Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፀአት 32:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ሙሴም፥ “ዛሬ በረ​ከ​ትን እን​ዲ​ያ​ወ​ር​ድ​ላ​ችሁ ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ ከል​ጁና፥ ከወ​ን​ድሙ የተ​ነሣ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በእ​ጃ​ችሁ ደስ አሰ​ኛ​ች​ሁት” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ከዚያም ሙሴ፣ “በራሳችሁ ወንዶች ልጆችና ወንድሞች ላይ በመነሣታችሁ፣ በዛሬዋ ቀን ለእግዚአብሔር የተለያችሁ ሆናችኋል፤ በዛሬዋም ዕለት ባርኳችኋል” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ሙሴም “ዛሬ በላያችሁ ላይ በረከት እንዲያወርድ እያንዳንዱ በልጁና በወንድሙ ላይ ተነሥቷልና ዛሬ ለጌታ እጃችሁን ቀደሳችሁ” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ሙሴም ሌዋውያንን እንዲህ አለ፤ “ዛሬ ልጆቻችሁንና ወንድሞቻችሁን በመግደል እግዚአብሔርን የምታገለግሉ ካህናት ሆናችሁ ራሳችሁን ቀድሳችኋል፤ እግዚአብሔርም በረከቱን ሰጥቶአችኋል።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ሙሴም፦ ዛሬ በረከትን እንዲያወርድላችሁ እያንዳንዳችሁ በልጃችሁና በወንድማችሁ ላይ ዛሬ እጃችሁን ለእግዚአብሔር ቅዱስ አድርጉ አለ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፀአት 32:29
11 Referências Cruzadas  

በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ መሥ​ራት የሚ​ች​ሉ​ትን ሌዋ​ው​ያን ራሳ​ቸ​ውን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲ​ያ​ነ​ጹና ቅድ​ስ​ቲ​ቱ​ንም ታቦት የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የዳ​ዊት ልጅ ሰሎ​ሞን በሠ​ራው ቤት ውስጥ እን​ዲ​ያ​ኖሩ አዘ​ዛ​ቸው። ንጉ​ሡም ኢዮ​ስ​ያስ አለ፥ “በት​ከ​ሻ​ችሁ የም​ት​ሸ​ከ​ሙት አን​ዳች ነገር አይ​ኑር፤ አሁ​ንም አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ሕዝ​ቡን እስ​ራ​ኤ​ልን አገ​ል​ግሉ፤


የሌ​ዊም ልጆች ሙሴ እን​ዳለ አደ​ረጉ፤ በዚ​ያም ቀን ከሕ​ዝቡ ሦስት ሺህ ሰዎች ሞቱ።


በነ​ጋ​ውም ሙሴ ለሕ​ዝቡ፥ “እና​ንተ ታላቅ በደል ሠር​ታ​ች​ኋል፤ አሁ​ንም አስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ችሁ ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እወ​ጣ​ለሁ፤” አላ​ቸው።


ጽድቅንና ቅን ፍርድን ማድረግ መሥዋዕት ከመሠዋት ይልቅ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ ነው።


ማንም ደግሞ ትንቢት ቢናገር የወለዱት አባቱና እናቱ፦ አንተ በእግዚአብሔር ስም ሐሰትን ተናግረሃልና በሕይወት አትኖርም ይሉታል፣ ትንቢትንም ሲናገር የወለዱት አባቱና እናቱ ይወጉታል።


ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios