Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዕዝራ 3:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ኢያ​ሱም፥ ልጆ​ቹም ተሾሙ፤ ወን​ድ​ሞ​ቹም፥ የይ​ሁ​ዳም ልጆች ቀደ​ም​ያ​ልና ልጆቹ፥ የኢ​ን​ሐ​ዳ​ድም ልጆች፥ ልጆ​ቻ​ቸ​ውና ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ሌዋ​ው​ያ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት የሚ​ሠ​ሩ​ትን ያሠሩ ዘንድ በአ​ን​ድ​ነት ቆሙ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ኢያሱ፣ ወንዶች ልጆቹና ወንድሞቹ፣ የዮሖዳያ ዘሮች ቀድምኤልና ወንዶች ልጆቹ፣ የኤንሐዳድ ወንዶች ልጆች፣ ልጆቻቸውና ወንድሞቻቸው፣ ሌዋውያኑም ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤት የሚሠሩትን ሰዎች ለመቈጣጠር በአንድ ላይ ሆኑ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ኢያሱ፥ ልጆቹ፥ ወንድሞቹ፥ የይሁዳም ልጆች ቃድሚኤልና ልጆቹ፥ የሔናዳድም ልጆች፥ ልጆቻቸውና ወንድሞቻቸው ሌዋውያንም የእግዚአብሔርን ቤት የሚሠሩትን እንዲቆጣጠሩ እንደ አንድ ቆሙ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ሌዋዊው ኢያሱና ወንዶች ልጆቹ፥ እንዲሁም ዘመዶቹ፥ ቃድሚኤልና ከሖዳዊያ ቤተሰብ ወገን የሆኑ ወንዶች ልጆቹም ሁሉ በአንድነት ተባብረው ቤተ መቅደሱን እንደገና የመሥራቱን ኀላፊነት ተረከቡ፤ የሔናዳድ ዘሮች የሆኑት ሌዋውያንም ይረዱአቸው ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ኢያሱ፥ ልጆቹና ወንድሞቹ፥ የይሁዳም ልጆች ቀድምኤልና ልጆቹ፥ የኤንሐዳድም ልጆች፥ ልጆቻቸውና ወንድሞቻቸው፥ ሌዋውያንም የእግዚአብሔርን ቤት የሚሠሩትን ያሠሩ ዘንድ በአንድነት ቆሙ።

Ver Capítulo Cópia de




ዕዝራ 3:9
6 Referências Cruzadas  

ከእ​ነ​ዚ​ህም ውስጥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሥራ የሚ​ያ​ሠ​ሩት ሃያ አራት ሺህ ነበሩ፤ ስድ​ስቱ ሺህም ጻፎ​ችና ፈራ​ጆች ነበሩ።


ሰዎ​ቹም ሥራ​ውን በመ​ታ​መን አደ​ረጉ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ የተ​ሾ​ሙት፥ ሥራ​ው​ንም የሚ​ያ​ሠ​ሩት ሌዋ​ው​ያን ከሜ​ራሪ ልጆች ይኤ​ትና አብ​ድ​ያስ፥ ከቀ​ዓ​ትም ልጆች ዘካ​ር​ያ​ስና ሜሱ​ላም ነበሩ። ከሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ወገን በዜማ ዕቃ ዐዋ​ቂ​ዎች፥ የነ​በሩ ሁሉ፥


ሌዋ​ው​ያኑ፤ ከሁ​ድያ ልጆች ወገን የኢ​ዮ​ስ​ስና የቀ​ዳ​ም​ሔል ልጆች ሰባ አራት።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወዳ​ለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በመጡ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር የሰ​ላ​ት​ያል ልጅ ዘሩ​ባ​ቤል፥ የኢ​ዮ​ሴ​ዴ​ቅም ልጅ ኢያሱ፥ የቀ​ሩ​ትም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን፥ ከም​ርኮ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የተ​መ​ለ​ሱት ሁሉ ጀመሩ፤ ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሥራ እን​ዲ​ያ​ሠ​ሩት ሾሙ​አ​ቸው።


ከእ​ር​ሱም በኋላ የኢ​ን​ሓ​ዳድ ልጅ ባኒ ከዓ​ዛ​ር​ያስ ቤት ጀምሮ እስከ ማዕ​ዘኑ እስከ ግን​ቡ​መ​ዞ​ሪያ ድረስ ያለ​ውን ሌላ​ውን ክፍል ሠራ።


ሌዋ​ው​ያ​ኑም ከሆ​ዳ​ይዋ ወገን የኢ​ያ​ሱና የቀ​ድ​ም​ኤል ልጆች ሰባ አራት።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios