Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፀአት 32:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ሙሴም ተመ​ለሰ፤ ሁለ​ቱ​ንም የም​ስ​ክር ጽላት በእጁ ይዞ ከተ​ራ​ራው ወረደ፤ የድ​ን​ጋይ ጽላ​ቱም በዚ​ህና በዚያ በሁ​ለት ወገን ተጽ​ፎ​ባ​ቸው ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሙሴም ሁለቱን የምስክር ጽላት በእጆቹ ይዞ ከተራራው ወረደ፤ ጽላቱም ከፊትና ከኋላ በሁለቱም ጐኖች ተጽፎባቸው ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ሙሴም ተመለሰ፥ ሁለቱንም የምስክር ጽላቶች በእጁ ይዞ ከተራራው ወረደ፤ ጽላቶቹም በዚህና በዚያ በሁለት ወገን ተጽፎባቸው ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከዚህ በኋላ ሙሴ ተነሥቶ በሁለቱም በኩል ዐሥሩ ትእዛዞች የተጻፉባቸውን ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶች በመያዝ ከተራራው ወረደ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ሙሴም ተመለሰ፥ ሁለቱንም የምስክር ጽላቶች በእጁ ይዞ ከተራራው ወረደ፤ ጽላቶቹም በዚህና በዚያ በሁለት ወገን ተጽፎባቸው ነበር።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፀአት 32:15
14 Referências Cruzadas  

እነ​ዚያ በፈ​ረ​ሶ​ችና በሰ​ረ​ገ​ላ​ዎች ይታ​መ​ናሉ፤ እኛ ግን በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ከፍ ከፍ እን​ላ​ለን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ ይጠ​በቅ ዘንድ አሮን በም​ስ​ክሩ ፊት አኖ​ረው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ወደ እኔ ወደ ተራ​ራው ውጣ፤ በዚ​ያም ሁን፤ እኔ የጻ​ፍ​ሁ​ትን ሕግና ትእ​ዛዝ፥ የድ​ን​ጋ​ይም ጽላት እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ ሕግ​ንም ትሠ​ራ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ” አለው።


ሙሴም ወደ ደመ​ናው ውስጥ ገባ፤ ወደ ተራ​ራ​ውም ወጣ፤ ሙሴም በተ​ራ​ራው ላይ አርባ ቀን፥ አርባ ሌሊ​ትም ቈየ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር በሲና ተራራ የተ​ና​ገ​ረ​ውን በፈ​ጸመ ጊዜ ሁለ​ቱን የም​ስ​ክር ጽላት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት የተ​ጻ​ፈ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ጽላት ለሙሴ ሰጠው።


ጽላቱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ ነበሩ፤ ጽሕ​ፈ​ቱም በጽ​ላቱ ላይ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ባ​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽሕ​ፈት ነበረ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሙሴ ከሲና ተራራ በወ​ረደ ጊዜ ሁለቱ ጽላት በሙሴ እጅ ነበሩ፤ ሙሴም ከተ​ራ​ራው በወ​ረደ ጊዜ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ሲነ​ጋ​ገር ፊቱ እን​ዳ​ን​ጸ​ባ​ረቀ አላ​ወ​ቀም ነበር።


ሙሴም ጽላ​ቱን ወስዶ በታ​ቦቱ ውስጥ አኖ​ረው፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም በታ​ቦቱ ቀለ​በ​ቶች ውስጥ አደ​ረገ፤ የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በታ​ቦቱ ላይ አኖ​ረው።


እና​ንተ ራሳ​ች​ሁም በእኛ የተ​ላ​ከች የክ​ር​ስ​ቶስ መል​እ​ክት እንደ ሆና​ችሁ ያው​ቃሉ፤ ይህ​ቺ​ውም የተ​ጻ​ፈች በሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነው እንጂ በቀ​ለም አይ​ደ​ለም፤ በሥጋ ልብ ሠሌ​ዳ​ነት ነው እንጂ በድ​ን​ጋይ ሠሌ​ዳም አይ​ደ​ለም።


ስለ​ዚያ ስለ አለ​ፈው የፊቱ ብር​ሃን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የሙ​ሴን ፊት መመ​ል​ከት እስ​ኪ​ሳ​ና​ቸው ድረስ በዚ​ያች በድ​ን​ጋይ ላይ በፊ​ደል ለተ​ቀ​ረ​ጸች ለሞት መል​እ​ክት ክብር ከተ​ደ​ረ​ገ​ላት፥


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​ራ​ራው ላይ፤ በእ​ሳ​ትና በጨ​ለማ፥ በጭ​ጋ​ግና በዓ​ውሎ ነፋስ መካ​ከል ሆኖ በታ​ላቅ ድምፅ እነ​ዚ​ህን ቃሎች ለጉ​ባ​ኤ​ያ​ችሁ ሁሉ ተና​ገረ፤ ምንም አል​ጨ​መ​ረም። በሁ​ለ​ቱም የድ​ን​ጋይ ጽላት ላይ ጻፋ​ቸው፤ ለእ​ኔም ሰጣ​ቸው።


እኔም ተመ​ልሼ ከተ​ራ​ራው ወረ​ድሁ፤ ተራ​ራ​ውም በእ​ሳት ይነ​ድድ ነበር፤ ሁለ​ቱም የቃል ኪዳን ጽላት በሁ​ለቱ እጆች ነበሩ።


በው​ስ​ጥ​ዋም የወ​ርቅ ማዕ​ጠ​ን​ትና ሁለ​ን​ተ​ና​ዋን በወ​ርቅ የለ​በ​ጡ​አት፥ የኪ​ዳን ታቦት፥ መና ያለ​ባት የወ​ርቅ መሶ​ብና የለ​መ​ለ​መ​ችው የአ​ሮን በትር፥ የኪ​ዳ​ኑም ጽላት ነበ​ሩ​ባት።


በዙፋኑ ላይም በተቀመጠው በቀኝ እጁ ላይ በውስጥና በኋላ የተጻፈበት በሰባትም ማኅተም የተዘጋ መጽሐፍን አየሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios