Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፀአት 38:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ከእ​ር​ሱም ጋር ከዳን ነገድ የሆነ የአ​ሒ​ሳ​ሚክ ልጅ ኤል​ያብ ነበረ፤ እር​ሱም በሰ​ማ​ያዊ፥ በሐ​ም​ራዊ፥ በቀ​ይም ግምጃ፥ በጥሩ በፍታ የሽ​መና ሥራ ይሠራ ዘንድ የቅ​ርጽ፥ የሽ​መ​ናና የጥ​ልፍ ሥራ አለቃ ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ከርሱም ጋራ ከዳን ነገድ የሆነው የአሂሳሚክ ልጅ ኤልያብ፣ ዕቅድ አውጭና የእጅ ጥበብ ባለሙያ፣ በሰማያዊ፣ በሐምራዊ፣ በቀይ ማግና በቀጭን በፍታ ጥልፍ ጠላፊ ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ከእርሱም ጋር ከዳን ነገድ የሆነው የአሒሳማክ ልጅ ኤልያብ ነበረ፤ እርሱም ቀራጭ፥ ንድፍ አውጪ፥ እንዲሁም በሰማያዊ በሐምራዊ፥ በቀይ ግምጃና በጥሩ በፍታ የሚጠልፍ ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ከእርሱም ጋር ከዳን ነገድ የሆነው የአሒሳማክ ልጅ አሆሊአብም አንጥረኛ፥ ፕላን አውጪ ባለሞያ፥ እንዲሁም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ እየጠለፈ ጥሩ በፍታ የሚሠራ ሸማኔ ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ከእርሱም ጋር ከዳን ነገድ የሆነ የአሂሳሚክ ልጅ ኤልያብ ነበረ፤ እርሱም የቅርጽ ሠራተኛና ብልህ ሠራተኛ፥ በሰማያዊ በሐምራዊም በቀይም ግምጃ፥ በጥሩም በፍታ የሚሠራ ጠላፊ ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፀአት 38:23
6 Referências Cruzadas  

ሰማ​ያ​ዊና ሐም​ራዊ፥ ቀይም ድርብ ግምጃ፥ ጥሩ በፍ​ታም፥


ለድ​ን​ኳኑ ደጃ​ፍም ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀይ ግም​ጃም ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍ​ም​ታም በጥ​ልፍ አሠ​ራር የተ​ሠራ መጋ​ረጃ አድ​ር​ግ​ለት።


“እይ! ከይ​ሁዳ ነገድ የሚ​ሆን የሆር የልጅ ልጅ የኡሪ ልጅ ባስ​ል​ኤ​ልን በስሙ ጠር​ቼ​ዋ​ለሁ።


እኔም እነሆ፥ ከዳን ነገድ የሚ​ሆን የአ​ሂ​ሳ​ሚ​ክን ልጅ ኤል​ያ​ብን ሰጠሁ፤ ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ሁሉ ያደ​ርጉ ዘንድ በል​ባ​ቸው ጥበ​በ​ኞች ለሆ​ኑት ሁሉ ዕው​ቅ​ትን ሰጠሁ።


እር​ሱና የዳን ነገድ የሆ​ነው የአ​ሒ​ሳ​ሚክ ልጅ ኤል​ያብ ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ በል​ባ​ቸው አሳ​ደ​ረ​ባ​ቸው።


“ባስ​ል​ኤ​ልና ኤል​ያብ፥ ለመ​ቅ​ደ​ስም ማገ​ል​ገያ ሥራ ሁሉ ያደ​ርጉ ዘንድ እን​ዲ​ያ​ውቁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​ብ​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን የሰ​ጣ​ቸው በል​ባ​ቸ​ውም ጥበ​በ​ኞች የሆኑ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ነገር ሁሉ አደ​ረጉ።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios