Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፀአት 16:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ ይጠ​በቅ ዘንድ አሮን በም​ስ​ክሩ ፊት አኖ​ረው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አሮን፣ መናው ይጠበቅ ዘንድ በምስክሩ ፊት አስቀመጠው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ ተጠብቆ እንዲኖር አሮን በምስክሩ ፊት አስቀምጠው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት አሮን ለመጪው ትውልድ ተጠብቆ እንዲኖር መናውን በኪዳኑ ታቦት ፊት አኖረው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ ይጠበቅ ዘንድ አሮን በምስክሩ ፊት አኖረው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፀአት 16:34
13 Referências Cruzadas  

በታ​ቦ​ቷም ውስጥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር በወጡ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን ባደ​ረገ ጊዜ ሙሴ በኮ​ሬብ ካስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው የቃል ኪዳን ጽላት ከሚ​ባ​ሉት ከሁ​ለቱ የድ​ን​ጋይ ጽላት በቀር ምንም አል​ነ​በ​ረ​ባ​ትም።


በታ​ቦ​ቱም ውስጥ እኔ የም​ሰ​ጥ​ህን ምስ​ክር ታስ​ቀ​ም​ጣ​ለህ።


የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በታ​ቦቱ ላይ ታደ​ር​ገ​ዋ​ለህ፤ እኔም የም​ሰ​ጥ​ህን ምስ​ክር በታ​ቦቱ ውስጥ ታኖ​ረ​ዋ​ለህ።


በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ካለው መጋ​ረጃ ውጭ አሮ​ንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያብ​ሩት፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃ​ቸው የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁን።


ከእ​ር​ሱም ጥቂት ትወ​ቅ​ጣ​ለህ፤ ታል​መ​ው​ማ​ለህ፤ ከዚ​ያም ለአ​ንተ በም​ገ​ለ​ጥ​በት በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በም​ስ​ክሩ ፊት ታኖ​ረ​ዋ​ለህ። እር​ሱም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ይሁ​ን​ላ​ችሁ።


ለአ​ንተ በም​ገ​ለ​ጥ​በት በም​ስ​ክሩ ታቦት ላይ ባለው መጋ​ረጃ ፊት ታኖ​ረ​ዋ​ለህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር በሲና ተራራ የተ​ና​ገ​ረ​ውን በፈ​ጸመ ጊዜ ሁለ​ቱን የም​ስ​ክር ጽላት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት የተ​ጻ​ፈ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ጽላት ለሙሴ ሰጠው።


በካ​ህኑ በአ​ሮን ልጅ በይ​ታ​ምር እጅ የሌ​ዋ​ው​ያን ተል​እኮ ይሆን ዘንድ ሙሴ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ደ​ታ​ዘዘ የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ሥር​ዐት ይህ ነው።


ሙሴም ጽላ​ቱን ወስዶ በታ​ቦቱ ውስጥ አኖ​ረው፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም በታ​ቦቱ ቀለ​በ​ቶች ውስጥ አደ​ረገ፤ የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በታ​ቦቱ ላይ አኖ​ረው።


ነገር ግን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳ​ንና በዕ​ቃ​ዎ​ችዋ ሁሉ፥ በው​ስ​ጥ​ዋም ባለው ነገር ሁሉ ላይ ሌዋ​ው​ያ​ንን አቁ​ማ​ቸው። ድን​ኳ​ን​ዋ​ንና ዕቃ​ዎ​ች​ዋን ሁሉ ይሸ​ከሙ፤ ያገ​ል​ግ​ሉ​አ​ትም፤ በድ​ን​ኳ​ን​ዋም ዙሪያ ይስ​ፈሩ።


ነገር ግን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ዕዳ እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ቸው ሌዋ​ው​ያን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ ፊት ለፊት ይስ​ፈሩ፤ ሌዋ​ው​ያን የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሕግ ይጠ​ብቁ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “ማጕ​ረ​ም​ረ​ማ​ቸው ከእኔ ዘንድ እን​ዲ​ጠፋ፥ እነ​ር​ሱም እን​ዳ​ይ​ሞቱ ለማ​ይ​ሰሙ ልጆች ምል​ክት ሆና ትጠ​በቅ ዘንድ የአ​ሮ​ንን በትር በም​ስ​ክሩ ፊት አኑር።”


ተመ​ል​ሼም ከተ​ራ​ራው ወረ​ድሁ፤ ጽላ​ቱ​ንም በሠ​ራ​ሁት ታቦት ውስጥ አደ​ረ​ግ​ኋ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘኝ በዚያ ኖሩ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios