Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሕዝቅኤል 4:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የብ​ረት ምጣ​ድም ወስ​ደህ በአ​ን​ተና በከ​ተ​ማ​ዪቱ መካ​ከል ለብ​ረት ቅጥር አድ​ር​ገው፤ ፊት​ህ​ንም ወደ እር​ስዋ አቅና፤ የተ​ከ​በ​በ​ችም ትሆ​ና​ለች፤ አን​ተም ትከ​ብ​ባ​ታ​ለህ። ይህም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ምል​ክት ይሆ​ናል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የብረት ምጣድ ወስደህ በአንተና በከተማዪቱ መካከል እንደ ብረት ቅጥር አቁመው፤ ፊትህንም ወደ እርሷ አዙር፤ የተከበበች ትሆናለች፤ አንተም ትከብባታለህ። ይህም ለእስራኤል ቤት ምልክት ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የብረት ምጣድም ውሰድ፥ በአንተና በከተማይቱ መካከል የብረት ቅጥር አድርገው፥ ፊትህንም ወደ እርሷ አቅና፥ የተከበበችም ትሆናለች፥ አንተም ትከብባታለህ። ይህም ለእስራኤል ቤት ምልክት ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የብረት ምጣድም ወስደህ በአንተና በከተማይቱ መካከል እንደ ቅጽር አቁመው፤ ፊትህንም ወደ ከተማይቱ አቅና፤ የተከበበችም ትምሰል፤ የምትከባትም አንተው ነህ፤ ይህም ለእስራኤል ሕዝብ ምልክት ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የብረት ምጣድም ወስደህ በአንተና በከተማይቱ መካከል ለብረት ቅጥር አድርገው፥ ፊትህንም ወደ እርስዋ አቅና፥ የተከበበችም ትሆናለች አንተም ትከብባታለህ። ይህም ለእስራኤል ቤት ምልክት ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de




ሕዝቅኤል 4:3
13 Referências Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “ባሪ​ያዬ ኢሳ​ይ​ያስ ሦስት ዓመት ራቁ​ቱን በባዶ እግሩ እንደ ሄደ፥ እን​ዲሁ በግ​ብ​ፅና በኢ​ት​ዮ​ጵያ ላይ ሦስት ዓመት ምል​ክ​ትና ተአ​ም​ራት ይደ​ረ​ጋል።


መል​ካ​ሞ​ቹን ሸለ​ቆ​ች​ሽ​ንም ሰረ​ገ​ሎች ሞሉ​ባ​ቸው፤ ፈረ​ሰ​ኞ​ችም መቆ​ሚ​ያ​ቸ​ውን በበ​ሮ​ችሽ ላይ አደ​ረጉ።


እነሆ፥ እኔና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠኝ ልጆች ለእ​ስ​ራ​ኤል በጽ​ዮን ተራራ ከሚ​ኖ​ረው ከሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ምል​ክ​ትና ተአ​ም​ራት ነን።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በይ​ሁዳ ንጉሥ በሴ​ዴ​ቅ​ያስ በዘ​ጠ​ነ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርና ሠራ​ዊቱ ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጥ​ተው ከበ​ቡ​አት።


በሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስም በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በአ​ራ​ተ​ኛው ወር፥ ከወ​ሩም በዘ​ጠ​ነ​ኛው ቀን ከተ​ማ​ዪቱ ተለ​ያ​የች።


ደግ​ሞም፦ እኔ ምል​ክ​ታ​ችሁ ነኝ፤ እኔ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እን​ዲሁ ይደ​ረ​ግ​ባ​ቸ​ዋል፥ እነ​ር​ሱ​ንም ማር​ከው ይወ​ስ​ዷ​ቸ​ዋል በል።


ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ምል​ክት አድ​ር​ጌ​ሃ​ለ​ሁና በፊ​ታ​ቸው ዕቃ​ህን በት​ከ​ሻህ ላይ አን​ግ​ተው፤ በጨ​ለ​ማም ተሸ​ክ​መህ ውጣ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም እን​ዳ​ታይ ፊት​ህን ሸፍን።”


የእ​ስ​ራ​ት​ህም ወራት በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ በከ​ተ​ማ​ዪቱ መካ​ከል ሢሶ​ውን በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ሢሶ​ው​ንም ወስ​ደህ ዙሪ​ያ​ውን በጎ​ራዴ ትመ​ታ​ለህ፤ ሢሶ​ው​ንም ወደ ነፋስ ትበ​ት​ና​ለህ፤ እኔም በኋ​ላ​ቸው ጎራዴ እመ​ዝ​ዛ​ለሁ።


ቍር​ባ​ን​ህም በም​ጣድ የተ​ጋ​ገረ ቍር​ባን ቢሆን፥ በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ የመ​ል​ካም ስንዴ ዱቄት ቂጣ ይሁን።


ስም​ዖ​ንም ባረ​ካ​ቸው፤ እና​ቱን ማር​ያ​ም​ንም እን​ዲህ አላት፤ “እነሆ፥ ይህ ሕፃን ከእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ለብ​ዙ​ዎች ለመ​ው​ደ​ቃ​ቸ​ውና ለመ​ነ​ሣ​ታ​ቸው፥ ለሚ​ቃ​ወ​ሙ​ትም ምል​ክት ይሆን ዘንድ የተ​ሠ​የመ ነው፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ራሱ ፈቃድ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ጸጋ በመ​ስ​ጠት፥ በም​ል​ክ​ትና በድ​ንቅ ነገር፥ በልዩ ልዩ ተአ​ም​ራ​ትም መሰ​ከ​ረ​ላ​ቸው፤ ነገ​ራ​ቸ​ው​ንም አስ​ረ​ዳ​ላ​ቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios