Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፀአት 9:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 በረ​ዶም ነበረ፤ በበ​ረ​ዶ​ውም መካ​ከል እሳት ይቃ​ጠል ነበር፤ በረ​ዶ​ውም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ ሕዝብ ከኖ​ረ​በት ጊዜ ጀምሮ እስ​ከ​ዚች ቀን እንደ እርሱ ያል​ሆነ እጅግ ብዙና ጠን​ካራ ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 በረዶ ወረደ፤ መብረቅም አብረቀረቀ፤ ግብጽ አገር ከሆነችበት ዘመን አንሥቶ በምድሪቱ ሁሉ እንደዚህ ያለ አስከፊ ማዕበል ሆኖ አያውቅም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 በረዶና እሳት ነበረ፥ በበረዶውም መካከል እጅግ ከባድ የሚበርቅ እሳት ነበር፥ በግብጽ ምድር ሁሉ አገር ከሆነ ጀምሮ እንደ እርሱ ሆኖ አያውቅም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እግዚአብሔር በዚህና በዚያ ከሚራወጥ የመብረቅ ብልጭልጭታ ጋር ከባድ የበረዶ ዝናብ አወረደ፤ ይህም ዐይነቱ የበረዶ ዝናብ በግብጽ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 በረዶም ነበረ፤ በበረዶውም መካከል እሳት ይቃጠል ነበር፤ በረዶውም በግብፅ አገር ሁሉ ሕዝብ ከሆነ ጀምሮ እንደ እርሱ ያልሆነ እጅግ ታላቅ ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፀአት 9:24
11 Referências Cruzadas  

ይህስ በጠ​ላ​ትህ ጊዜ ለሰ​ል​ፍና ለጦ​ር​ነት ቀን ይጠ​በ​ቅ​ል​ሃ​ልን?


በክ​ር​ክር ውኃ ዘን​ድም አስ​ቈ​ጡት፥ ስለ እነ​ር​ሱም ሙሴ ተበ​ሳጨ፤


ከልዩ ሰው ባሪ​ያ​ህን አድ​ነው። ካል​ገ​ዙኝ የዚ​ያን ጊዜ ፍጹም እሆ​ና​ለሁ፥ ከታ​ላ​ቁም ኀጢ​አቴ እነ​ጻ​ለሁ።


ቤቶ​ች​ህም የሹ​ሞ​ች​ህም ሁሉ ቤቶች፥ የግ​ብ​ፃ​ው​ያን ሁሉ ቤቶች በእ​ርሱ ይሞ​ላሉ፤ አባ​ቶ​ችህ፥ የአ​ባ​ቶ​ች​ህም አባ​ቶች በም​ድር ላይ ከተ​ቀ​መ​ጡ​በት ቀን ጀምሮ እስ​ከ​ዚህ ቀን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያላ​ዩት ነው።” ሙሴም ተመ​ልሶ ከፈ​ር​ዖን ዘንድ ወጣ።


እነሆ፥ ከተ​መ​ሠ​ረ​ተች ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንደ እርሱ ያለ በግ​ብፅ ሆኖ የማ​ያ​ውቅ እጅግ ታላቅ በረዶ ነገ በዚህ ጊዜ አዘ​ን​ባ​ለሁ።


ሙሴም እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነጐ​ድ​ጓ​ድና በረዶ ላከ፤ እሳ​ትም ወደ ምድር ወረደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ ላይ በረዶ አዘ​ነበ።


በረ​ዶ​ውም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ በሜዳ ያለ​ውን ሁሉ ሰው​ንና እን​ስ​ሳን መታ፤ በረ​ዶ​ውም የእ​ር​ሻን ቡቃያ ሁሉ መታ። የጫ​ካ​ው​ንም ዛፍ ሁሉ ሰበረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የድ​ም​ፁን ክብር ያሰ​ማል፤ የክ​ን​ዱ​ንም መፈ​ራት፥ በጽኑ ቍጣና በም​ት​በላ እሳት፥ በወ​ጀ​ብም፥ በዐ​ውሎ ነፋ​ስም፥ በበ​ረ​ዶም ድን​ጋይ ይገ​ል​ጣል።


እኔም አየሁ፤ እነ​ሆም ከሰ​ሜን በኩል ዐውሎ ነፋ​ስና ታላቅ ደመና፥ የሚ​በ​ር​ቅም እሳት መጣ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ፀዳል ነበረ፤ በመ​ካ​ከ​ልም በእ​ሳቱ ውስጥ የሚ​ብ​ለ​ጨ​ለጭ ነገር ነበረ።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በመ​ዓቴ በዐ​ውሎ ነፋስ እሰ​ነ​ጣ​ጥ​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ያጠ​ፋ​ውም ዘንድ በቍ​ጣዬ የሚ​ያ​ሰ​ጥም ዝናብ፥ በመ​ዓ​ቴም ታላቅ የበ​ረዶ ድን​ጋይ አወ​ር​ዳ​ለሁ።


በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናልና።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios