Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፀአት 28:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 ቀሚ​ሱ​ንም ከጥሩ በፍታ ዝን​ጕ​ር​ጕር አድ​ር​ገህ፥ አክ​ሊ​ልን ከበ​ፍታ ትሠ​ራ​ለህ፤ በጥ​ልፍ አሠ​ራ​ርም መታ​ጠ​ቂያ ትሠ​ራ​ለህ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 “ሸሚዙን ከቀጭን በፍታ ሥራ፤ መጠምጠሚያውንም ከቀጭን በፍታ አብጀው፤ መታጠቂያውንም ጥልፍ ጠላፊ የሠራው ይሁን።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 እጀ ጠባቡን ከጥሩ በፍታ፥ መጠምጠሚያውን ከበፍታ ትሠራለህ፥ በጥልፍ የተጠለፈ መታጠቂያ ትሠራለህ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 “የአሮንን ሸሚዝና መጠምጠሚያ ከጥሩ በፍታ ሥራው፤ መታጠቂያውም ከጥሩ በፍታ ተሠርቶ በጥልፍ ጥበብ ያጌጠ ይሁን።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 ሸሚዙንም ከጥሩ በፍታ ዝንጕርጕር አድርገህ፥ መጠምጠሚያውን ከበፍታ ትሠራለህ፤ በጥልፍ አሠራር መታጠቂያም ትሠራለህ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፀአት 28:39
10 Referências Cruzadas  

ለድ​ን​ኳኑ ደጃ​ፍም ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀይ ግም​ጃም ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍ​ም​ታም በጥ​ልፍ አሠ​ራር የተ​ሠራ መጋ​ረጃ አድ​ር​ግ​ለት።


ለአ​ደ​ባ​ባዩ ደጅም ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም ከቀ​ይም ግምጃ ከጥሩ በፍ​ታም በጥ​ልፍ አሠ​ራር የተ​ሠራ ሃያ ክንድ መጋ​ረጃ ይሆ​ናል፤ ምሰ​ሶ​ዎ​ቹም አራት፥ እግ​ሮ​ቹም አራት ይሁኑ።


የሚ​ሠ​ሩ​አ​ቸ​ውም ልብ​ሶች እነ​ዚህ ናቸው፤ ልብሰ እን​ግ​ድዓ፥ ልብሰ መት​ከፍ፥ ቀሚ​ስም፥ ዥን​ጕ​ር​ጕር እጀ ጠባብ፥ መጠ​ም​ጠ​ሚያ፥ መታ​ጠ​ቂ​ያም፤ እነ​ዚ​ህ​ንም በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ለወ​ን​ድ​ምህ ለአ​ሮን፥ ለል​ጆ​ቹም የተ​ቀ​ደሰ ልብስ ያድ​ርጉ።


ልብ​ሶ​ችን ወስ​ደህ ለወ​ን​ድ​ምህ ለአ​ሮን የነጭ ሐር እጀ ጠባብ ቀሚስ፥ ልብሰ መት​ከ​ፍና ልብሰ እን​ግ​ድዓ ታለ​ብ​ሰ​ዋ​ለህ፤ ለእ​ር​ሱም ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውን ከል​ብሰ መት​ከፉ ጋር አያ​ይ​ዝ​ለት።


አክ​ሊ​ል​ንም በራሱ ላይ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ የወ​ር​ቁ​ንም ቀጸላ በአ​ክ​ሊሉ ላይ ታኖ​ራ​ለህ።


ልጆ​ቹ​ንም ታቀ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ቀሚ​ሶ​ች​ንም ታለ​ብ​ሳ​ቸ​ዋ​ለህ፤


እንደ ሸማኔ ሥራ ከጥሩ በፍታ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ እጀ ጠባ​ቦ​ችን፥ ከጥሩ በፍ​ታም አክ​ሊ​ልን፥


የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም የተ​ልባ እግር ቀሚስ ይል​በስ፤ የተ​ልባ እግ​ርም ሱሪ በገ​ላው ላይ ይሁን፤ የተ​ልባ እግር መታ​ጠ​ቂያ ይታ​ጠቅ፤ የተ​ልባ እግር አክ​ሊ​ልም በራሱ ላይ ያድ​ርግ፤ እነ​ዚህ የተ​ቀ​ደሱ ልብ​ሶች ናቸው፤ ገላ​ው​ንም በውኃ ታጥቦ ይል​በ​ሳ​ቸው።


ካህ​ኑም የተ​ልባ እግር ቀሚ​ስና የተ​ልባ እግር ሱሪ በሰ​ው​ነቱ ላይ ይለ​ብ​ሳል፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት እሳቱ ከበ​ላው በኋላ አመ​ዱን አን​ሥቶ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios