Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፀአት 28:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ለአ​ሮ​ንም ልጆች የበ​ፍታ ቀሚ​ሶ​ችን፥ መታ​ጠ​ቂ​ያ​ዎ​ች​ንም፥ ቆቦ​ች​ንም ለክ​ብ​ርና ለመ​ለያ ታደ​ር​ግ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 የአሮን ወንድ ልጆች ክብርና ማዕርግ እንዲኖራቸው ሸሚዞችን፣ መታጠቂያዎችን፣ የራስ ማሰሪያዎችን አብጅላቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ለአሮን ልጆች እጀ ጠባቦችን፥ መታጠቂያዎችንና ቆቦችን ለክብርና ለጌጥ ትሠራላቸዋለህ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 “ለአሮንም ልጆች ክብርና ውበት ይሆንላቸው ዘንድ ሸሚዞችን፥ መታጠቂያዎችንና ቆቦችን ሥራላቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ለአሮንም ልጆች ሸሚዞችን መታጠቂያዎችንም ቆቦችንም ለክብርና ለጌጥ ታደርግላቸዋለህ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፀአት 28:40
16 Referências Cruzadas  

የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም ልብስ ለክ​ብ​ርና ለመ​ለያ እን​ዲ​ሆን ለወ​ን​ድ​ምህ ለአ​ሮን ሥራ​ለት።


የሚ​ሠ​ሩ​አ​ቸ​ውም ልብ​ሶች እነ​ዚህ ናቸው፤ ልብሰ እን​ግ​ድዓ፥ ልብሰ መት​ከፍ፥ ቀሚ​ስም፥ ዥን​ጕ​ር​ጕር እጀ ጠባብ፥ መጠ​ም​ጠ​ሚያ፥ መታ​ጠ​ቂ​ያም፤ እነ​ዚ​ህ​ንም በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ለወ​ን​ድ​ምህ ለአ​ሮን፥ ለል​ጆ​ቹም የተ​ቀ​ደሰ ልብስ ያድ​ርጉ።


ልጆ​ቹ​ንም ታቀ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ቀሚ​ሶ​ች​ንም ታለ​ብ​ሳ​ቸ​ዋ​ለህ፤


በመ​ታ​ጠ​ቂ​ያም ታስ​ታ​ጥ​ቃ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ቆብ​ንም ታደ​ር​ግ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐ​ትም ክህ​ነት ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ እን​ዲ​ሁም የአ​ሮ​ን​ንና የል​ጆ​ቹን እጆች ትቀ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ።


በመ​ቅ​ደስ ውስጥ ለማ​ገ​ል​ገል በብ​ል​ሃት የተ​ሠ​ሩ​ትን ልብ​ሶች፥ በክ​ህ​ነ​ትም ያገ​ለ​ግ​ሉ​በት ዘንድ የተ​ቀ​ደ​ሱ​ትን የካ​ህ​ኑን የአ​ሮ​ንን ልብ​ሶች፥ የል​ጆ​ቹ​ንም ልብ​ሶች አመጡ።


ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፤ ጽዮን ሆይ፥ ኀይ​ል​ሽን ልበሺ፤ አን​ቺም ቅድ​ስ​ቲቱ ከተማ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ያል​ተ​ገ​ረ​ዘና ርኩስ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ወደ አንቺ አያ​ል​ፍ​ምና ክብ​ር​ሽን ልበሺ።


በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ስፍራ ገላ​ውን በውኃ ይታ​ጠ​ባል፤ ሌላ​ው​ንም ልብስ ለብሶ ይወ​ጣል፤ የእ​ር​ሱ​ንም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ ለካ​ህ​ናቱ እን​ዳ​ስ​ተ​ሰ​ረየ ለራ​ሱም፥ ለሕ​ዝ​ቡም ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሙሴ የአ​ሮ​ንን ልጆች አቀ​ረበ፤ የበ​ፍታ ቀሚ​ሶ​ች​ንም አለ​በ​ሳ​ቸው፤ በመ​ታ​ጠ​ቂ​ያም አስ​ታ​ጠ​ቃ​ቸው፤ አክ​ሊ​ልም ደፋ​ላ​ቸው።


የሚቃወም ሰው ስለ እኛ የሚናገረውን መጥፎ ነገር ሲያጣ እንዲያፍር፥ በነገር ሁሉ መልካምን በማድረግህ ምሳሌ የሚሆን ራስህን አሳይ፤ በትምህርትህም ደኅንነትን፥ ጭምትነትን፥ ጤናማና የማይነቀፍ ንግግርን ግለጥ።


እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ልበሱ፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios