Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ገላትያ 4:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 መቅ​ና​ትስ ዘወ​ትር ለመ​ል​ካም ሥራ ልት​ቀኑ ይገ​ባል፤ ነገር ግን እኔ ከእ​ና​ንተ ዘንድ ባለ​ሁ​በት ጊዜ ብቻ አይ​ደ​ለም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ለበጎ እስከ ሆነ ድረስ ተቈርቋሪ መሆን መልካም ነው፤ ይህም መሆን የሚገባው ዘወትር እንጂ እኔ ከእናንተ ጋራ ሳለሁ ብቻ አይደለም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ሁልጊዜ መልካም ለሆነ ነገር ሁሉ ብትቀኑ መልካም ነው፤ ነገር ግን እኔ ከእናንተ ጋር ባለሁበት ጊዜ ብቻ አይደለም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ዓላማው ጥሩ ከሆነ መትጋት ምንጊዜም መልካም ነው፤ ነገር ግን ይህ መትጋታችሁ እኔ ከእናንተ ጋር በምኖርበት ጊዜ ብቻ አይሁን።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ በምኖርበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ በመልካም ነገር ተፈላጊ ብትሆኑ መልካም ነው።

Ver Capítulo Cópia de




ገላትያ 4:18
13 Referências Cruzadas  

ጽድ​ቅ​ንም እንደ ጥሩር ለበሰ፤ በራ​ሱም ላይ የማ​ዳ​ንን ራስ ቍር አደ​ረገ፤ የበ​ቀ​ል​ንም ልብስ ለበሰ።


ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም፥ “የቤ​ትህ ቅናት በላኝ” የሚል ቃል ተጽፎ እን​ዳለ ዐሰቡ።


አሁ​ንም የተ​ወ​ደ​ዳ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የጸ​ና​ች​ሁና የማ​ት​ና​ወጡ ሁኑ፤ ዘወ​ትር በጎ ምግ​ባ​ርን አብ​ዝ​ታ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አበ​ር​ክቱ፤ ስለ ጌታ​ችን መድ​ከ​ማ​ችሁ ለከ​ንቱ እን​ዳ​ይ​ደለ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።


መጀ​መ​ሪያ ወን​ጌ​ልን በሰ​በ​ክ​ሁ​ላ​ችሁ ጊዜ፥ ከሥጋ ድካም የተ​ነሣ እንደ ነበር ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


እነ​ዚ​ያማ ይቀ​ኑ​ባ​ች​ኋል፤ ነገር ግን በእ​ነ​ርሱ ላይ እን​ድ​ት​ቀኑ ሊዘ​ጉ​አ​ችሁ ይወ​ዳሉ እንጂ ለመ​ል​ካም አይ​ደ​ለም።


ቃሌን ለውጬ አሁን በእ​ና​ንተ ዘንድ ልገኝ እሻ​ለሁ፤ ስለ እና​ንተ የም​ና​ገ​ረ​ውን አጣ​ለ​ሁና።


ነገር ግን ምና​ል​ባት የመ​ጣሁ እንደ ሆነ፥ ሳል​ኖ​ርም ቢሆን በወ​ን​ጌል ሃይ​ማ​ኖት እየ​ተ​ጋ​ደ​ላ​ችሁ በአ​ንድ መን​ፈ​ስና በአ​ንድ አካል ጸን​ታ​ችሁ እን​ደ​ም​ት​ኖሩ አይና እሰማ ዘንድ ሥራ​ችሁ ለክ​ር​ስ​ቶስ ትም​ህ​ርት እን​ደ​ሚ​ገባ ይሁን።


አሁ​ንም ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ዘወ​ትር እን​ደ​ም​ት​ሰ​ሙኝ ሳለሁ ብቻ ሳይ​ሆን፥ ሳል​ኖ​ርም በፍ​ር​ሀ​ትና በመ​ን​ቀ​ጥ​ቀጥ ሆና​ችሁ ለድ​ኅ​ነ​ታ​ችሁ ሥሩ።


መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና፤ ንስሓም ግባ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios