Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 11:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ሦራም መካን ነበ​ረች፤ ልጆ​ችም አል​ነ​በ​ሩ​አ​ትም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ሦራ መካን ነበረች፤ ልጅ አልነበራትም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ሦራም መካን ነበረች፥ ልጅ አልነበራትም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ሣራይ መኻን በመሆንዋ ልጅ አልወለደችም ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ሦራም መካን ነበረች፤ ልጅ አልነበራትም።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 11:30
14 Referências Cruzadas  

ታራም ልጁን አብ​ራ​ም​ንና የልጅ ልጁን የአ​ራ​ንን ልጅ ሎጥን፥ የል​ጁ​ንም የአ​ብ​ራ​ምን ሚስት ምራ​ቱን ሦራን ወሰደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ወደ ከነ​ዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር አወ​ጣ​ቸው። ወደ ካራ​ንም መጡ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጡ።


ይስ​ሐ​ቅም ስለ ሚስቱ ርብቃ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመነ፤ መካን ነበ​ረ​ችና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማው፤ ሚስቱ ርብ​ቃም ፀነ​ሰች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልያ የተ​ጠ​ላች መሆ​ን​ዋን በአየ ጊዜ ማኅ​ፀ​ን​ዋን ከፈ​ተ​ላት፤ ራሔል ግን መካን ነበ​ረች።


ለእኛ አይ​ደ​ለም፥ አቤቱ፥ ለእኛ አይ​ደ​ለም፥ ነገር ግን ለስ​ምህ፥ ስለ ምሕ​ረ​ት​ህና ስለ እው​ነ​ት​ህም ምስ​ጋ​ናን እን​ስጥ


እነሆ፥ ከዘ​መ​ዶ​ችሽ ወገን የም​ት​ሆን ኤል​ሣ​ቤ​ጥም እር​ስዋ እንኳ በእ​ር​ጅ​ናዋ ወንድ ልጅን ፀን​ሳ​ለች፤ መካን ትባል የነ​በ​ረ​ችው ከፀ​ነ​ሰች እነሆ፥ ይህ ስድ​ስ​ተኛ ወር ነው።


ልጅም አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም፤ ኤል​ሳ​ቤጥ መካን ነበ​ረ​ችና፤ ሁለ​ቱም አር​ጅ​ተው ነበር፤ ዘመ​ና​ቸ​ውም አልፎ ነበር።


ከዳን ወገን የሆነ ማኑሄ የሚ​ባል አንድ የሶ​ራሕ ሰው ነበረ፤ ሚስ​ቱም መካን ነበ​ረች፤ ልጅም አል​ወ​ለ​ደ​ችም ነበር።


ሁለ​ትም ሚስ​ቶች ነበ​ሩት፤ የአ​ን​ዲቱ ስም ሐና፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ስም ፍናና ነበረ፤ ለፍ​ና​ናም ልጆች ነበ​ሩ​አት፤ ለሐና ግን ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​አ​ትም።


ለሐ​ናም ልጅ ስላ​ል​ነ​በ​ራት አንድ ዕድል ፋንታ ሰጣት፤ ሕል​ቃ​ናም ከዚ​ያ​ች​ኛ​ይቱ ይልቅ ሐናን ይወ​ድድ ነበር። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ማኅ​ፀ​ን​ዋን ዘግቶ ነበር።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios