Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 2:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ወንዝ ስም ጤግ​ሮስ ነው፤ እር​ሱም በአ​ሶር ላይ የሚ​ሄድ ነው። አራ​ተ​ኛ​ውም ወንዝ ኤፍ​ራ​ጥስ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ሦስተኛው፣ ከአሦር በስተምሥራቅ የሚፈስሰው የጤግሮስ ወንዝ ሲሆን፣ አራተኛው የኤፍራጥስ ወንዝ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የሦስተኛውም ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው፥ እርሱም በአሦር ምሥራቅ የሚሄድ ነው። አራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ሦስተኛው ወንዝ ጤግሮስ ይባላል፤ እርሱም በአሦር በስተምሥራቅ ይፈስሳል፤ አራተኛው ወንዝ ኤፍራጥስ ይባላል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የሦስተኚውም ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው፤ እርሱም በአሦር ምሥራቅ የሚሄድ ነው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 2:14
11 Referências Cruzadas  

አሦ​ርም ከዚ​ያች ሀገር ወጣ፤ ነነ​ዌን፥ ረሆ​ቦት የተ​ባ​ለ​ች​ውን ከተማ ካለ​ህን፥


የሴ​ምም ልጆች ኤላም፥ አሦር፥ አር​ፋ​ክ​ስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ ቃይ​ናን።


በዚ​ያ​ችም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ራም ተስፋ ያደ​ረ​ገ​ለ​ትን ቃል ኪዳን አጸና፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ከግ​ብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ ይህ​ችን ምድር ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤


በዚ​ያም የሚ​ያ​በራ ዕን​ቍና የሚ​ያ​ብ​ረ​ቀ​ርቅ ዕንቍ አለ። የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እር​ሱም የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያን ምድር ሁሉ ይከ​ብ​ባል፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ሰውን ወስዶ ያበ​ጃ​ትም፥ ይጠ​ብ​ቃ​ትም ዘንድ በኤ​ዶም ገነት አኖ​ረው።


ይስ​ማ​ኤ​ልም የኖ​ረ​በት የዕ​ድ​ሜው ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው ፤ ሸም​ግሎ ሞተ፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም ተጨ​መረ።


እነ​ር​ሱም የባ​ቢ​ሎን ልጆች፥ ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም ሁሉ፥ ፋቁድ፥ ሱሔ፥ ቆዓ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር አሦ​ራ​ው​ያን ሁሉ፥ መልከ መል​ካ​ሞች ጐበ​ዛ​ዝት፥ መሳ​ፍ​ን​ትና መኳ​ን​ንት ሁሉ፥ መሳ​ፍ​ን​ትና አማ​ካ​ሪ​ዎች ሁሉ፥ በሦ​ስት ወገን በፈ​ረስ ላይ የተ​ቀ​መጡ ናቸው።


ተመ​ል​ሳ​ችሁ ተጓዙ፤ ወደ አሞ​ራ​ው​ያን ተራራ፥ ወደ አረ​ባም ሀገ​ሮች ሁሉ፥ በተ​ራ​ራ​ውም፥ በሜ​ዳ​ውም፥ በሊ​ባም፥ በባ​ሕ​ርም ዳር ወዳሉ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን ምድር፥ ወደ ሊባ​ኖ​ስም ፊት ለፊት እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ድረስ ሂዱ።


የእ​ግ​ራ​ችሁ ጫማ የም​ት​ረ​ግ​ጣት ስፍራ ሁሉ ለእ​ና​ንተ ትሆ​ና​ለች፤ ከም​ድረ በዳም፥ ከአ​ን​ጢ​ሊ​ባ​ኖ​ስም፥ ከታ​ላ​ቁም ከኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ባሕር ድረስ ዳር​ቻ​ችሁ ይሆ​ናል።


መለከትም ያለውን ስድስተኛውን መልአክ “በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ የታሰሩትን አራቱን መላእክት ፍታቸው፤” አለው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios