Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዕዝራ 8:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በካ​ሲ​ፍያ ስፍራ ወደ ነበ​ረው ወደ አለ​ቃው ወደ አዶ ላክ​ኋ​ቸው፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤትም አገ​ል​ጋ​ዮ​ችን ያመ​ጡ​ልን ዘንድ በካ​ሲ​ፍያ ስፍራ ለሚ​ኖ​ሩት ለአ​ዶና ለወ​ን​ድ​ሞቹ ለና​ታ​ኒም የሚ​ነ​ግ​ሩ​አ​ቸ​ውን በአ​ፋ​ቸው አደ​ረ​ግሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እነርሱንም ካሲፍያ በሚባል ስፍራ አለቃ ወደ ሆነው ወደ አዶ ላክኋቸው፤ በአምላካችን ቤት የሚያገለግሉ ሰዎችን ያመጡልን ዘንድ በካሲፍያ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች ለሆኑት ለአዶና ለሥጋ ዘመዶቹ የሚናገሩትን አስታወቅኋቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በካሲፍያ ስፍራ አለቃ ወደ ሆነው ወደ ኢዶ ላክኋቸው፥ ለአምላካችን ቤት አገልጋዮችን እንዲያመጡልን በካሲፍያ ስፍራ ለሚኖሩት ለኢዶና ለወንድሞቹ ለቤተ መቅደስ አገልጋዮች ምን የሚነግሩአቸውን አስታወቅኳቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እነርሱንም በካሲፍያ ለሚኖር ሕዝብ መሪ ወደ ሆነው ወደ ኢዶ በመላክ ኢዶና የቤተ መቅደስ ሠራተኞች የሆኑት ረዳቶቹ በቤተ መቅደስ የሚያገለግሉ ሰዎችን ይልኩልን ዘንድ እንዲነግሩአቸው አደረግሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በካሲፍያ ስፍራ ወደ ነበረው ወደ አለቃው ወደ አዶ ላክኋቸው፤ ለአምላካችን ቤት አገልጋዮችን ያመጡልን ዘንድ በካሲፍያ ስፍራ ለሚኖሩት ለአዶና ለወንድሞቹ ለናታኒም የሚነግሩአቸውን በአፋቸው አደረግሁ።

Ver Capítulo Cópia de




ዕዝራ 8:17
16 Referências Cruzadas  

ንጉ​ሡም፥ “በዚህ ሁሉ ነገር የኢ​ዮ​አብ እጅ ከአ​ንቺ ጋር አለን?” አላት። ሴቲ​ቱም ንጉ​ሡን አለ​ችው፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ! ጌታዬ ንጉሥ ከተ​ና​ገ​ረው ነገር ሁሉ ወደ ቀኝም ወደ ግራም ሊል የሚ​ችል የለም፤ አገ​ል​ጋ​ይህ ኢዮ​አብ አዝ​ዞ​ኛል፤ ይህ​ንም ቃል ሁሉ በአ​ገ​ል​ጋ​ይህ አፍ አደ​ረ​ገው።


ወደ ንጉ​ሡም ገብ​ተሽ እን​ዲህ ያለ​ውን ቃል ንገ​ሪው” አላት፤ ኢዮ​አ​ብም ቃሉን በእ​ር​ስዋ አፍ አደ​ረገ።


በእ​ስ​ራ​ኤል ከተ​ሞ​ችና በአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ቻ​ቸው መጀ​መ​ሪያ የተ​ቀ​መጡ ካህ​ናት፥ ሌዋ​ው​ያ​ንም፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ነበሩ።


ናታ​ኒም፤ የሲሓ ልጆች፥ የሐ​ሡፊ ልጆች፥ የጠ​ብ​ዖት ልጆች፤


እነ​ዚህ ናታ​ኒም ሁሉና የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ።


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከካ​ህ​ና​ቱም፥ ከሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም፥ ከመ​ዘ​ም​ራ​ኑም፥ ከበ​ረ​ኞ​ቹም፥ ከና​ታ​ኒ​ምም በን​ጉሡ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት ዐያ​ሌ​ዎች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጡ።


ወደ አለ​ቆ​ቹም ወደ አል​ዓ​ዛር፥ ወደ አር​ኤል፥ ወደ ሰማ​አያ፥ ወደ ሀሎ​ናም፥ ወደ ያሪብ፥ ወደ ሄል​ና​ታን፥ ወደ ናታን፥ ወደ ዘካ​ር​ያስ፥ ወደ ሜሱ​ላም፥ ደግ​ሞም ወደ ዐዋ​ቂ​ዎቹ ወደ ዮያ​ሪ​ብና ወደ ሄል​ና​ታን ላክሁ።


አን​ተም ትና​ገ​ረ​ዋ​ለህ፤ ቃሌ​ንም በአፉ ታደ​ር​ገ​ዋ​ለህ፤ እኔ አን​ደ​በ​ት​ህ​ንና አን​ደ​በ​ቱን አረ​ታ​ለሁ፤ የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ት​ንም አለ​ብ​ማ​ች​ኋ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጁን ዘር​ግቶ አፌን ዳሰሰ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “እነሆ፥ ቃሌን በአ​ፍህ ውስጥ አኑ​ሬ​አ​ለሁ፤


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ብት​መ​ለስ እመ​ል​ስ​ሃ​ለሁ፤ በፊ​ቴም ትቆ​ማ​ለህ፤ የከ​በ​ረ​ው​ንም ከተ​ዋ​ረ​ደው ብት​ለይ እንደ አፌ ትሆ​ና​ለህ፤ እነ​ርሱ ወደ አንተ ይመ​ለ​ሳሉ፤ አንተ ግን ወደ እነ​ርሱ አት​መ​ለ​ስም።


እኔም፦ እነሆ፥ ሌዋ​ው​ያ​ንን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ወስ​ጄ​አ​ለሁ፤ የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን አገ​ል​ግ​ሎት ያደ​ርጉ ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሰጡ ስጦ​ታ​ዎች ናቸው።


ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቃሌ​ንም በአፉ አኖ​ራ​ለሁ፤ እንደ አዘ​ዝ​ሁ​ትም ይነ​ግ​ራ​ቸ​ዋል፤


ስለዚህ ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም እኔ አንተን እንዳዘዝሁ፥ ሽማግሌዎችን እንድትሾም በቀርጤስ ተውሁህ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios