Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ገላትያ 4:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 “የማ​ት​ወ​ልድ መካን ደስ ይላ​ታል፤ ምጥ የማ​ታ​ው​ቀ​ውም ደስ ብሎ​አት እልል ትላ​ለች፤ ባል ካላት ይልቅ የፈ​ቲቱ ልጆች ብዙ​ዎች ናቸ​ውና” ተብሎ ተጽ​ፎ​አል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፦ “አንቺ የማትወልጅ መካን ሆይ፤ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፣ በእልልታ ጩኺ፤ ባል ካላት ይልቅ፣ የብቸኛዪቱ ልጆች በዝተዋልና።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 “አንቺ የማትወልጅ መካን! ደስ ይበልሽ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ! እልል በዪ፥ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ የብቸኛይቱ ልጆች በዝተዋልና” ተብሎ ተጽፎአልና።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 “አንቺ ልጆች የማትወልጂ መኻን ደስ ይበልሽ! አንቺ ለመውለድ አምጠሽ የማታውቂ ‘እልል!’ በዪ፤ ባል ካላት ሴት ይልቅ ባል የሌላት ሴት ብዙ ልጆች አሉአት” ተብሎ ተጽፎአል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 አንቺ የማትወልጅ መካን፥ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፥ እልል በዪና ጩኺ፤ ባል ካላቱ ይልቅ የብቸኛይቱ ልጆች በዝተዋልና ተብሎ ተጽፎአል።

Ver Capítulo Cópia de




ገላትያ 4:27
9 Referências Cruzadas  

ወን​ድ​ም​ዋም አቤ​ሴ​ሎም፥ “ወን​ድ​ምሽ አም​ኖን ከአ​ንቺ ጋር ነበ​ርን? እኅቴ ሆይ፥ አሁን ግን ዝም በዪ፤ ወን​ድ​ምሽ ነውና፤ ይህን ነገር ትና​ገሪ ዘንድ በል​ብሽ አታ​ስቢ” አላት። ትዕ​ማ​ርም በወ​ን​ድ​ምዋ በአ​ቤ​ሴ​ሎም ቤት መበ​ለት ሆና ተቀ​መ​ጠች።


ለእኛ አይ​ደ​ለም፥ አቤቱ፥ ለእኛ አይ​ደ​ለም፥ ነገር ግን ለስ​ምህ፥ ስለ ምሕ​ረ​ት​ህና ስለ እው​ነ​ት​ህም ምስ​ጋ​ናን እን​ስጥ


አን​ቺም በል​ብሽ፦ የወ​ላድ መካን ሆኛ​ለ​ሁና፥ እኔም መበ​ለት ነኝና እነ​ዚ​ህን ማን ወለ​ደ​ልኝ? እነ​ዚ​ህ​ንስ ማን አሳ​ደ​ጋ​ቸው? እነሆ፥ ብቻ​ዬን ቀርቼ ነበር፤ እነ​ዚ​ህስ ከወ​ዴት መጡ?” ትያ​ለሽ።


ልጆች፥ እንደ ገና የም​ጨ​ነ​ቅ​ላ​ችሁ ክር​ስ​ቶስ በል​ባ​ችሁ እስ​ኪ​ሣ​ል​ባ​ችሁ ድረስ ነው።


ብቻዋንም ኖራ በእውነት ባልቴት የምትሆን በእግዚአብሔር ተስፋ ታደርጋለች፤ ሌትና ቀንም በልመና በጸሎትም ጸንታ ትኖራለች፤


እን​ጀራ ጠግ​በው የነ​በሩ ተራቡ፤ ተር​በ​ውም የነ​በሩ ጠገቡ፤ መካ​ኒቱ ሰባት ወል​ዳ​ለ​ችና፥ ብዙም የወ​ለ​ደ​ችው መው​ለድ አል​ቻ​ለ​ችም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios