Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዕዝራ 6:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ይህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ይሠሩ ዘንድ ለአ​ይ​ሁድ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን፥ በወ​ንዝ ማዶ ካለው ሀገር ከሚ​መ​ጣው ግብር ከን​ጉሡ ገን​ዘብ ለእ​ነ​ዚህ ሰዎች ወጭ​ውን በት​ጋት እን​ድ​ት​ሰ​ጡ​አ​ቸው፥ ሥራም እን​ዳ​ታ​ስ​ፈ​ቱ​አ​ቸው አዝ​ዣ​ለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በተጨማሪም የአይሁድ መሪዎች ይህን የእግዚአብሔር ቤት እንደ ገና ሲሠሩ፣ እናንተ ምን እንደምታደርጉላቸው ይህን ትእዛዝ ሰጥቻለሁ፤ ሥራውም እንዳይቋረጥ የእነዚህ ሰዎች ወጪ በሙሉ ከመንግሥት ግምጃ ቤትና ከኤፍራጥስ ማዶ ከሚገኘው ገቢ ላይ ይከፈል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ይህን የእግዚአብሔርን ቤት እንዲሠሩ ለአይሁድ ሽማግሌዎች የምታደርጉትን አዝዣለሁ፥ በወንዝ ማዶ ካለው አገር ከሚመጣው ግብር ከንጉሡ ገንዘብ ለእነዚህ ሰዎች ወጪውን በትጋት ይሰጣቸው፥ ሥራም እንዳታስፈቱአቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በዚሁ አጋጣሚ ይልቁንም የቤተ መቅደሱን ሥራ እንድታግዙአቸው አዝዣችኋለሁ። ስለዚህም አስፈላጊው የማሠሪያ ገንዘብ ሁሉ ከኤፍራጥስ ምዕራባዊ ክፍል ከተሰበሰበው የመንግሥት ግብር ሳይዘገይ ወጪ እየሆነ ይሰጣቸው፤ ሥራውም መሰናከል አይገባውም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ይህን የእግዚአብሔርን ቤት ይሠሩ ዘንድ ለአይሁድ ሽማግሌዎች የምታደርጉትን፥ በወንዝ ማዶ ካለው አገር ከሚመጣው ግብር ከንጉሡ ገንዘብ ለእነዚህ ሰዎች ወጪውን በትጋት እንድትሰጡአቸው፥ ሥራም እንዳታስፈቱአቸው አዝዣለሁ።

Ver Capítulo Cópia de




ዕዝራ 6:8
15 Referências Cruzadas  

ይህ​ችም ከተማ የተ​ሠ​ራች እንደ ሆነ፥ ቅጥ​ር​ዋም የታ​ደሰ እንደ ሆነ፥ ሰላም እን​ደ​ማ​ይ​ኖ​ርህ ለን​ጉሡ እና​ስ​ታ​ው​ቃ​ለን።”


የን​ጉ​ሡም የአ​ር​ተ​ሰ​ስታ መል​እ​ክ​ተኛ በደ​ረሰ ጊዜ በአ​ዛዡ በሬ​ሁ​ምና በጸ​ሓ​ፊው በሲ​ም​ሳይ፥ በተ​ባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ፊት መል​እ​ክ​ቱን ባነ​በበ ጊዜ ፈጥ​ነው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አይ​ሁድ በፈ​ረስ ሄዱ፤ በኀ​ይ​ልም አስ​ተ​ዉ​አ​ቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይን ግን በይ​ሁዳ ምር​ኮ​ኞች ላይ ነበረ፤ ይህም ነገር ወደ ዳር​ዮስ እስ​ኪ​ደ​ርስ ድረስ፥ መል​ሱም በመ​ል​እ​ክ​ተኛ እስ​ኪ​መጣ ድረስ አል​ከ​ለ​ከ​ሉ​አ​ቸ​ውም።


የአ​ይ​ሁድ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ሌዋ​ው​ያ​ንም በነ​ቢዩ በሐ​ጌና በአዶ ልጅ በዘ​ካ​ር​ያስ ትን​ቢት መሠ​ረት ሠሩ፤ ተከ​ና​ወ​ነ​ላ​ቸ​ውም። እንደ እስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ትእ​ዛዝ፥ እንደ ፋር​ስም ነገ​ሥ​ታት እንደ ቂሮ​ስና እንደ ዳር​ዮስ፥ እንደ አር​ተ​ሰ​ስ​ታም ትእ​ዛዝ ሠር​ተው ፈጸሙ።


በሦ​ስት ተራ ታላ​ላቅ ድን​ጋይ፥ በአ​ንድ ተራ እን​ጨት ይደ​ረግ፤ ወጭ​ውም ከን​ጉሡ ቤት ይሰጥ።


ይህም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ይሠራ ዘንድ ተዉ፤ የአ​ይ​ሁ​ድም አለ​ቆ​ችና የአ​ይ​ሁድ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ይህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት በስ​ፍ​ራው ይሥሩ።


ለሰ​ማይ አም​ላክ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ውን ወይ​ፈ​ኖ​ችና አውራ በጎች፥ ጠቦ​ቶ​ችም፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እን​ዳሉ እንደ ካህ​ናቱ ቃል ስን​ዴና ጨው፥ የወ​ይን ጠጅና ዘይት የሚ​ጠ​ይ​ቋ​ች​ሁን ዕለት ዕለት ስጡ​አ​ቸው።


ንጉ​ሡና ሰባቱ አማ​ካ​ሪ​ዎቹ በእ​ጅህ እን​ዳ​ለ​ችው እንደ አም​ላ​ክህ ሕግ ይሁ​ዳ​ንና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ትጐ​በኝ ዘንድ አዝ​ዘ​ዋል፤


በእ​ነ​ር​ሱም ላይ የን​ጉሥ ትእ​ዛዝ ነበረ፤ የመ​ዘ​ም​ራ​ኑም ሥር​ዐት ለየ​ዕ​ለቱ የተ​ሠራ ነበረ።


በቤ​ቱም አጠ​ገብ ላለው ለግ​ንብ በሮች፥ ለከ​ተ​ማ​ውም ቅጥር፥ ለም​ገ​ባ​በ​ትም ቤት እን​ጨት እን​ዲ​ሰ​ጠኝ ለን​ጉሡ ዱር ጠባቂ ለአ​ሳፍ ደብ​ዳቤ ይሰ​ጠኝ” አል​ሁት። ንጉ​ሡም ሁሉን ሰጠኝ። የከ​በ​ረች የአ​ም​ላኬ እጅ ከእኔ ጋር ነበ​ረ​ችና።


ብሩ የእኔ ነው፥ ወርቁም የእኔ ነው፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios