Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዕዝራ 7:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እኔም ንጉሡ አር​ተ​ሰ​ስታ በወ​ንዝ ማዶ ላሉት ግምጃ ቤቶች ሁሉ ይህን ትእ​ዛዝ ሰጥ​ቻ​ለሁ፦ የሰ​ማይ አም​ላክ ሕግ ጸሓፊ ካህኑ ዕዝራ ከእ​ና​ንተ የሚ​ፈ​ል​ገ​ውን ሁሉ አዘ​ጋ​ጁ​ለት፤

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በኤፍራጥስ ማዶ የምትገኙ በጅሮንዶች ሁሉ፣ የሰማይ አምላክ ሕግ መምህር የሆነው ካህኑ ዕዝራ የሚጠይቃችሁን ሁሉ በትጋት እንድትሰጡት እኔ ንጉሥ አርጤክስስ እነሆ አዝዣለሁ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እኔም ንጉሡ አርጤክስስ በወንዝ ማዶ ለምትገኙ ገንዘብ ያዦች ሁሉ፦ የሰማያት አምላክ ሕግ ጸሐፊ የሆነው ካህኑ ዕዝራ የሚጠይቃችሁን ሁሉ በትጋት እንድትሰጡት ይህን ትእዛዝ ሰጥቻለሁ፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “እኔ ንጉሥ አርጤክስስ ከኤፍራጥስ ምዕራብ የምትገኙ በጅሮንዶች ሁሉ በሰማይ አምላክ ሕግ ምሁር የሆነው ካህኑ ዕዝራ የሚጠይቃችሁን ሁሉ ትሰጡት ዘንድ አዝዣለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 “እኔም ንጉሡ አርጤክስስ በወንዝ ማዶ ላሉት በጅሮንዶች ሁሉ ይህን ትእዛዝ ሰጥቻለሁ፦ ‘የሰማይ አምላክ ሕግ ጸሐፊ ካህኑ ዕዝራ ከእናንተ የሚፈልገውን ሁሉ አዘጋጁለት፤

Ver Capítulo Cópia de




ዕዝራ 7:21
11 Referências Cruzadas  

ይህ​ችም ከተማ የተ​ሠ​ራች እንደ ሆነ፥ ቅጥ​ር​ዋም የታ​ደሰ እንደ ሆነ፥ ሰላም እን​ደ​ማ​ይ​ኖ​ርህ ለን​ጉሡ እና​ስ​ታ​ው​ቃ​ለን።”


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እጅግ ኀያ​ላን ነገ​ሥ​ታት ነበሩ፤ በወ​ን​ዝም ማዶ ያለ​ውን ሀገር ሁሉ ይገዙ ነበር፤ ግብ​ር​ንና እጅ መን​ሻ​ንም ይቀ​በሉ ነበር።


“አሁ​ንም አንተ በወ​ንዝ ማዶ ያለ​ኸው የሀ​ገሩ ገዥ ተን​ት​ናይ ደግሞ አሰ​ተ​ር​ቡ​ዝ​ናይ በወ​ንዝ ማዶም ያሉ ተባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ችሁ አፈ​ር​ስ​ካ​ው​ያን ከዚያ ራቁ፤


ከዚ​ህም ነገር በኋላ በፋ​ርስ ንጉሥ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ መን​ግ​ሥት ዕዝራ የሠ​ራያ ልጅ፥ የዓ​ዛ​ር​ያስ ልጅ፥ የኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ፥


እስከ መቶ መክ​ሊት ብርም ቢሆን፥ እስከ መቶም የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ስንዴ፥ እስከ መቶም የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ የወ​ይን ጠጅ፥ እስከ መቶም የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ ዘይት ቢሆን፥ ጨውም ያለ ልክ ቢሆን፤


ይህም ዕዝራ ከባ​ቢ​ሎን ወጣ፤ እር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ የሰ​ጠ​ውን ሕግ ዐዋቂ ነበረ፤ የአ​ም​ላ​ኩም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረ​ችና ንጉሡ ያሻ​ውን ሁሉ ሰጠው።


የን​ጉ​ሡ​ንም ትእ​ዛዝ በወ​ንዙ ማዶ ላሉት ለን​ጉሡ ሹሞ​ችና ገዢ​ዎች ሰጡ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝ​ቡ​ንና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት አከ​በሩ።


ንጉ​ሡ​ንም፥ “ንጉሥ ደስ ቢለው፥ እስከ ይሁዳ ሀገር እን​ዲ​ያ​ደ​ር​ሱኝ በወ​ንዝ ማዶ ላሉት ገዦች ደብ​ዳቤ ይስ​ጠኝ፤


እንደ በረሃ ቋያ የኀ​ያል ፍላ​ጾች የተ​ሳሉ ናቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios