Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፀአት 8:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 አሮ​ንም እጁን ዘረጋ፤ በበ​ት​ሩም የም​ድ​ሩን ትቢያ መታው፤ በሰ​ውና በእ​ን​ስ​ሳም ላይ ቅማል ሆነ፤ በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ የም​ድር ትቢያ ሁሉ ቅማል ሆነ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፣ አሮን በትሩን እንደ ያዘ እጁን ሲዘረጋና የምድሩን ትቢያ ሲመታ፣ በግብጽ ምድር ያለው ትቢያ ሁሉ ተናካሽ ትንኝ ሆነ። ሰውንም ሆነ እንስሳውን ተናካሽ ትንኝ ወረረው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ሕዝቤን ባትለቅቅ፥ እነሆ በአንተ ላይ፥ በአገልጋዮችህ ላይ፤ በሕዝብህ ላይ፥ በቤቶችህም ላይ የዝንብ መንጋ እልካለሁ፤ የግብፃውያንም ቤቶች፥ የቆሙባትም ምድር ሁሉ በዝንብ መንጋ ይሞላሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እንደተባሉትም አደረጉ፤ አሮንም እጁን ዘርግቶ በበትሩ የምድሩን ትቢያ መታ፤ በግብጽ አገር ያለውም ትቢያ ሁሉ ወደ ተናካሽ ትንኝነት ተለወጠ፤ ሰዎችንና እንስሶችንም ሁሉ ሸፈነ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እንዲሁም አደረጉ፤ አሮንም እጁን ዘረጋ፤ በበትሩም የምድሩን ትቢያ መታው፤ በሰውና በእንስሳም ላይ ቅማል ሆነ፤ በግብፅ አገር ሁሉ የምድር ትቢያ ሁሉ ቅማል ሆነ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፀአት 8:17
7 Referências Cruzadas  

ያም እስከ ዘለ​ዓ​ለም ለልጅ ልጅ ጽድቅ ሆኖ ተቈ​ጠ​ረ​ለት።


ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ አል​ሁህ፤ አን​ተም ልት​ለ​ቅ​ቃ​ቸው ባት​ፈ​ቅድ፤ እኔ የበ​ኵር ልጅ​ህን እን​ደ​ም​ገ​ድል ዕወቅ።”


ከዚ​ህም በኋላ ሙሴና አሮን ወደ ፈር​ዖን ገብ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ‘በም​ድረ በዳ በዓል ያደ​ር​ግ​ልኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።’ ”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “አሮ​ንን፦ ‘በት​ር​ህን በእ​ጅህ ዘርጋ፤ የም​ድ​ሩ​ንም ትቢያ ምታ’ በለው፤ ቅማ​ልም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ በሰ​ውና በእ​ን​ስሳ ላይ ይወ​ጣል።”


የክ​ቡ​ራ​ንን ትዕ​ቢት ይሽር ዘንድ፥ የም​ድ​ር​ንም ክቡ​ራን ሁሉ ያዋ​ርድ ዘንድ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወስ​ኖ​ታል።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ስለ አል​ሰጠ ያን​ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ቀሠ​ፈው፤ ተል​ቶም ሞተ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios