Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዕዝራ 10:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ይፈቱ ዘንድ እጃ​ቸ​ውን ሰጡ፤ ስለ በደ​ላ​ቸ​ውም ከመ​ን​ጋው አንድ አውራ በግ ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እነዚህ ሁሉ ሚስቶቻቸውን ለመፍታት ቃል በመግባት እጃቸውን ሰጡ፤ ስለ በደላቸውም እያንዳንዳቸው ከመንጋው አንዳንድ አውራ በግ ለበደል መሥዋዕት አቀረቡ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ሚስቶቻቸውን ለማሰናበት እጃቸውን ሰጡ፤ ስለ በደላቸውም ከመንጋው አንድ አውራ በግ ለበደል መሥዋዕት አቀረቡ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እነርሱም ሚስቶቻቸውን ፈተው ለማሰናበት ቃል ከገቡ በኋላ ለኃጢአታቸው ማስተስረያ የሚሆን አንድ የበግ አውራ ለሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ሚስቶቻቸውን ይፈቱ ዘንድ እጃቸውን ሰጡ፤ ስለ በደላቸውም ከመንጋው አንድ አውራ በግ ለበደል መሥዋዕት አቀረቡ።

Ver Capítulo Cópia de




ዕዝራ 10:19
9 Referências Cruzadas  

ከዚ​ያም በሄደ ጊዜ የሬ​ካ​ብን ልጅ ኢዮ​ና​ዳ​ብን በመ​ን​ገድ አገ​ኘው፤ ተቀ​ብ​ሎም መረ​ቀው፤ ኢዩም፥ “ልቤ ከል​ብህ ጋር ቅን እንደ ሆነ ያህል ልብህ ከልቤ ጋር በቅ​ን​ነት ነውን?” አለው። ኢዮ​ና​ዳ​ብም፥ “አዎን” አለው። ኢዩም፥ “እው​ነ​ት​ህስ ከሆነ እጅ​ህን ስጠኝ” አለ። እጁ​ንም ሰጠው፤ ወደ እር​ሱም ወደ ሰረ​ገ​ላው አወ​ጣው።


አለ​ቆ​ቹም ሁሉ፥ ኀያ​ላ​ኑም፥ ደግ​ሞም የን​ጉሡ የአ​ባቱ የዳ​ዊት ልጆች ሁሉ ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን ተገ​ዙ​ለት።


አሁ​ንም እንደ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ አን​ገ​ታ​ች​ሁን አታ​ደ​ን​ድኑ፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ስጡ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ወደ ተቀ​ደ​ሰው ወደ መቅ​ደሱ ግቡ፤ ጽኑ ቍጣ​ው​ንም ከእ​ና​ንተ እን​ዲ​መ​ልስ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዙ።


ከኢ​ሚር ልጆ​ችም አና​ኒና ዝብ​ድያ።


ግብ​ፃ​ው​ያ​ንና አሦ​ራ​ው​ያን፥ እን​ጀ​ራን ያጠ​ግ​ቡን ዘንድ እጃ​ቸ​ውን ሰጡን።


እርሱ ቢበ​ድ​ልና ከዚህ በኋላ ንስሓ ቢገባ፥ በቅ​ድ​ሚያ የወ​ሰ​ደ​ውን፥ ወይም በዐ​መ​ፅና በግፍ የተ​ቀ​በ​ለ​ውን፥ ወይም የተ​ሰ​ጠ​ውን አደራ፥ ወይም ጠፍቶ ያገ​ኘ​ውን፥


ስለ በደል መሥ​ዋ​ዕ​ትም ከመ​ን​ጋው ነውር የሌ​ለ​በ​ትን፥ ዋጋው እንደ በደሉ የተ​ገ​መ​ተ​ውን አውራ በግ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያምጣ።።


የሰ​ጠ​ኝ​ንም ጸጋ ዐው​ቀው አዕ​ማድ የሚ​ሏ​ቸው ያዕ​ቆ​ብና ኬፋ፥ ዮሐ​ን​ስም እኛ ወደ አሕ​ዛብ፥ እነ​ር​ሱም ወደ አይ​ሁድ እን​ድ​ን​ሄድ ለእ​ኔና ለበ​ር​ና​ባስ ቀኝ እጃ​ቸ​ውን ሰጡን።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios