Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፀአት 22:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 መበ​ለ​ቲ​ቱ​ንና ድሀ-አደ​ጎ​ቹን አታ​ስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 “ባል በሞተባት ወይም አባትና እናት በሌለው ልጅ ላይ ግፍ አትዋሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ብታስጨንቁአቸውና ወደ እኔ ቢጮኹ ግን እኔ ጩኸታቸውን በእርግጥ እሰማለሁ፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ባልዋ የሞተባትን መበለት ወይም አባትና እናት የሞቱበትን ድኻ ዐደግ አታጒላሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 መበለቲቱንና ድሀ አደጎቹን አታስጨንቁአቸው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፀአት 22:22
23 Referências Cruzadas  

“ድሆች የሚ​ሹ​ትን እን​ዳ​ያ​ገኙ አድ​ርጌ እንደ ሆነ፥ የመ​በ​ለ​ቲ​ቱ​ንም ዐይን አጨ​ልሜ እንደ ሆነ፥


እር​ሱም የድ​ሆ​ችን ጩኸት በእ​ነ​ርሱ ላይ ይመ​ል​ሳል፥ የች​ግ​ረ​ኞ​ች​ንም ልቅሶ ይሰ​ማል።


በከ​ንቱ ያጠ​ፉኝ ዘንድ ወጥ​መ​ዳ​ቸ​ውን ሸሽ​ገ​ው​ብ​ኛ​ልና፥ ነፍ​ሴን በከ​ንቱ አበ​ሳ​ጭ​ተ​ዋ​ታ​ልና።


እግዚአብሔር ፍርዱን ይፈርድለታልና። አንተም ነፍስህን በሰላም ታድናለህ።


አባቶችህ ያኖሩትን የድንበር ምልክት አታፍልስ፤ ወደ ድሃ አደጎች እርሻም አትግባ፤


ታዳጊአቸው እግዚአብሔር ጽኑ ነውና፥ እርሱም ፍርዳቸውን ከአንተ ጋር ይፋረዳልና።


መል​ካም መሥ​ራ​ትን ተማሩ፤ ፍር​ድን ፈልጉ፤ የተ​ገ​ፋ​ውን አድኑ፤ ለድ​ሃ​አ​ደጉ ፍረ​ዱ​ለት፤ ስለ መበ​ለ​ቲ​ቱም ተሙ​አ​ገቱ።”


አለ​ቆ​ችሽ ዐመ​ፀ​ኞ​ችና የሌ​ቦች ባል​ን​ጀ​ሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወ​ድ​ዳሉ፤ ፍር​ድ​ንም ሊያ​ጣ​ምሙ ይፈ​ል​ጋሉ፤ ለሙት ልጅ አይ​ፈ​ር​ዱም፤ የመ​በ​ለ​ቲ​ቱ​ንም አቤ​ቱታ አያ​ዳ​ም​ጡም።


መበ​ለ​ቶች ቅሚ​ያ​ቸው እን​ዲ​ሆኑ፥ የሙት ልጆ​ች​ንም ብዝ​በ​ዛ​ቸው እን​ዲ​ያ​ደ​ርጉ፥ የድ​ሃ​ውን ፍርድ ያጣ​ምሙ ዘንድ፥ የች​ግ​ረ​ኛ​ው​ንም ሕዝ​ቤን ፍርድ ያጐ​ድሉ ዘንድ የግ​ፍን ትእ​ዛ​ዛት ለሚ​ያ​ዝዙ ወዮ​ላ​ቸው!


መጻ​ተ​ኛ​ው​ንና ድሃ​አ​ደ​ጉን፥ መበ​ለ​ቲ​ቱ​ንም ባት​ገፉ፥ በዚ​ህም ስፍራ ንጹሕ ደምን ባታ​ፈ​ስሱ፥ ክፉም ሊሆ​ን​ባ​ችሁ እን​ግ​ዶ​ችን አማ​ል​ክት ባት​ከ​ተሉ፤


ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ በሰ​ጠ​ኋ​ቸው ምድር በዚህ ስፍራ አሳ​ድ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።


በአ​ንቺ ውስጥ አባ​ት​ንና እና​ትን አቃ​ለሉ፤ በመ​ካ​ከ​ልሽ በመ​ጻ​ተ​ኛው ላይ በደ​ልን አደ​ረጉ፤ በአ​ንቺ ውስጥ ድሀ አደ​ጉ​ንና መበ​ለ​ቲ​ቱን አስ​ጨ​ነቁ።


መጻተኛውንና ችግረኛውን አትበድሉ፣ ከእናንተም ማንም በወንድሙ ላይ ክፉውን ነገር በልቡ አያስብ።


ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፣ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! በጸሎት ርዝመት እያመካኛችሁ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ፥ ወዮላችሁ፤ ስለዚህ የባሰ ፍርድ ትቀበላላችሁ።


ለመ​ጻ​ተኛ፥ ለድሃ አደ​ጉና ለመ​በ​ለ​ቲቱ ይፈ​ር​ዳል፤ መብ​ልና ልብ​ስም ይሰ​ጠው ዘንድ ስደ​ተ​ኛ​ውን ይወ​ድ​ዳል።


ሰባ​ተ​ኛው ዓመት የም​ሕ​ረት ዓመት ቅርብ ነው፤ አል​ሰ​ጠ​ው​ምም ብለህ ክፉ ዐሳብ በል​ብህ እን​ዳ​ታ​ስብ ለራ​ስህ ዕወቅ። ወን​ድ​ም​ህም ዐይ​ኑን በአ​ንተ ላይ ያከ​ፋል፤ እር​ሱም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ንተ ላይ ይጮ​ሃል፤ ኀጢ​አ​ትም ይሆ​ን​ብ​ሃል።


“የመ​ጻ​ተ​ኛ​ው​ንና የድሃ-አደ​ጉን፥ የመ​በ​ለ​ቲ​ቱ​ንም ፍርድ አታ​ጣ​ም​ም​ባ​ቸው፤ የመ​በ​ለ​ቲ​ቱ​ንም ልብስ ለመ​ያዣ አት​ው​ሰ​ድ​ባት።


አን​ተም በግ​ብፅ ባሪያ እንደ ነበ​ርህ፥ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚያ እን​ዳ​ዳ​ነህ ዐስብ፤ ስለ​ዚህ ይህን ነገር ታደ​ርግ ዘንድ አዝ​ዤ​ሃ​ለሁ።


“በመ​ጻ​ተኛ፥ በድሃ-አደ​ጉም፥ በመ​በ​ለ​ቲ​ቱም ላይ ፍር​ድን የሚ​ያ​ጣ​ምም ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።


ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios