Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 14:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ተመ​ል​ሰ​ውም ቃዴስ ወደ ተባ​ለች ወደ ፍርድ ምንጭ መጡ፤ የአ​ማ​ሌ​ቅን አለ​ቆች ሁሉና በአ​ሳ​ሶን ታማር የሚ​ኖሩ አሞ​ራ​ው​ያ​ን​ንም ገደ​ሉ​አ​ቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ከዚያም ተመልሰው ዓይንሚስፖጥ ወደተባለው ወደ ቃዴስ መጡ፤ የአማሌቃውያንና በሐሴሶን ታማር ይኖሩ የነበሩትን የአሞራውያንን ግዛት በሙሉ ድል አድርገው ያዙ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ተመልሰውም ቃዴስ ወደተባለች ወደ ዓይንሚስፓጥ መጡ፥ የአማሌቅን አገር ሁሉና ደግሞ በሐሴቦን ታማር የነበረውን አሞራውያንን መቱ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ከዚያም ተመልሰው ወደ ቃዴስ መጡ፤ በዚያን ጊዜ የዚህ ቦታ ስም ዔይንሚሽፖጥ ይባል ነበር። የዐማሌቃውያንንም ምድር ሁሉ ያዙ፤ በሐጸጾን ታማር ይኖሩ የነበሩትን አሞራውያንንም አሸነፉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ተመልሰውም ቃዴስ ወደ ተባለች ወደ ዓይንሚስፓጥ መጡ፤ የአማሌቅን አገር ሁሉና ደግሞ በሐሴሶን ታማር የነበረውን አሞራውያንን መቱ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 14:7
19 Referências Cruzadas  

ስለ​ዚ​ህም የዚ​ያን ጕድ​ጓድ ስም “በፊቴ የተ​ገ​ለ​ጠ​ልኝ የእ​ርሱ ጕድ​ጓድ” ብላ ጠራ​ችው፤ እር​ሱም በቃ​ዴ​ስና በባ​ሬድ መካ​ከል ነው። አጋ​ርም ተመ​ለ​ሰች።


አብ​ር​ሃ​ምም ከዚያ ተነ​ሥቶ ወደ አዜብ ምድር አቅ​ጣጫ ሄደ፤ በቃ​ዴ​ስና በሱር መካ​ከ​ልም ኖረ፤ በጌ​ራ​ራም በእ​ን​ግ​ድ​ነት ተቀ​መጠ።


ቴም​ና​ሕም ለዔ​ሳው ልጅ ለኤ​ል​ፋዝ ዕቅ​ብት ነበ​ረች፤ አማ​ሌ​ቅ​ንም ለኤ​ል​ፋዝ ወለ​ደ​ች​ለት፤ የዔ​ሳ​ውም ሚስት የሐ​ዳሶ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።


ቆሬ መስ​ፍን፥ ጎቶን መስ​ፍን፥ አማ​ሌቅ መስ​ፍን፤ በኤ​ዶም ምድር የኤ​ል​ፋዝ መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው፤ እነ​ዚህ የሓ​ዳሶ ልጆች ናቸው ።


ሰዎ​ችም መጥ​ተው፥ “ከባ​ሕሩ ማዶ ከሶ​ርያ ታላቅ ሠራ​ዊት መጥ​ቶ​ብ​ሃል፤ እነ​ሆም፥ ዓይ​ን​ጋዲ በተ​ባ​ለች በሐ​ሴ​ሶን ታማር ናቸው” ብለው ለኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ነገ​ሩት።


ዓሣ አጥ​ማ​ጆ​ችም ከዓ​ይ​ን​ጋዲ ጀምሮ እስከ ዓይ​ን​ኤ​ግ​ላ​ይም ድረስ በዚያ ይቆ​ማሉ። ያም መረብ መዘ​ር​ጊያ ይሆ​ናል፤ ዓሣ​ዎ​ችም እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣ​ዎች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው እጅግ ይበ​ዛሉ።


ከጋ​ድም ድን​በር ቀጥሎ በደ​ቡብ በኩል ድን​በሩ ከታ​ማር ጀምሮ እስከ ሜሪባ ቃዴስ ውኃ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ይሆ​ናል።


ገሥ​ግ​ሠ​ውም በቃ​ዴስ ፋራን ምድረ በዳ ወዳ​ሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ደረሱ፤ ወሬ​ው​ንም ለእ​ነ​ር​ሱና ለማ​ኅ​በሩ ሁሉ ነገ​ሩ​አ​ቸው፤ የም​ድ​ሪ​ቱ​ንም ፍሬ አሳ​ዩ​አ​ቸው።


ዐማ​ሌ​ቃ​ዊና ከነ​ዓ​ናዊ በፊ​ታ​ችሁ ናቸ​ውና በሰ​ይፍ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ከ​ተል ተመ​ል​ሳ​ች​ኋ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር አይ​ሆ​ንም።”


በዚ​ያም ተራራ ላይ የተ​ቀ​መጡ ዐማ​ሌ​ቃ​ዊና ከነ​ዓ​ናዊ ወረዱ፤ መት​ተ​ዋ​ቸ​ውም እስከ ኤርማ ድረስ አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው። ወደ ከተ​ማም ተመ​ለሱ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ፤ ሕዝ​ቡም በቃ​ዴስ ተቀ​መጡ፤ ማር​ያ​ምም በዚያ ሞተች፤ ተቀ​በ​ረ​ችም።


ዐማ​ሌ​ቅ​ንም አይቶ በም​ሳሌ ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ “ዐማ​ሌቅ የአ​ሕ​ዝብ አለቃ ነበረ፤ ዘራ​ቸ​ውም ይጠ​ፋል።”


“ከኮ​ሬ​ብም ተጓ​ዝን፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘን በታ​ላቁ፥ እጅ​ግም በሚ​ያ​ስ​ፈራ በዚያ ባያ​ች​ሁት ምድረ በዳ ሁሉ በኩል በአ​ሞ​ሬ​ዎን ተራራ መን​ገድ ሄድን፤ ወደ ቃዴስ በር​ኔም መጣን።


ቀድሞ እንደ ተቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​በ​ትም ዘመን መጠን በቃ​ዴስ ብዙ ቀን ተቀ​መ​ጣ​ችሁ።


ናፍ​ላ​ዛ​ንና ከተ​ሞ​ቻ​ቸው፥ ሳዶን፥ አቃ​ዴስ፥ ሰባት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios