Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 2:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም አዳ​ምን እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዘው፥ “በገ​ነት ካለው ዛፍ ሁሉ ብላ፤

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እግዚአብሔር አምላክ ሰውን እንዲህ በማለት አዘዘው፤ “በአትክልት ስፍራው ውስጥ ከሚገኝ ከማንኛውም ዛፍ ፍሬ ትበላለህ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ከዚያም ጌታ እግዚአብሔር ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ “በገነት ካለው ዛፍ ሁሉ ብላ፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እግዚአብሔር አምላክ ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ “በአትክልቱ ቦታ ከሚገኙት ዛፎች ሁሉ ፍሬ ልትበላ ትችላለህ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፤ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 2:16
8 Referências Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “እነሆ፥ መብል ይሆ​ና​ችሁ ዘንድ በየ​ዘሩ የሚ​ዘ​ራ​ው​ንና የሚ​በ​ቅ​ለ​ውን፥ በም​ድር ሁሉ ላይ የም​ት​ዘ​ሩ​ትን የእ​ህል ፍሬ፥ ዘሩ በው​ስጡ ያለ​ውን ቡቃያ፥ በየ​ፍ​ሬ​ውም የሚ​ዘ​ራ​ውን ዛፍ ሁሉ ሰጠ​ኋ​ችሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ሰውን ወስዶ ያበ​ጃ​ትም፥ ይጠ​ብ​ቃ​ትም ዘንድ በኤ​ዶም ገነት አኖ​ረው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ለማ​የት ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን፥ ለመ​ብ​ላ​ትም መል​ካም የሆ​ነ​ውን ዛፍ ሁሉ ደግሞ ከም​ድር አበ​ቀለ፤ በገ​ነ​ትም መካ​ከል የሕ​ይ​ወ​ትን ዛፍ፥ መል​ካ​ም​ንና ክፉን የሚ​ያ​ሳ​የ​ው​ንና የሚ​ያ​ስ​ታ​ው​ቀ​ው​ንም ዛፍ አበ​ቀለ።


ነገር ግን በገ​ነት መካ​ከል ካለው ከዛፉ ፍሬ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አለ፦ እን​ዳ​ት​ሞቱ ከእ​ርሱ አት​ብሉ፤ አት​ን​ኩ​ትም።”


እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም ነውና፥ ከምስጋናም ጋር ቢቀበሉት የሚጣል ምንም የለም፤


በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ፥ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።


ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን፥ “በውኑ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በመ​ስ​ማት ደስ እን​ደ​ሚ​ለው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ቃ​ጠ​ልና በሚ​ታ​ረድ መሥ​ዋ​ዕት ደስ ይለ​ዋ​ልን? እነሆ፥ መታ​ዘዝ ከመ​ሥ​ዋ​ዕት፥ ማዳ​መ​ጥም የአ​ውራ በግ ስብ ከማ​ቅ​ረብ ይበ​ል​ጣል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios