ዐሥራ ሁለት አለ​ቆ​ች​ንም ይወ​ል​ዳል፤ ታላቅ ሕዝ​ብም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።


የይ​ስ​ማ​ኤል የበ​ኵር ልጁ ናቡ​አት፥ ቄዳር፥ ነብ​ዳ​ኤል፥ መብ​ሳን፥


ዔሳው ወደ ይስ​ማ​ኤል ሄደ፤ ቤሴ​ሞ​ት​ንም በፊት ካሉ ሚስ​ቶቹ ጋር ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ወሰ​ዳት፤ እር​ስ​ዋም የና​ኮር ወን​ድም የአ​ብ​ር​ሃም ልጅ የሆ​ነው የይ​ስ​ማ​ኤል ልጅና የና​ቡ​ዓት እኅት ናት።


የይ​ስ​ማ​ኤ​ልን ልጅ የና​ቡ​አት እኅት ቤሴ​ሞ​ትን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጠ​ብ​ቅህ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቀኝ እጁ ይጋ​ር​ድህ።


እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ እኔ ጥቁር ነኝ፤ ነገር ግን ውብ ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድን​ኳ​ኖች እንደ ሰሎ​ሞ​ንም መጋ​ረ​ጃ​ዎች።


ምድረ በዳ​ውና ከተ​ሞ​ችዋ፥ የቄ​ዳ​ርም ነዋ​ሪ​ዎ​ችና መን​ደ​ሮች ድም​ፃ​ቸ​ውን ያንሡ፤ በዋ​ሻም የሚ​ኖሩ እልል ይበሉ፤ በተ​ራ​ሮ​ችም ራስ ላይ ሆነው ይጩኹ።


የቄ​ዳር በጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ የነ​ባ​ዮ​ትም አውራ በጎች ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ፤ በመ​ሠ​ዊ​ያዬ ላይም የተ​መ​ረ​ጠው መሥ​ዋ​ዕት ይቀ​ር​ባል፤ የጸ​ሎቴ ቤትም ይከ​ብ​ራል።


ወደ ኬቲም ደሴ​ቶች እለ​ፉና ተመ​ል​ከቱ፤ ወደ ቄዳ​ርም ላኩና እጅግ መር​ምሩ፤ እን​ደ​ዚ​ህም ያለ ነገር ሆኖ እንደ ሆነ እዩ።


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ስለ መታ​ቸው ስለ ቄዳ​ርና ስለ አሦር መን​ግ​ሥ​ታት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ተነሡ ወደ ቄዳ​ርም ውጡ፤ የም​ሥ​ራ​ቅ​ንም ልጆች አጥፉ።


ዓረ​ብና የቄ​ዳር አለ​ቆች ሁሉ የእ​ጅሽ ነጋ​ዴ​ዎች ነበሩ፤ በግ​መ​ሎ​ችና በአ​ውራ በጎች፥ በፍ​የ​ሎ​ችም በእ​ነ​ዚህ ከአ​ንቺ ጋር ይነ​ግዱ ነበር።


እስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም ስለ ነበሩ የወ​ርቅ ጕትቻ ነበ​ራ​ቸ​ውና ጌዴ​ዎን፥ “ሁላ​ች​ሁም ከም​ር​ኮ​አ​ችሁ ጕት​ቻ​ች​ሁን እን​ድ​ት​ሰ​ጡኝ እለ​ም​ና​ች​ኋ​ለሁ” አላ​ቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios