Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፀአት 21:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 በሬ​ውም ትና​ን​ትና ከት​ና​ንት ወዲያ ተዋጊ መሆኑ ቢታ​ወቅ ለባ​ለ​ቤ​ቱም ቢመ​ሰ​ክ​ሩ​ለት፥ ባለ​ቤ​ቱም ባያ​ስ​ወ​ግ​ደው በሬ​ውን በበ​ሬው ፋንታ ይስጥ፤ የሞ​ተ​ውም ለእ​ርሱ ይሁ​ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ሆኖም በሬው የመዋጋት ዐመል ያለው መሆኑ ከታወቀ፣ ባለቤቱም በረት ሳይዘጋበት ቢቀር፣ ባለቤቱ በሬውን በበሬው ፈንታ ይክፈል፤ የሞተውም እንስሳ ለርሱ ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 በሬው አስቀድሞ ተዋጊ መሆኑ ቢታወቅ፥ ባለቤቱም ባይጠብቀው፥ በሬውን በበሬው ፈንታ ይስጥ፥ የሞተውም ለእርሱ ይሁነው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ነገር ግን በሬው ተዋጊ መሆኑ ታውቆ ሳለ ባለቤቱ በበረት ውስጥ ሳይዘው ቀርቶ ከሆነ፥ በሬው ለሞተበት ሰው አንድ በሕይወት ያለ በሬ ካሣ ይክፈል፤ የሞተውንም በሬ ለራሱ ያስቀር።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 በሬውም አስቀድሞ ተዋጊ መሆኑ ቢታወቅ፥ ባለቤቱም ባይጠብቀው፥ በሬውን በበሬው ፈንታ ይስጥ፥ የሞተውም ለእርሱ ይሁነው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፀአት 21:36
4 Referências Cruzadas  

በሬው ግን ከት​ና​ን​ትና ከት​ና​ንት ወዲያ ተዋጊ ቢሆን፥ ሰዎ​ችም ለባ​ለ​ቤቱ ቢመ​ሰ​ክ​ሩ​ለት ባያ​ስ​ወ​ግ​ደ​ውም፥ ወን​ድን ወይም ሴትን ቢገ​ድል፥ በሬው ይወ​ገር፤ ባለ​ቤቱ ደግሞ ይገ​ደል።


“የሰው በሬ የሌ​ላ​ውን በሬ ቢወጋ፥ ቢሞ​ትም፥ ደኅ​ና​ውን በሬ ይሽጡ፤ ዋጋ​ው​ንም በት​ክ​ክል ይካ​ፈሉ፤ የሞ​ተ​ው​ንም ደግሞ በት​ክ​ክል ይካ​ፈሉ።


“ሰው በሬ ወይም በግ ቢሰ​ርቅ፥ ቢያ​ር​ደው ወይም ቢሸ​ጠው፥ በአ​ንድ በሬ ፋንታ አም​ስት በሬ​ዎች፥ በአ​ንድ በግም ፋንታ አራት በጎች ይክ​ፈል።


እን​ስ​ሳ​ንም ቢገ​ድል በነ​ፍስ ፋንታ ነፍስ ይክ​ፈል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios