Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፀአት 32:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ሙሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ም​ላኩ ፊት ጸለየ፤ አለም፥ “አቤቱ፥ በታ​ላቅ ኀይ​ልና በጽኑ እጅ ከግ​ብፅ ምድር በአ​ወ​ጣ​ኸው በሕ​ዝ​ብህ ላይ ለምን ተቈ​ጣህ?

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ነገር ግን ሙሴ የአምላኩን የእግዚአብሔርን ቸርነት ፈለገ፤ እንዲህም አለ፤ “እግዚአብሔር ሆይ በታላቅ ሥልጣንህና በኀያል ክንድህ ከግብጽ ባወጣኸው ሕዝብህ ላይ ቍጣህ ለምን ይነድዳል?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሙሴም በጌታ አምላኩ ፊት ለመነ፥ እንዲህም አለ፦ “ጌታ ሆይ በታላቅ ኃይልና በጽኑ እጅ ከግብጽ ምድር ባወጣኸው በሕዝብህ ላይ ቁጣህ ስለምን ነደደ?

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሙሴ ግን እግዚአብሔር አምላኩን በመማለድ እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ በሥልጣንህና በታላቅ ኀይልህ ከግብጽ ምድር ያወጣኸውን ሕዝብህን እስከዚህ የምትቈጣው ስለምነው?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሙሴም በእግዚአብሔር በአምላኩ ፊት ጸለየ፥ አለም፦ አቤቱ፥ ቁጣህ በታላቅ ኃይልና በጽኑ እጅ ከግብፅ ምድር ባወጣኸው በሕዝብህ ላይ ስለ ምን ተቃጠለ?

Ver Capítulo Cópia de




ዘፀአት 32:11
23 Referências Cruzadas  

አብ​ር​ሃ​ምም መለሰ፤ አለም፥ “እኔ አፈ​ርና አመድ ስሆን ከጌ​ታዬ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር እና​ገር ዘንድ አሁን ጀመ​ርሁ፤


ከግ​ብጽ ምድር ከብ​ረት እቶን ውስጥ ያወ​ጣ​ሃ​ቸው ሕዝ​ብ​ህና ርስ​ትህ ናቸ​ውና።


“እነ​ዚ​ህም በታ​ላቅ ኀይ​ል​ህና በብ​ርቱ እጅህ የተ​ቤ​ዥ​ሃ​ቸው ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህና ሕዝ​ብህ ናቸው።


በመ​ር​ከ​ቦች ወደ ባሕር የሚ​ወ​ርዱ፥ በብዙ ውኃ ሥራ​ቸ​ውን የሚ​ሠሩ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ተና​ገ​ረው እን​ዲ​ህም አለው፥ “ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኻ​ቸው ሕዝ​ብህ በድ​ለ​ዋ​ልና ሂድ፤ ፈጥ​ነህ ውረድ።


ስለ​ዚ​ህም ፈጥ​ነህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ በላ​ቸው፥ “እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ተገ​ዥ​ነት አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከባ​ር​ነ​ታ​ቸ​ውም አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ በተ​ዘ​ረጋ ክንድ፤ በታ​ላቅ ፍር​ድም እታ​ደ​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤


ፈር​ዖ​ንም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ጠርቶ፥ “ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ቹን ከእኔ፥ ከሕ​ዝ​ቤም እን​ዲ​ያ​ርቅ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ዩ​ልኝ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሠዋ ዘንድ ሕዝ​ቡን እለ​ቅ​ቃ​ለሁ” አላ​ቸው።


አቤቱ፥ ከመ​ን​ገ​ድህ ለምን አሳ​ት​ኸን? እን​ዳ​ን​ፈ​ራ​ህም ልባ​ች​ንን ለምን አጸ​ና​ህ​ብን? ስለ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ስለ ርስ​ትህ ነገ​ዶች ተመ​ለስ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ሙሴና ሳሙ​ኤል በፊቴ ቢቆ​ሙም፥ ልቤ ወደ​ዚህ ሕዝብ አያ​ዘ​ነ​ብ​ልም፤ እነ​ዚ​ህን ሕዝ​ቦች ከፊቴ አባ​ር​ራ​ቸው፤ ይውጡ።


ሬስ። አቤቱ፥ እይ፤ ተመ​ል​ከት ማንን እን​ዲህ ቃረ​ምህ? በውኑ ሴቶች የማ​ኅ​ፀ​ና​ቸ​ውን ፍሬ፥ ያሳ​ደ​ጓ​ቸ​ውን ሕፃ​ናት ይበ​ላ​ሉን? በውኑ ካህ​ኑና ነቢዩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደስ ውስጥ ይገ​ደ​ላ​ሉን?


ነገር ግን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው በአሉ፥ ከግ​ብ​ጽም ምድር አወ​ጣ​ቸው ዘንድ በፊ​ታ​ቸው በተ​ገ​ለ​ጥ​ሁ​ላ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ ፊት ስሜ እን​ዳ​ይ​ረ​ክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋ​ዮች ካህ​ናት በወ​ለ​ሉና በም​ሥ​ዋዑ መካ​ከል እያ​ለ​ቀሱ፥ “አቤቱ! ለሕ​ዝ​ብህ ራራ፤ አሕ​ዛ​ብም ይገ​ዙ​አ​ቸው ዘንድ ርስ​ት​ህን ለማ​ላ​ገጫ አሳ​ል​ፈህ አት​ስጥ፤ ከአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል፦ አም​ላ​ካ​ቸው ወዴት ነው? ስለ ምን ይላሉ?” ይበሉ።


ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ለምን በአ​ገ​ል​ጋ​ይህ ላይ ክፉ አደ​ረ​ግህ? ለም​ንስ በፊ​ትህ ሞገ​ስን አላ​ገ​ኘ​ሁም? ለም​ንስ የዚ​ህን ሁሉ ሕዝብ ሸክም በእኔ ላይ አደ​ረ​ግህ?


ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ግብ​ፃ​ው​ያን ይሰ​ማሉ፤ እኒ​ህን ሕዝብ ከእ​ነ​ርሱ በኀ​ይ​ልህ አው​ጥ​ተ​ኻ​ቸ​ዋ​ልና፤


እነ​ር​ሱም በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ወድ​ቀው፥ “የነ​ፍ​ስና የሥጋ ሁሉ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ አንድ ሰው ኀጢ​አት ቢሠራ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በማ​ኅ​በሩ ላይ ይሆ​ና​ልን?” አሉ።


ሕዝ​ቡም ወደ ሙሴ መጥ​ተው፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በአ​ንተ ስለ ተና​ገ​ርን በድ​ለ​ናል፤ እባ​ቦ​ችን ከእኛ ያር​ቅ​ልን ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ይ​ልን” አሉት። ሙሴም ስለ ሕዝቡ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸለየ።


ወንድ ልጅስ ባይ​ኖ​ረው የአ​ባ​ታ​ችን ስም ከወ​ገኑ መካ​ከል ለምን ይጠ​ፋል?


“ሳኦል እኔን ከመ​ከ​ተል ተመ​ል​ሶ​አ​ልና፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም አል​ፈ​ጸ​መ​ምና ስላ​ነ​ገ​ሥ​ሁት ተጸ​ጸ​ትሁ።” ሳሙ​ኤ​ልም አዘነ። ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios