Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፀአት 25:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 በገ​በ​ታም ላይ ኅብ​ስተ ገጹን ሁል​ጊዜ በፊቴ ታደ​ር​ጋ​ለህ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 በማንኛውም ጊዜ በፊቴ እንዲሆን በገጸ ኅብስቱ በዚህ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጥ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 በገበታው ላይ ኅብስተ ገጹን ሁልጊዜ በፊቴ ታደርጋለህ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ጠረጴዛውም በታቦቱ ፊት ለፊት ይቀመጥ፤ ለእኔ የሚቀርበው የተቀደሰ ኅብስት ዘወትር በጠረጴዛው ላይ መኖር አለበት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 በገበታም ላይ የገጽ ኅብስት ሁልጊዜ በፊቴ ታደርጋለህ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፀአት 25:30
20 Referências Cruzadas  

ሰሎ​ሞ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ዕቃን ሁሉ አሠራ፤ የወ​ር​ቁን መሠ​ዊያ፥ የገ​ጹም ኅብ​ስት የነ​በ​ረ​በ​ትን የወ​ርቅ ገበታ፥


ደግ​ሞም ገጸ ኅብ​ስት፥ ስስ ቂጣም ቢሆን፥ በም​ጣ​ድም ቢጋ​ገር፥ ቢለ​ወ​ስም ለእ​ህል ቍር​ባን በሆ​ነው በመ​ል​ካሙ ዱቄት በመ​ስ​ፈ​ሪ​ያና በልክ ሁሉ ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ሹሞ​አ​ቸው ነበር።


በየ​ሰ​ን​በ​ቱም ያዘ​ጋጁ ዘንድ ቀዓ​ታ​ዊው በን​ያ​ስና ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው በገጹ ኅብ​ስት ላይ ሹሞች ነበሩ።


በየ​ጥ​ዋ​ቱና በየ​ማ​ታ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ጣፋ​ጩን ዕጣን ያሳ​ር​ጋሉ፤ የገ​ጹ​ንም ኅብ​ስት በን​ጹሕ ገበታ ላይ፥ የወ​ር​ቁን መቅ​ረ​ዝና ቀን​ዲ​ሎ​ቹ​ንም ማታ ማታ እን​ዲ​ያ​በሩ ያዘ​ጋ​ጃሉ፤ እኛም የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ እን​ጠ​ብ​ቃ​ለን፤ እና​ንተ ግን ትታ​ች​ሁ​ታል።


ሰሎ​ሞ​ንም እን​ዲህ ሲል ወደ ጢሮስ ንጉሥ ወደ ኪራም ላከ፥ “ከአ​ባቴ ከዳ​ዊት ጋር እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ፥ የሚ​ቀ​መ​ጥ​በ​ት​ንም ቤት ይሠራ ዘንድ የዝ​ግባ እን​ጨት እንደ ላክ​ህ​ለት፥ እን​ዲሁ ለእኔ አድ​ርግ።


እነሆ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ለዘ​ለ​ዓ​ለም እንደ ታዘ​ዘው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የጣ​ፋ​ጩን ሽቱ ዕጣን ለማ​ጠን፥ የገ​ጹ​ንም ኅብ​ስት ለማ​ኖር፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት በጥ​ዋ​ትና በማታ፥ በሰ​ን​በ​ታ​ቱም፥ በመ​ባ​ቻ​ዎ​ቹም፥ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ላት ለማ​ቅ​ረብ እኔ ልጁ ለአ​ም​ላኬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት እሠ​ራ​ለሁ፤ እር​ሱ​ንም እቀ​ድ​ሳ​ለሁ።


ገበ​ታ​ው​ንና መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ ኅብ​ስተ ገጹ​ንም፤


ገበ​ታ​ው​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ ኅብ​ስተ ገጹ​ንም፤


ኅብ​ስተ ገጹ​ንም በላዩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አሰ​ናዳ።


ገበ​ታ​ው​ንም ታገ​ባ​ለህ፤ በሥ​ር​ዐ​ቱም ታሰ​ና​ዳ​ዋ​ለህ፤ መቅ​ረ​ዙ​ንም አግ​ብ​ተህ ቀን​ዲ​ሎ​ቹን ትለ​ኵ​ሳ​ለህ።


መሠ​ዊ​ያ​ውም ቁመቱ ሦስት ክንድ፥ ርዝ​መቱ ሁለት ክንድ፥ ወር​ዱም ሁለት ክንድ ሆኖ ከእ​ን​ጨት ተሠ​ርቶ ነበር፤ ማዕ​ዘ​ኖ​ቹም፥ እግ​ሩም፥ አገ​ዳ​ዎ​ቹም ከእ​ን​ጨት ተሠ​ር​ተው ነበር፤ እር​ሱም፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያለ​ችው ገበታ ይህች ናት” አለኝ።


እናንተ ግን፦ የእግዚአብሔር ገበታ ርኩስ ነው፣ ፍሬውና መብሉም የተናቀ ነው በማለታችሁ አስነቀፋችሁት።


በመሠዊያዬ ላይ ርኩስ እንጀራ ታቀርባላችሁ። እናንተም፦ ያረከስንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። የእግዚአብሔር ገበታ የተነቀፈ ነው በማለታችሁ ነው።


በኅ​ብ​ስተ ገጹ ገበታ ላይም ሰማ​ያ​ዊ​ውን መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይዘ​ር​ጉ​በት፤ በእ​ር​ሱም ላይ ወጭ​ቶ​ቹን፥ ጭል​ፋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ጽዋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ለማ​ፍ​ሰ​ስም መቅ​ጃ​ዎ​ቹን ያድ​ር​ጉ​በት፤ ሁል​ጊ​ዜም የሚ​ኖር ኅብ​ስት በእ​ርሱ ላይ ይሁን።


የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዪ​ቱም ድን​ኳን ተዘ​ጋ​ጅታ ነበ​ርና፥ በእ​ር​ስ​ዋም ቅድ​ስት በም​ት​ባ​ለው ውስጥ መቅ​ረ​ዙና ጠረ​ጴ​ዛው፥ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱም ኅብ​ስት ነበ​ረ​ባት።


ካህ​ኑም ለዳ​ዊት መልሶ፥ “ሁሉ የሚ​በ​ላው እን​ጀራ የለ​ኝም፤ ነገር ግን የተ​ቀ​ደሰ እን​ጀራ አለ፤ ብላ​ቴ​ኖቹ ከሴ​ቶች ንጹ​ሓን እንደ ሆኑ መብ​ላት ይች​ላሉ” አለው።


ዳዊ​ትም ለካ​ህኑ መልሶ፥ “ከሴ​ቶች ተለ​ይ​ተን ወደ መን​ገድ ከወ​ጣን ዛሬ ሦስ​ተኛ ቀና​ችን ነው። እኔም ብላ​ቴ​ኖ​ቼም ንጹ​ሓን ነን። ነገር ግን ዛሬ ሰው​ነቴ ንጽ​ሕት ስለ ሆነች ነው እንጂ ይህች መን​ገድ የነ​ጻች አይ​ደ​ለ​ችም” አለው።


ካህኑ አቤ​ሜ​ሌ​ክም በእ​ርሱ ፋንታ ትኩስ እን​ጀራ ይደ​ረግ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከአ​ለው ኅብ​ስት በቀር ሌላ እን​ጀራ አል​ነ​በ​ረ​ምና የቍ​ር​ባ​ኑን ኅብ​ስት ሰጠው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios