Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ገላትያ 6:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህስ የሚ​ያ​ደ​ክ​መኝ አይ​ኑር፤ እኔ የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን መከራ በሥ​ጋዬ እሸ​ከ​ማ​ለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እኔ የኢየሱስን ምልክት በሥጋዬ ተሸክሜአለሁና፣ ከእንግዲህ ወዲህ ማንም አያስቸግረኝ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እኔ የኢየሱስን ምልክት በሰውነቴ ላይ ተሸክሜአለሁና ከእንግዲህ ወዲህ ማንም አያስቸግረኝ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 በሰውነቴ ላይ ያለው የግርፋት ምልክት የኢየሱስ አገልጋይ መሆኔን ስለሚያመለክት ከእንግዲህ ወዲህ ማንም አያስቸግረኝ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እኔ የኢየሱስን ማኅተም በሥጋዬ ተሸክሜአለሁና ከእንግዲህ ወዲህ አንድ ስንኳ አያድክመኝ።

Ver Capítulo Cópia de




ገላትያ 6:17
14 Referências Cruzadas  

ይህ፦ እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ ይላል፤ ያም በያ​ዕ​ቆብ ስም ይጠ​ራል፤ ይህም፦ እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ ብሎ በእጁ ይጽ​ፋል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ስም ይጠ​ራል።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በከ​ተ​ማ​ዪቱ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መካ​ከል እለፍ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ዋም ስለ ተሠ​ራው ኀጢ​አት ሁሉ በሚ​ያ​ለ​ቅ​ሱና በሚ​ተ​ክዙ ሰዎች ግን​ባር ላይ ምል​ክት ጻፍ አለው።


ያላ​ዘ​ዝ​ና​ቸው ሰዎች ከእኛ ወጥ​ተው፦ ‘ትገ​ዘሩ ዘን​ድና የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ ትጠ​ብቁ ዘንድ ይገ​ባ​ች​ኋል’ ብለው በነ​ገር እንደ አወ​ኩ​አ​ች​ሁና ልባ​ች​ሁን እንደ አና​ወ​ጡት ሰም​ተ​ናል።


የክ​ር​ስ​ቶስ መከራ በእኛ ላይ እንደ በዛ መጠን እን​ዲሁ መጽ​ና​ና​ታ​ች​ንም በክ​ር​ስ​ቶስ ይበ​ዛ​ልና።


የክ​ር​ስ​ቶስ ሕይ​ወቱ በዚህ በሟች ሰው​ነ​ታ​ችን ላይ ይገ​ለጥ ዘንድ፥ ዘወ​ትር የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ሞት በሥ​ጋ​ችን እን​ሸ​ከ​ማ​ለን።


እርሱ ግን ሌላ አይ​ደ​ለም፤ የሚ​ያ​ው​ኳ​ችሁ ከክ​ር​ስ​ቶ​ስም ወን​ጌል ሊያ​ጣ​ምሙ የሚ​ወዱ አሉ እንጂ።


በእ​ር​ሱም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን አው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ የመ​ነ​ሣ​ቱ​ንም ኀይል በሕ​ማሙ እሳ​ተ​ፈ​ዋ​ለሁ፤ በሞ​ቱም እመ​ስ​ለ​ዋ​ለሁ።


አሁ​ንም በመ​ከ​ራዬ ደስ ይለ​ኛል፤ አካሉ ስለ ሆነች ስለ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን፥ ከክ​ር​ስ​ቶስ መከራ ጥቂ​ቱን በሥ​ጋዬ እፈ​ጽ​ማ​ለሁ።


አስ​ተ​ውሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ጸጋ የሚ​ያ​ቃ​ልል አይ​ኑር፤ ሕማ​ምን የም​ታ​መጣ፥ ብዙ​ዎ​ች​ንም የም​ታ​ስ​ታ​ቸ​ውና የም​ታ​ረ​ክ​ሳ​ቸው መራራ ሥር የም​ት​ገ​ኝ​በ​ትም አይ​ኑር።


ኢያ​ሱም፥ “ለምን አጠ​ፋ​ኸን? ዛሬ እን​ዳ​ጠ​ፋ​ኸን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ያጥ​ፋህ” አለው፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ወገ​ሩት፤ በእ​ሳ​ትም አቃ​ጠ​ሉት፤ በድ​ን​ጋ​ይም ወገ​ሩ​አ​ቸው።


ታናናሾችና ታላላቆችም ባለጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፥


የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios